Saro Media Network

Saro Media Network ወቅታዊ ፣ ታማኝ እና ሚዛናዊ መረጃ የሚያገኙበት ገጽ ነው ‼️

ከብትዎ መኖን ትታ (ፌሰታል) ናይሎን ስትበላ፡ እያንዳንዱ ገበሬ ማወቅ ያለበት ነገር===============================አንዳንድ ጊዜ ከብትዎ ወይም በግዎ ደካማ ሆኖ፣ ለመብላት ...
12/10/2025

ከብትዎ መኖን ትታ (ፌሰታል) ናይሎን ስትበላ፡ እያንዳንዱ ገበሬ ማወቅ ያለበት ነገር
===============================

አንዳንድ ጊዜ ከብትዎ ወይም በግዎ ደካማ ሆኖ፣ ለመብላት ወይም ለመራመድ ፍቃደኛ ሳይሆን፣ እንደ ሐውልት ቆሞ ሲያዩት ተጨንቀው ይሆናል 😩። ሆዷን ሲነኳት እንደ ከበሮ ደርቃለች። መኖ ሲሰጧት ትሸሻለች። ውሃ ሲያፈሱላት ያላየች መስላ ትቀራለች።

ወንድሜ፣ ይህ "የመንደር ሰዎች ጥቃት" አይደለም! ነገር ግን በአብዛኛው ጊዜ ምክንያቱ ናይሎን፣ ፕላስቲክ፣ ገመድ፣ ወይም ሌሎች የማይፈጩ ነገሮች በሩመን (የመጀመሪያው ሆድ) ውስጥ ተጣብቀው ስለሚገኙ ነው።
💊 ገበሬዎች ብዙውን ጊዜ መጀመሪያ የሚያደርጉት
በተለምዶ፣ አንቲባዮቲክስ፣ የህመም ማስታገሻዎች፣ ሩመን አነቃቂዎች፣ መርፌዎች፣ ፓራፊን ዘይት (paraffin oil) የመሳሰሉትን ሁሉ መሞከር እንጀምራለን፣ ሆኖም ምንም መሻሻል አይታይም። እንስሳው ደንዝዟል፣ አያመነዥግም (አያጎመጥምጥም)፣ እና ሆዱ እንደተለመደው ይቆያል።

“ይህስ ምን አይነት ጣጣ ነው?” ብለው መጠየቅ ይጀምራሉ። ከዚያም በትክክለኛ ምርመራ በኋላ ወይም አንዳንድ ጊዜ እንስሳው ከሞተ ወይም ከታረደ በኋላ፣ እውነቱን እናገኛለን—ሩመኑ በናይሎንና በፕላስቲክ ተሞልቷል! 😭
ምን ማድረግ አለብዎት (ማረድ ከማሰብዎ በፊት)
ቀድመው ካስተዋሉ፡

👉 በውስጥ ያለውን ነገር ለማለስለስ ፈሳሽ ፓራፊን፣ የአትክልት ዘይት፣ ወይም ሩመን አነቃቂዎች (እንደ ሩመን ቡስተር ወይም የሞላሰስ ውሃ) ይስጡ።

👉 የምግብ መፈጨትን ለመርዳት በቂ ድርቆሽ እና ውሃ ያቅርቡ።
👉 አንዳንድ ጊዜ ማዕድን እጥረት ስላለባቸው ቆሻሻ ስለሚበሉ የጨው ማዕድን ወይም የማዕድን ብሎክ ይስጡ።
አንዳንድ ጊዜ ይህ ቀደም ብሎ የተደረገ እርምጃ እንስሳውን ሙሉ በሙሉ ያድነዋል።
ሁኔታው አሳሳቢ ሲሆን
ከብትዎ ወይም በግዎ በጣም ከደከመ፣ ከነፋ፣ ወይም መራመድ ወይም መብላት ካልቻለ፣ ለሩመኖቶሚ ጊዜው ሊሆን ይችላል።
ይህ ትልቅ ቃል ምን ማለት ነው?

