የእመ ምሕረት ገዳም/ememihret monastry

የእመ ምሕረት ገዳም/ememihret monastry Addis Ababa, Ethiopia

16/10/2025

የእመቤታችን ምልጃዋ በረከቷ የልጇ ቸርነት ዐይለየን።
=========================
🟢🟡🔴
=========================
የዩቲዮብ ገፃችንን ይጎብኙ https://youtube.com/channel/UCYPbuN3s28rEZYxI4STtV2w

ሀገረ ስብከት የ5 ዓመት ሥልታዊ ዕቅድ በማዘጋጀትና  በየ3  ወሩ ሪፖርት በማድረግ የሚሰጠውን ግብረ መልስ በትክክል በመፈጸም በሥልታዊ ዕቅድ የሚመራ ብቸኛና ዓርአያ የሆነ ሀገረ ስብከት መሆ...
14/10/2025

ሀገረ ስብከት የ5 ዓመት ሥልታዊ ዕቅድ በማዘጋጀትና በየ3 ወሩ ሪፖርት በማድረግ የሚሰጠውን ግብረ መልስ በትክክል በመፈጸም በሥልታዊ ዕቅድ የሚመራ ብቸኛና ዓርአያ የሆነ ሀገረ ስብከት መሆኑ ተገለጸ።

ጥቅምት ፬ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም (አቡቀለምሲስ ሚዲያ ፤ ደብረ ብርሃን)
++++ +++++ +++++ ++++++ +++++ +++++

የሰሜን ሸዋ ደብረ ብርሃን ሀገረ ስብከት የ5 ዓመት ሥልታዊ ዕቅድ በማዘጋጀትና በየ3 ወሩ ሪፖርት በማድረግ የሚሰጠውን ግብረ መልስ በትክክል በመፈጸም በሥልታዊ ዕቅድ የሚመራ ብቸኛና ዓርአያ የሆነ ሀገረ ስብከት መሆኑ በ፵፬ኛው የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ሪፖርት ተገልጿል።

ይህ የተገጸለው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት በ፵፬ኛው የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ባቀረበው ሪፖርት ሲሆን ሀገረ ስብከቱ የሚሰጠውን ግብረ መልስ በትክክል በመፈጸም በሥልታዊ ዕቅድ የሚመራ ብቸኛና ዓርአያ መሆኑን ተገልጿል።

ሀገረ ስብከቱ በብዙ ፈተናዎች እያለፈ በ2018 በጀት ዓመት የተሰበሰበውን ከ36 ሚሊዮን 2 መቶ ሺህ ብር በላይ ገቢ የተደረገበትን የባንክ ስሊፕ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ ለቅዱስነታቸው አስረክበዋል።

መረጃው የአቡቀለምሲስ ሚድያ ነው

፵፬ ኛው የሰበካ ጉባኤ ዓለም አቀፍ መደበኛ ስብሰባ ተጀምሯል።ጥቅምት ፬/ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም እመ ምሕረት ሚዲያ =========================                     🟢🟡🔴...
14/10/2025

፵፬ ኛው የሰበካ ጉባኤ ዓለም አቀፍ መደበኛ ስብሰባ ተጀምሯል።
ጥቅምት ፬/ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም እመ ምሕረት ሚዲያ
=========================
🟢🟡🔴
=========================
የዩቲዮብ ገፃችንን ይጎብኙ https://youtube.com/channel/UCYPbuN3s28rEZYxI4STtV2w

11/10/2025
የደብረ ብርሃን ቅዱስ ባስልዮስ መንፈሳዊ ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም ለ2ኛ ዙር ለሚያሰለጥናቸው የመግቢያ ፈተና መስጠቱ ተገጸ።ጥቅምት ፩ ቀን ፳፻፲፰ዓ.ም (እመ ምሕረት ሚዲያ ) ===========...
11/10/2025

የደብረ ብርሃን ቅዱስ ባስልዮስ መንፈሳዊ ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም ለ2ኛ ዙር ለሚያሰለጥናቸው የመግቢያ ፈተና መስጠቱ ተገጸ።

