Tamirat

11/06/2026
JVC
11/06/2026

JVC

23/05/2026

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከ17አመት በታች

አርሰናል በቻምፒየንስ ሊግ ስፖርቲንግ ሲፒን ባሸነፈበት ወቅት 26ኛውን የውድድር ዘመን የንፁህ ጎል ማስቆጠር ችሏል 🧱የማይክል አርቴታ ወንዶች በአውሮፓ አምስት ከፍተኛ ሊጎች ውስጥ እጅግ በጣ...
08/04/2026

አርሰናል በቻምፒየንስ ሊግ ስፖርቲንግ ሲፒን ባሸነፈበት ወቅት 26ኛውን የውድድር ዘመን የንፁህ ጎል ማስቆጠር ችሏል 🧱

የማይክል አርቴታ ወንዶች በአውሮፓ አምስት ከፍተኛ ሊጎች ውስጥ እጅግ በጣም ጥሩ የሆነ የመከላከያ ሪከርድ አላቸው 👏

መልካም ልደት በሉት  እነ ብያለሁኝhappy birthday 🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎉🎉🎉🎉🎉🎉👨‍🍼👨‍🍼👨‍🍼👨‍🍼👨‍🍼👩‍🍼👩‍🍼👩‍🍼👩‍🍼birthday 😃😃...
30/03/2026

መልካም ልደት በሉት እነ ብያለሁኝ
happy birthday 🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎉🎉🎉🎉🎉🎉👨‍🍼👨‍🍼👨‍🍼👨‍🍼👨‍🍼👩‍🍼👩‍🍼👩‍🍼👩‍🍼birthday 😃😃😃😃😃🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈Happy birthday Mirakel Tamrat

ለ73 ዓመታት በመቃብር ቆፋሪነት ያገለገሉት አሜሪካዊ ጡረታ ወጡ። ። ። ። ። ። ። ። ።በዓለም ላይ ረጅሙን ጊዜ በመቃብር ቆፋሪነት ያገለገሉት ግለሰብ፣ ከ73 ዓመታት በላይ አገልግሎት በኋ...
22/03/2026

ለ73 ዓመታት በመቃብር ቆፋሪነት ያገለገሉት አሜሪካዊ ጡረታ ወጡ

። ። ። ። ። ። ። ። ።
በዓለም ላይ ረጅሙን ጊዜ በመቃብር ቆፋሪነት ያገለገሉት ግለሰብ፣ ከ73 ዓመታት በላይ አገልግሎት በኋላ በመጨረሻ በጡረታ ተሰናብተዋል።

እ.ኤ.አ. በ2021፣ ለ68 ዓመታት ከ191 ቀናት በመስራት "ረጅሙን መቃብር ቆፋሪነት የሥራ ዘመን" የሚል ማዕረግ ያገኙት አለን ማክክሎስኪ የተባሉት እኝህ አሜሪካዊ አሁን በ92 ዓመታቸው፣ ክብረ ወሰናቸውን ወደ 73 ዓመታት ከ75 ቀናት ካራዘሙ በኋላ ስራቸውን አቁመዋል።

አለን በወቅቱ በሚሰሩበት ከተማ ጋልቭስቶን ውስጥ ትልቅ መነጋገሪያ ሆነው ነበር። በዜናዎች ላይ ጭምር የቀረቡ ሲሆን፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ሰዎችን መርዳት የሚወዱ ልዩ ሰው መሆናቸውን መስክረዋል።

የሶስት ልጆች አባት የሆኑት አለን ስራቸውን የጀመሩት እ.ኤ.አ. በ1952 አንድ መቃብር ቆፋሪ ለአንድ ሳምንት እሱን ተክተው እንዲሰሩለት ከጠየቃቸው በኋላ በእጃቸው መቃብር በመቆፈር ነበር።

ውድ ባለቤታቸውን በሞት ሲያጡም መቃብሯን የቆፈሩት ራሳቸው ነበሩ። ለምን እንደዛ እንዳደረጉ ሲናገሩም "እኔ እንድቆፍርላት የምትፈልግ ይመስለኛል" ሲሉ መልሰዋል።