👉 ሩመኖቶሚ ማለት የእንስሳት ሐኪም ሩመኑን (የመጀመሪያውን ሆድ) ከፍቶ በውስጡ ያለውን ቆሻሻ ሁሉ ማለትም ናይሎኖች፣ ፕላስቲኮች፣ ገመዶች፣ የምግብ መፈጨትን የሚያግደውን ነገር ሁሉ ማውጣት ማለት ነው። እሱን እንደ “የናይሎን ማስወገድ ቀዶ ጥገና” አድርገው ያስቡ።

ከዚያ በኋላ እንስሳው እንደገና መብላት ይጀምራል፣ በደንብ ይራመዳል፣ እና ወደ መደበኛ ሁኔታው ይመለሳል።
እባክዎን፣ የታመሙ ከብቶችን ሁሉ ለማረድ አይጣደፉ!
አንዳንዶቹ በወቅቱ በሚደረግ እንክብካቤ እና ትንሽ ትዕግስት ሊድኑ ይችላሉ። ቶሎ ማረድ ገንዘብንም እምቅ ኃይልንም ማጣት ብቻ ነው።
ስለዚህ በሚቀጥለው ጊዜ እንስሳዎ ሲሚንቶ የዋጠ መስሎ ሲታይ፣ “እረዱት!” ብለው ብቻ አይጮኹ።

የእንስሳት ሐኪምዎን ይደውሉ፣ መጀመሪያ ለመርዳት ይሞክሩ ምክንያቱም ሕይወትንና ኪስዎን በተመሳሳይ ጊዜ ሊያድኑ ይችላሉ።

የጋሞ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ ክቡር አቶሃኪሜ አየለ በተገኙበት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በዞኑ ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ድጋፍ የተገነባን ቤት ለባለቤቶቹ ...
12/10/2025

የጋሞ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ ክቡር አቶሃኪሜ አየለ በተገኙበት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በዞኑ ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ድጋፍ የተገነባን ቤት ለባለቤቶቹ ርክክብ ተደረገ።

የ2017/18 በጀት ዓመት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአንድ ጀንበር የአቅመ ደካሞች አዲስ ቤት ግንባታ ንቅናቄን በቦረዳ ወረዳ ጎቾ አገልግሎት ዱባና ቡሎ ቀበሌ በመገኘት ባበሰሩበት ወቅት በዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ድጋፍ የሚገነባን ቤት የጋሞ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ ክቡር አቶ ሃኪሜ አየለ በተገኙበት ማስጀመራቸው ይታወሳል።

በዕለቱ ግንባታው የተጀመረው በቦረዳ ወረዳ ጎቾ አገልግሎት የዱባና ቡሎ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት የአቶ ታሪኩ እንጃ የአዲስ ቤት ግንባታ ሥራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ በዛሬው ዕለት የርክክብ መርሐ ግብር ተካሂዷል።

በርክክቡ ወቅት ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የጋሞ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ ክቡር አቶ ሃኪሜ አየለ እንዳሉት በጎነት የአቅመ ደካሞች ወገኖችንን ችግር ማቃለያ የመኖር ተስፋን የሚያለመልም የብልጽግና ፓርቲያችን ሰው ተኮር ዕሳቤ መገለጫ እና ባህል ያደረግነው የአንድነታችንና የአብሮነታችን ማሳያ የበረከታችን ምንጭ የሆነ ትልቅ ተግባር ነው ብለዋል።

በመሆኑም ይህን የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህል አጠናክረን የምንቀጥለው የማይቋረጥ ተግባራችን ነው ብለው ለቤቱ ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

የቦረዳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ አሸናፊ ሻሌ በበኩላቸ ይህ ክንውን ቃልን በተግባር የመፈፀም የብልጽግና ፓርቲ ዕሳቤን ትሩፋት በተግባር ተቋዳሽ የሆንበት ታሪካዊ ክዋኔ ነው ብለው የዞኑን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ባለድርሻ አካላትን አመስግነዋል።