ጥቅምት ፩ ቀን ፳፻፲፰ዓ.ም (እመ ምሕረት ሚዲያ )
=========================
🟢🟡🔴
========================
የደብረ ብርሃን ቅዱስ ባስልዮስ መንፈሳዊ ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም ለ2ኛ ዙር በቲኦሎጂ ዲፕሎማና በካህናት ልዩ ዲፕሎማ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ቀደም ሲል ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡

ኮሌጁ ለመዘገባቸው 2 መቶ 17 ተማሪዎች በመግቢያ ፈተና ለይቶ ትምህርት ለመስጠት ይቻል በነገረ መለኮት ዲፕሎማና በካህናት ልዩ ሴሚናሪ ዲፕሎማ ተማሪዎችን መዝግቧል።

ዛሬ ጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም በደብረ ብርሃን ከተማ ዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ ትምህርት ቤት ኮሌጁ የመግቢያ ፈተና መስጠቱን እና ውጤቱን እንደሚያሳውቅ የአቡ ቀለምሲስ ሚዲያ በፌስቡክ ገጹ ዘግቧል።
================
የዩቲዮብ ገፃችንን ይጎብኙ https://youtube.com/channel/UCYPbuN3s28rEZYxI4STtV2w

"ሃይማኖት በአፍ የሚነገር ብቻ ሳይሆን በልብ የሚታሰብ የምንቀበለው እውነታ ነው።" ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስመስከረም ፳፱/፳፻፲፰ ዓ/ም የእመ ምሕረት ሚዲያ =======================...
09/10/2025

"ሃይማኖት በአፍ የሚነገር ብቻ ሳይሆን በልብ የሚታሰብ የምንቀበለው እውነታ ነው።" ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ

መስከረም ፳፱/፳፻፲፰ ዓ/ም የእመ ምሕረት ሚዲያ =========================
🟢🟡🔴
=========================

የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ዓድዋ ሙዚየም ሕንጻ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሄዷል።

ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባ፣ ሀዲያና ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የቦርድ ሰብሳቢ "ሃይማኖት በአፍ የሚነገር ብቻ ሳይሆን በልብ የሚታሰብ የምንቀበለው እውነታ ነው።" በማለት የሃይማኖትን ከፍታ አንስተዋል።

ብፁዕነታቸው የሃይማኖትን ምንነት ከቃሉ የት መጣነት ጠቅሰው አብራርተዋል። አክለውም "ሃይማኖትን ከምግባር ጋራ አስተሳስረን ልንይዝ ያስፈልጋል።" ሲሉ ተግባራዊ ጉዳዮች ላይ ልንይዘው ያስፈልጋል ብለዋል።

ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ሓላፊ "ስለሰላም ለመስበክና ለማስተማር የሃይማኖት ተቋማትን የሚቀድመው የለም።" ብለዋል።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ "አሁን ያለንበት ወቅት ከበፊቱ የበለጠ ርብርብ፣ ትብብር ማድረግ አለብን።" ሲሉ ዋና ፀሐፊው አክለው ተናግረዋል።

በዕለቱ ለተለያዩ ተቋማት፣ የቀድሞ የጉባኤው አመራር አካላት፣ ለተባባሪ አካላት የዕውቅናና የምስጋና መርሐግብር የተደረገ ሲሆን፤ በ2017 የበጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት እቅድ ቀርቦ ውይይት እና ምክክር ተደርጓል።

በውይይቱ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባ፣ ሀዲያና ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የቦርድ ሰብሳቢ፣ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሐፊ መጋቤ ታምራት አበጋዝ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ዋና ፀሐፊ፣ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ፣ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር የጉባኤው አባላት አመራሮችን ጨምሮ ተወካዮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው የመንግሥት አመራር አካላት ተገኝተዋል ሲል የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ በፌስ ቡክ ገጹ ዘግቧል።
=============
የዩቲዮብ ገፃችንን ይጎብኙ https://youtube.com/channel/UCYPbuN3s28rEZYxI4STtV2w

09/10/2025

Address

Ankober

Telephone

+251970101010

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የእመ ምሕረት ገዳም/ememihret monastry posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share