Visit Arba Minch

Visit Arba Minch Media/News Company

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የሚከተሉትን አመራሮች በሚኒስትር ዴዔታነት ሾመዋል
10/10/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የሚከተሉትን አመራሮች በሚኒስትር ዴዔታነት ሾመዋል

የኢፌዴሪ 7ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ1ኛ ልዩ ስብሰባው በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ እየተወያየ ነው--------------------(ዜና ፓርላማ) መስከረም 27 ፣ 2019 ዓ.ም፤ አዲስ...
07/10/2026

የኢፌዴሪ 7ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ1ኛ ልዩ ስብሰባው በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ እየተወያየ ነው
--------------------
(ዜና ፓርላማ) መስከረም 27 ፣ 2019 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ 7ው የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 1ኛ ልዩ ስብሰባው በፌደራል መንግስት አስፈጻሚ አካላት ስያሜ፣ አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ እየመከረ ይገኛል።

የምክር ቤት አባልና የመንግሥት ተወካይ የተከበሩ አቶ ፍቃዱ ተሰማ በረቂቅ አዋጁ አስፈላጊነት ላይ አጭር ማብራሪያ አቅርበዋል።

በቀረበው ማብራሪያም ከዚህ በፊት በነበሩት 22 አስፈፃሚ አካላት ላይ የቁጥር ልዩነት እንደሌለና ከቁጥር አንፃር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በነበሩበት 22 ሆነው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።

ይህም ሆኖ በሁለት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ላይ ብቻ የስያሜ ለውጥ መደረጉንና ሁለት ሚኒስቴሮች አንደ አዲስ መቋቋማቸው ተብራርቷል።

እንደ አዲስ የተቋቋሙት ሁለት ሚኒስቴር መ/ቤቶች ቀድሞ "የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር" የነበረው በአዲሱ "የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር" በሚል እና ቀድሞ "የቱሪዝም ሚኒስቴር" የነበረው በአዲሱ "የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር" በሚል መቋቋማቸው ተጠቁሟል።

በተጨማሪም ቀድሞ "የፕላንና ልማት ሚኒስቴር" የነበረው "የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስቴር" በሚል እና ቀድሞ "የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር" የነበረው "የሎጂስቲክስ ሚኒስቴር" በሚል ስያሜያቸው መቀየሩ ተገልጿል።

በሚኒስቴር መ/ቤቶቹ ላይ ማሻሻያው ያስፈለገበት ምክንያት ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ እና ከተልዕኳቸው ጋር ለማጣጣም መሆኑም ተብራርቷል።

በረቂቅ አዋጁ ላይ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ክብርት ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ለምክር ቤቱ ሰፋ ያለ ማብራሪያ እያቀረቡ ይገኛሉ።

እንደ አዲስ በተቋቋሙት ሁለቱ ሚኒስቴር መ/ቤቶችም ሆነ የስያሜ ለውጥ በተደረገባቸው ሁለቱ ሚኒስቴር መ/ቤቶች ዙሪያ በቀጣይ ሰፋ ያለ ትንታኔ ይዘን የምንቀርብ ይሆናል።

07/10/2026

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Yared Endrias Alange Churi, Fasika Kaleb, ሰንታዩሁ ዉርቁ ካሣ, Asnake Asefa, Adime Abrham, Mahari Mahari, Tinbite Shanko, Debebe Abiyo, Ayiru Unko

በፌዴሬሽን ምክርቤት ታሪክ የነበሩ አፈጉባኤዎችአልማዝ መቆ (1987–1993 ዓ.ም)በኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት መሠረት የመጀመሪያዋ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ያገለገሉ ናት።ዶ/ር ሙላ...
06/10/2026

በፌዴሬሽን ምክርቤት ታሪክ የነበሩ አፈጉባኤዎች

አልማዝ መቆ (1987–1993 ዓ.ም)

በኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት መሠረት የመጀመሪያዋ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ያገለገሉ ናት።

ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ (1994–1997 ዓ.ም)

የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ከመሆናቸውም በላይ በኋላ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት (2006–2011 ዓ.ም) ሆነው ያገለገሉ ታዋቂ ዲፕሎማትና ፖለቲከኛ ናቸው።

ደገፌ ቡላ (1997–2002 ዓ.ም)