የጋሞ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ክቡር አቶ ሃኪሜ አየለን ጨምሮ የፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊ ክቡር አቶ ገዛኸኝ ጋሞ ፣የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ ክቡር አቶ ተመስገን ኢዩኤል፣የጋሞ ዞን ህዝብ ምክር ቤት ማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣የጋሞ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ ሃላፊ ክብርት ሂሩት ማሞ፣የቦረዳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ አሸናፊ ሻሌ፣የወረዳው የመንግስት ዋና ተጠሪ ክቡር አቶ አባይነህ ባሳ እና ሌሎች ሥራ አስፈፃሚ አካላት፣የቀበሌው አመራር አካላት፣የሀገር ሽማግሌዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

"የእግዚአብሔር ቃል የነጠረ ነው፤ በእርሱ ለሚታመኑት ሁሉ ጋሻ ነው" ሳሙኤል ካልዕ 22:31
12/10/2025

"የእግዚአብሔር ቃል የነጠረ ነው፤ በእርሱ ለሚታመኑት ሁሉ ጋሻ ነው" ሳሙኤል ካልዕ 22:31



እናት እና ልጅ ❤እናቴ የዘጠኝ ወር ቤቴ ልጅነቴ ረጂም ዕድሜ ከሙሉ ጤና  ጋር  ይስጥልኝ ፈጣሪ ❤️❤️❤️
12/10/2025

እናት እና ልጅ ❤
እናቴ የዘጠኝ ወር ቤቴ ልጅነቴ ረጂም ዕድሜ ከሙሉ ጤና ጋር ይስጥልኝ ፈጣሪ ❤️❤️❤️

ይህ ኢትዮጵያዊ ወጣት ቲክቶከር ማን ይባላል ?
12/10/2025

ይህ ኢትዮጵያዊ ወጣት ቲክቶከር ማን ይባላል ?

12/10/2025

Saro Media Network
ለሁሉም ተከታዮች መልካም ሰንበት
እንድሆንላችሁ ይመኛል ።

እጅግ በጣም ደስ የሚል ዜና! 🎉በአቡዳቢ የሚገነባው የምስካየ ኅዙናን መድሃኔዓለም ወ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳምየተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስት ለታላቁ ገዳማችን የሰጠው የ17,682 ካሬ ...
12/10/2025

እጅግ በጣም ደስ የሚል ዜና! 🎉

በአቡዳቢ የሚገነባው የምስካየ ኅዙናን መድሃኔዓለም ወ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስት ለታላቁ ገዳማችን የሰጠው የ17,682 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ፣ እነሆ በአቡዳቢ የሚገኘው የምስካየ ኅዙናን መድሃኔዓለም ወ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም የአጥር ግንባታ ተፈቅዶለት ስራው ተጀምሯል!

ይህ ታላቅ ምዕራፍ እውን እንዲሆን ላደረገው ልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይግባው! 🙏

በመላው ዓለም የምትገኙ ኢትዮጵያውያን በጠቅላላ—እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!

ይህ ታሪካዊ ፕሮጀክት በመቅረጽ፣ አብሮነታችንን በማጠናከር እና የእምነት ቅርስ በመገንባት የበኩላችሁን እንድትወጡ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ሁሉም ሰው የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ የእግዚአብሔርን በረከት እንጠይቃለን

የገጠር ኮርደሪ 😍
11/10/2025

የገጠር ኮርደሪ 😍

11/10/2025

አርባምንጭ ላይ ያልተዘመረለት ጀግና ምትሉትን ሰው እስከ ስራው ? እንዲሁም ለሀገር ባለውለታ ሆኖ ህዝብ የማያውቀው?

