Ancharo News

Ancharo News ገፃችን ላይክ በማድረግ አዳዲስ እና ትኩስ ዜናዎችን፤ጠቃሚና አስፈላጊ መረጃዎችን እና ስለ ሀገራችን ዋና ዋና ጉዳዪችን ያገኛሉ።
መረጃ እውቀት ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሳምንት 3 ቀናት ወደ ሞንሮቪያ ለመብረር መዘጋጀቱን አስታወቀአዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሕዳር 21 ቀን 2017 ዓ...
23/10/2024

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሳምንት 3 ቀናት ወደ ሞንሮቪያ ለመብረር መዘጋጀቱን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሕዳር 21 ቀን 2017 ዓ.ል ጀምሮ በሳምንት ሦስት ቀናት ወደ ላይቤሪያ ሞንሮቪያ የሚያደርገውን የመንገደኞች የበረራ አገልግሎት እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ ወደ ሞንሮቪያ በሣምንት ሦስት ቀናት መብረሩ በምዕራብ አፍሪካ ያለውን ግንኙነት እንደሚያጎለብተው ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም በምዕራብ አፍሪካ እና ለአካባቢው ኢኮኖሚ እድገት ከፍኛ አስተዋፅዖ እንደሚያበረክት መገለጹን የአየር መንገዱ መረጃ አመላክቷል፡፡

The six-year-old remained alive for hours among the bodies of her dead relatives after they were attacked by Israeli tro...
23/06/2024

The six-year-old remained alive for hours among the bodies of her dead relatives after they were attacked by Israeli troops.

23/06/2024

ወሎዬ ነኝ

17/04/2024

Apr 17,2024
Ancharo News

ገፃችን ላይክ በማድረግ አዳዲስ እና ትኩስ ዜናዎችን፤ጠቃሚና አስፈላጊ መረጃዎችን እና ስለ ሀገራችን ዋና ዋና ጉዳዪችን ያገኛሉ።
መረጃ እውቀት ነው።

28/09/2023

የጫት ኢማም

በጎንደር ከተማ ያለውን የጸጥታ ሁኔታ አስመልክቶ በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰው መረጃ ፈጽሞ ከእውነት የራቀ ነው- ብርጋዴር ጄኔራል ማርዬ በየነአዲስ አበባ ፤ መስከረም 16/2016 (ኢዜአ)፦ ...
27/09/2023

በጎንደር ከተማ ያለውን የጸጥታ ሁኔታ አስመልክቶ በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰው መረጃ ፈጽሞ ከእውነት የራቀ ነው- ብርጋዴር ጄኔራል ማርዬ በየነ

አዲስ አበባ ፤ መስከረም 16/2016 (ኢዜአ)፦ በጎንደር ከተማ ያለውን የጸጥታ ሁኔታ አስመልክቶ በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰው መረጃ ፈጽሞ ከእውነት የራቀ መሆኑን የጎንደር ከተማ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ብርጋዴር ጄኔራል ማርዬ በየነ ገለጹ፡፡

ኮማንድ ፖስቱ ጽንፈኛ ቡድኑ ላይ እየወሰደ ካለው እርምጃ ባሻገር የከተማዋን ነዋሪዎች በማወያየት ባከናወነው ስራ የከተማዋ የሰላም ሁኔታ መሻሻሉንም ነው የተናገሩት፡፡

ጽንፈኛ ቡድኑ የኢትዮጵያን ህልውና እና ሰላም ከማይፈልጉ አካላት የሚላክለትን ፍርፋሪ በመጠቀም ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት የሚፈጽም የህዝብ ጠላት መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ኮማንድ ፖስቱ ከህዝብ ጋር ባደረገው ውይይትም ህብረተሰቡ የጽንፈኛ ቡድኑን እኩይ ድርጊት በግልጽ ማንሳቱን ጠቅሰዋል፡፡

ነገር ግን ከጽንፈኛ ቡድኑ ጎን የተሰለፉ አንዳንድ አካላት በማህበራዊ ሚዲያ የሃሰት መረጃዎችን በማሰራጨት ህዝብ ለማደናገር እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ለአብነትም ባለፉት ቀናት "ብርጋዴር ጄኔራል ማርዬ ተገድለዋል" በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የሃሰት መረጃ ሲያሰራጩ መቆየታቸውን አንስተዋል፡፡

በተጨማሪም "ክፍለ ጦር ደመሰስን፤ ታንክ ማረክን፤ አውሮፕላን ጣልን" የሚሉ የበሬ ወለደ መረጃዎችን ሲያሰራጩ መቆየታቸውን ጠቁመዋል፡፡

በመሆኑም ህብረተሰቡ ሆነ ብለው የሃሰት መረጃ በሚያሰራጩ የጽንፈኛው ቡድን አባላት መደናገር የለበትም ነው ያሉት፡፡

ኮማንድ ፖስቱ በጽንፈኛ ቡድኑ ላይ ከሚወስደው እርምጃ ባሻገር ህዝብን በማወያየት ዘላቂ ሰላም ለማስፈን እየሰራ መሆኑንም ብርጋዴር ጄኔራል ማርዬ ተናግረዋል፡፡

በዚህም የመከላከያ ሰራዊቱ የተሰጠውን ግዳጅ በብቃት እየተወጣ ነው ብለዋል፡፡

በቅርቡ በጎንደር ከተማ በአንድ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ተኩስ በመክፈት ለማምለጥ በሞከሩ የጽንፈኛው ኃይል አባላት ላይ እርምጃ በመውሰድ የከተማዋን ሰላም ማስጠበቅ መቻሉንም ብርጋዴር ጄኔራል ማርዬ ገልጸዋል፡፡

ሰራዊቱ ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ውጤታማ ስራ እያከናወነ ነው፤ ለዚህ ደግሞ ደጀኑ ህዝባችን ምስክር ነው ብለዋል፡፡

Address

Ancharo

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ancharo News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share