ልጃቸው ዲን ስለአባቱ ሲናገር ቤተሰቡ በአባቱ ስራ እንደሚኮራ ገልጾ የሚከተለውን ብሏል ፦ "እኛ እንደ ቤተሰብ ስራውን ለማቆም በመወሰኑ እና በራሱ ምርጫ በመልቀቁ በጣም ደስተኞች ነን። ከእንግዲህ በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ወይም በከፍተኛ ሙቀት ውስጥ በመቆፈር ጤንነቱ ይጎዳል ብለን አንሰጋም። ነገር ግን ይህ ስራ ከ1952 ጀምሮ የህይወቱ ትልቅ አካል እንደነበረ እንረዳለን። ስራው ለቤታችን ምግብ፣ ለሰውነታችን ልብስ እና ለራሳችን መጠለያ ሆኖናል።"

ዘገባው የጊነስ ወርልድ ሪከርድስ ነው።

 : የአሜሪካ እና የእስራኤል ጦር በደቡብ ምዕራብ ኢራን በሚገኝ የአየር ኃይል ጦር ሰፈር ላይ የአየር ድብደባ ፈጸሙ!የአሜሪካ እና የእስራኤል ኃይሎች በርካታ የተቀናጀ የአየር ድብደባ በኢራን...
21/03/2026

: የአሜሪካ እና የእስራኤል ጦር በደቡብ ምዕራብ ኢራን በሚገኝ የአየር ኃይል ጦር ሰፈር ላይ የአየር ድብደባ ፈጸሙ!

የአሜሪካ እና የእስራኤል ኃይሎች በርካታ የተቀናጀ የአየር ድብደባ በኢራን የጦር መሣሪያ ማከማቻዎች ላይ ፈጽመዋል። ጥቃቱ ያነጣጠረው በኩዜስታን ግዛት በዴዝፉል በሚገኘው ቫህዳቲ (Vahdati) በተሰኘው የኢራን አየር ኃይል የጦር ሰፈር ላይ ነው።

የጦር ሰፈሩ በደቡብ ምዕራብ ኢራን፣ ከኢራቅ ድንበር አቅራቢያ እና ለፋርስ ባህረ ሰላጤ ቅርብ በሆነ እጅግ ስትራቴጂካዊ ቦታ ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ አካባቢው ለቀጣናዊ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ቁልፍ ኮሪደር ነው።

ድብደባው የኢራንን የጦር መሣሪያ ክምችት ለማውደም እና በዚያ አካባቢ ያለውን ወታደራዊ የመንቀሳቀስ አቅም ለመቀነስ ያለመ እንደሆነ ተዘግቧል።

በአፋር ክልል በደረሰ ከባድ የንፋስና የዝናብ አደጋ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ።​በአፋር ክልል ፋንቲ ረሱ ዞን ጎሊና ወረዳ ትላንት ማምሻውን በጣለ ከባድ ዝናብና ንፋስ ከፍተኛ የንብረት ውድመት ደር...
21/03/2026

በአፋር ክልል በደረሰ ከባድ የንፋስና የዝናብ አደጋ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ።

​በአፋር ክልል ፋንቲ ረሱ ዞን ጎሊና ወረዳ ትላንት ማምሻውን በጣለ ከባድ ዝናብና ንፋስ ከፍተኛ የንብረት ውድመት ደርሷል።

​በደረሰው አደጋ በግል መኖሪያ ቤቶችና በመንግስት የልማት ተቋማት ህንፃዎች ላይ ውድመት ደርሷል። በእንስሳት፣ በእርሻ ቦታዎችና በተለያዩ የልማት ተቋማት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ተመዝግቧል።

​የጎሊና ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት እንደገለጸው፤ በአደጋው ከፍተኛ የንብረት ጉዳት ቢደርስም እስካሁን ባለው መረጃ በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።

Address

Arba Minch'

Telephone

+251919724775

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tamirat posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share