ከዳውሮ ዞን ገሣ ከተማ ወደ ወላይታ ሶዶ ከተማ ስጓዝ የነበረው ተሸከርካሪ በተለምዶው ካረታ ወንዝ ተብሎ በሚጠራበት አካባቢ በተከሰተው የትራፊክ አደጋ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል በሎ...
11/10/2025

ከዳውሮ ዞን ገሣ ከተማ ወደ ወላይታ ሶዶ ከተማ ስጓዝ የነበረው ተሸከርካሪ በተለምዶው ካረታ ወንዝ ተብሎ በሚጠራበት አካባቢ በተከሰተው የትራፊክ አደጋ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል

በሎማ ቦሣ ወረዳ በተለምዶው ካረታ ወንዝ ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ ጠዋት 2:00 ሰዓት በተከሰተው የትራፊክ አደጋ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

ከዳውሮ ዞን ገሣ ከተማ ወደ ወላይታ ሶዶ ይጓዝ የነበረ ታርጋ ቁጥሩ ደ/ኢ 00377 የሆነው የህዝብ ማመላለሻ መኪና ተገልብጦ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የሎማ ቦሣ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የትራፊክ ደኅንነት አስተባባሪ ኢንስፔክተር ደረሰ ደበልቄ አስታውቋል።

በአደጋው ምንም እንኳ የሰው ህይወት ባይጠፋም በሰው አካልና በንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ስሆን የተጎዱትም በገሳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል።

የአደጋው መንስኤ ጥንቃቄ ጉድለት መሆኑን የጠቆሙት ኢንስፔክተር ደረሰ፣ አሽከርካሪዎች በጥንቃቄ ማሽከርከር እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል።

መረጃው የሎማ ቦሳ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ነው

እንደሀገር የተጀመረው የሌማት ትሩፋት ኢንሼቲቭ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ፦ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር)ወላላይታ ሶዶ፤ጥቅምት 1፣2018 የግብርና ሚኒስቴር የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር ተግባራት ተ...
11/10/2025

እንደሀገር የተጀመረው የሌማት ትሩፋት ኢንሼቲቭ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ፦ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር)

ወላላይታ ሶዶ፤ጥቅምት 1፣2018 የግብርና ሚኒስቴር የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ አለ።

ሀገር አቀፍ ሞዴል የእንስሳት አርቢዎች ቀን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ እየተከበረ ሲሆን በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር ስራዎችን ጎብኝተው፤ የእንስሳት መኖ ተከላ አስጀምረዋል።

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) በወቅቱ እንዳሉት፤ በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር መንግስት የጀመረውን ስራ በማጠናከር የወተት፣ እንቁላል እና ማር ፍላጎት ከማሟላት ባሻገር ህብረተሰቡን በኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ ነው።

መርሐ ግብሩ ዓላማውን እንዲያሳካ በተሰሩ ስራዎች ውጤት መገኘቱን ገልጸው፤ ለአብነትም በወላይታ ሶዶ ከተማ በእንስሳት ልማት የተመዘገበው ውጤት አመርቂ መሆኑን ተናግረዋል።

በተለይም በወተት ምርታማነት ላይ እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች መሆኑን ገልጸዋል።

የሌማት ትሩፋት የቤት ፍጆታን ከመቻል አልፎ ሌሎችን ለመደገፍ የሚያስችል ሁኔታ መፍጠር መጀመሩን ተናግረዋል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የአርብቶና አርሶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻል የተቀናጀ ተግባር እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል።

በመርሃ-ግብሩ የኢፌዴሪ ግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር)፣ በምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ማዕረግ የዲላ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረ/ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ እታገኝ ኃይለማርያምን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እየጎበኙ ይገኛሉ።

የልምድ ልውውጡ የኢፌዴሪ ግብርና ሚኒስቴር ከክልሉ ግብርና ቢሮ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ስለመሆኑ ተጠቁሟል።

እኒህ ኢትዮጵያዊ ማህበራዊ አንቂ ማን ይባላሉ ??
11/10/2025

እኒህ ኢትዮጵያዊ ማህበራዊ አንቂ ማን ይባላሉ ??

Address

Saro Media Network
Arba Minch'

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Saro Media Network posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Saro Media Network:

Share