ከ1997 እስከ 2002 ዓ.ም የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ሆነው አገልግለዋል።

ካሳ ተክለብርሃን (2003–2008 ዓ.ም)

የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ከመሆናቸውም በላይ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር እና በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል።

ያለው አባተ (2008–2010 ዓ.ም)

የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የነበሩ ሲሆን፣ ከ2008 እስከ 2010 ዓ.ም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ሰርተዋል።

ኬሪያ ኢብራሂም (2010–2012 ዓ.ም)

በሰኔ 2012 ዓ.ም በሀገሪቱ በነበረው የፖለቲካ ውጥረትና በምርጫ መራዘም ምክንያት ከኃላፊነታቸው እስከለቀቁበት ጊዜ ድረስ አፈ ጉባኤ ነበሩ።

አደም ፋራህ (2012–2014 ዓ.ም)

ኬሪያ ኢብራሂምን ተክተው አፈ ጉባኤ ሆነው የሰሩ ሲሆን፣ በኋላም የብልፅግና ፓርቲ ዋና ሥራ አስፈጻሚና የፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ተሾመዋል።

አገኘሁ ተሸገር (2014–2019 ዓ.ም)

የቀድሞ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሲሆኑ፣ ከመስከረም 2014 ዓ.ም እስከ መስከረም 2019 ዓ.ም ድረስ አፈ ጉባኤ ሆነው አገልግለዋል።

ሙፈሪሃት ካሚል (ከመስከረም 2019 ዓ.ም ጀምሮ)

የቀድሞ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ፣ የሰላም ሚኒስትር እና የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የነበሩ ሲሆን፣ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም የምክር ቤቱ አዲስ አፈ ጉባኤ ሆነው ተመርጠዋል።

የክልል ምክር ቤቶች የምስረታ ጉባኤዎች አድርገው የክልል ርዕሰ መስተዳድሮችንና የከተማ ከንቲባዎችን ሰይመዋል። በዚህም መሰረት 1. የማ/ኢትዮጵያ ክልል 👉 ዶ/ር የትምጌታ አስራት2. የሀረሪ ...
06/10/2026

የክልል ምክር ቤቶች የምስረታ ጉባኤዎች አድርገው የክልል ርዕሰ መስተዳድሮችንና የከተማ ከንቲባዎችን ሰይመዋል። በዚህም መሰረት

1. የማ/ኢትዮጵያ ክልል 👉 ዶ/ር የትምጌታ አስራት
2. የሀረሪ ክልል 👉 አቶ ኦርዲን በድሪ
3. የጋምቤላ ክልል 👉 ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ
4. የሲዳማ ክልል 👉 ዶ/ር መሳይ ሀይሉ
5. የሶማሊ ክልል 👉 አቶ ሙስጠፌ መሀመድ
6. የአ/አ ከተማ አስተዳደር 👉 ወይዘሮ አዳነች አቤቤ
7. የአማራ ክልል 👉 አቶ አረጋ ከበደ
8. የአፋር ክልል 👉 ሐጂ አወል አርባ
9. የኦሮሚያ ክልል 👉 አቶ ሽመልስ አብዲሳ
10. የደ/ኢትዮጵያ ክልል 👉 ዶ/ር ተስፋዬ በልጂጌ
11. የደ/ምዕ/ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል👉 አቶ ፍቅሬ አማን
12. የድ/ከተማ አስተዳደር 👉 አቶ አብዱላሂ አደን
13. የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 👉 አቶ አሻድሊ ሃሰን
በመሰየም በየምክር ቤቶቻቸው ቃለ መሐላ ፈፅመዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አዲሱ ካቢኔ ይፋ የሆነ ሲሆን የክልሉ ምክር ቤት አዳዲስ የቢሮ ኃላፊዎችን ሾመ።​የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆኖ በቅርቡ የተሾመው ዶ/ር ተስፋዬ በልጅጌ ...
02/10/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አዲሱ ካቢኔ ይፋ የሆነ ሲሆን የክልሉ ምክር ቤት አዳዲስ የቢሮ ኃላፊዎችን ሾመ።

​የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆኖ በቅርቡ የተሾመው ዶ/ር ተስፋዬ በልጅጌ የቀረቡላቸውን አዳዲስ የካቢኔ አባላት ለክልሉ ምክር ቤት ያቀረቡ ሲሆን ምክር ቤቱም በዛሬው ዕለት ባካሄደው ስብሰባ አዳዲሶቹን የቢሮ ኃላፊዎችና የርዕሰ መስተዳድር ተጠሪዎችን በሙሉ ድምፅ አጽድቆ ሾሟል።

​በዚህ መሠረት አዲሱ የክልሉ አስተዳደር ምክር ቤት (ካቢኔ) አባላት ዝርዝር ከዚህ በታች ተዘርዝሯል፦

​1. ዶ/ር ደሚስ አድማሱ – ም/ር/መስተዳድር እና የሥራ እና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ (ጋሞ)
​2. ኢ/ር ወንድሙ ሴታ – በም/ር/መ ማዕረግ የከተማና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ (ዎላይታ)
​3. አቶ ንጋቱ ዳንሳ – በም/ር/መስተዳድር ማዕረግ የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ (ማሌ)
​4. ዶ/ር ከርታ ካስኬ – የግብርና ቢሮ ኃላፊ (ጋሞ)
​5. አቶ ዳዊት ደሳለኝ – የጤና ቢሮ ኃላፊ (ዎላይታ)

​6. ወ/ሮ ወይኒቱ መልኩ – የባህል እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ (ባስኬቶ)
​7. ዶ/ር መስፍን መንዛ – የትምህርት ቢሮ ኃላፊ (ጋሞ)
​8. አቶ ኃ/ማሪያም ተስፋዬ – ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ (ጌዴኦ)
​9. አቶ ብረሃኑ ዘውዴ – ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር (ጋሞ)
​10. አቶ ተፈሪ አባተ – መሬት ሀብት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ (ጎፋ)

​11. አቶ ታደለ – ንግድ እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ (ዎላይታ)
​12. ዶ/ር ዝናቡ ዎልዴ – ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ (ጌዴኦ)
​13. አቶ መንግስቱ በየነ – ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ (ኮሬ)
​14. ኤከል ኔቱም – መስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ቢሮ ኃላፊ (ደ/ኦሞ)
​15. አለምነሽ ደመቀ – ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ (ጋሞ)

​16. አቶ ሙሉቀን ታደሰ – ፍትህ ቢሮ ኃላፊ (ወላይታ)
​17. ኢ/ር ፍሬዘር ኮርባይዶ – ውሃ እና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ (ኮንሶ)
​18. አቤኔዘር ታፈሰ – ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ (አሪ)
​19. አቶ ተወልደ ተስፋዬ – ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ (ጌዴኦ)
​20. ዶ/ር አልማዝ ባልታ – ፕላን ልማት ቢሮ ኃላፊ (ወላይታ)
​21. ዶ/ር ሰለሞን ቡኬ – ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር (ቡርጂ)
​22. አቶ ወንድማገኝ ደግፌ – ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ (ጋረዱላ/ደራሼ)

በሌላ በኩል በርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) አቅራቢነት ዶ/ር አበባየሁ ታደሰ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ በመሆን ተሰይመዋል።

ዶ/ር ቦጋለ ቦሼ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል።

ምክርቤቱ ወ/ሮ ካሰች ኤልያስን የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ አድርጎ ሾሟል።

ንቁ የሕዝብ አገልጋዮች የሆኑ የአርባምንጭ ተወላጆች ❤
29/09/2026

ንቁ የሕዝብ አገልጋዮች የሆኑ የአርባምንጭ ተወላጆች ❤

ጨፌ ኦሮሚያ አቶ  ሽመልስ አብዲሳን የኦሮሚያ ክልል  ፕሬዝዳንት አድርጎ  ሾመጨፌ ኦሮሚያ የ7ኛው የጨፌ የሥራ ዘመን 1ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባዔ በመካሄድ ላይ ይገኛል። በዚህም ጨፌ ኦሮሚያ...
28/09/2026

ጨፌ ኦሮሚያ አቶ ሽመልስ አብዲሳን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾመ

ጨፌ ኦሮሚያ የ7ኛው የጨፌ የሥራ ዘመን 1ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባዔ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በዚህም ጨፌ ኦሮሚያ አቶ ሽመልስ አብዲሳን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾሟል።

Address

Gamo Zone
Arba Minch'
76115698

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Visit Arba Minch posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share