16/10/2025
የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ለሀላባ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ለሁለተኛ ዙር የአንድ ወር ደሞዛቸውን ድጋፍ አደረጉ
በህዝብ ተሳትፎ እየተገነባ የሚገኘው የሀላባ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ግንባታ ድጋፍ በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠናክሮ የቀጠለ ስሆን በዛሬው ዕለት የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር አመራሮች የአንድ ወር ደሞዛቸውን ድጋፍ አድርጓል።
የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አ/መጅድ ፍጣሞና የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሁሴን አብደላ የዉይይት መድረኩን መርቷል።
በመድረኩም ስታዲዬማችን ከምንም በላይ ቅድሚያ የምንሰጠው ታላቅ ፕሮጄክት በመሆኑ ድጋፍ በቀጣይ በፐብሊክ ሰርቫንቲ በአርሶ አደር በነዋሪዎች ና በሌሎች በሁሉም ዘርፎች ተጠናክሮ የምቀጥል እንደሆነም ተገልጿል።
አመራሩ ከደሞዙ በተጨማሪ በተለያዩ ቻሌንጆች በመሳተፍ ስታዲየም ግንባታው እስኪጠናቀቅ ድጋፉን እንደምቀጥሉ ቃል ገብተዋል።