DebubTimes ደቡብ ታይምስ

DebubTimes ደቡብ ታይምስ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from DebubTimes ደቡብ ታይምስ, አርባ ምንጭ ደቡብ ኢትዮጵያ, Arba Minch'.

😲😳😳😳
28/09/2025

😲😳😳😳

27/09/2025
26/09/2025

እንኳን ለመስቀል በዓል አደረሳችሁ

የመስቀል በዓል ሲታሰብ እውነት ተቀብራ እንደማትቀር እናስባለን። መስቀሉ የተቀበረበት ቦታ ተራራ ሠርቶ ነበር። የቀበሩት ሰዎች ከዚህ በኋላ እንደማይወጣ ደምድመው ነበር። አንዳንድ አማኞችም ተስፋ ቆርጠው ነበር ። ጊዜው በረዘመ ቁጥር ቀባሪዎቹ ያሸነፉ መስሏቸው ተደሰቱ። የተቀበረው መስቀልም ታሪክ የሆነ መሰለ።

ብርቱ ሰዎች፣ እውነት ፈላጊ ሰዎች፣ አቧራውን የሚገልጡ፣ ቆሻሻውን የሚያነሡ ሰዎች፣ ሲመጡ ግን መስቀሉ ከተቀበረበት ወጣ።
እውነት አይቀበርም። ጊዜው ሲደርስ አቧራውን አንሥቶ ዐሻራውን ያሳያል። ሐሰቱን እንደ ጉም አትንኖ፣ ሐቁን እንደ ዐለት አግንኖ ያሳያል።
የኢትዮጵያም እውነት እንደዚሁ ነው። የአውራ ዶሮዎች ጩኸት የፀሐይን መውጣት አያስቀረውም። የሌሊት ወፎች ክንፍ የፀሐይን ንጋት አያግደውም። በዚህም ተባለ በዚያ ፀሐይ ትወጣለች።

የኢትዮጵያ እውነት እንደ መስቀሉ ሁሉ አቧራውን ጥሶ፣ አፈሩን አፍልሶ፣ ቆሻሻውን ደርምሶ ይገለጣል። የወጓት ያዩዋታል። ከላይ ሆነው እንዳዩዋት ሁሉ፣ ከታች ሆነው ይገረሙባታል።
በመደመር ደመራ እየተመራን፣ በትጋት እየቆፈርን፣ የኢትዮጵያን ብልጽግና እናወጣዋለን። ይህ ዓመት የኢትዮጵያ ብርሃን ሲወጣ የምናይበት ይሆናል።በድጋሚ መልካም የደመራና የመስቀል በዓል ይሁንልን።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ.ም

25/09/2025
25/09/2025
25/09/2025

በግብፅ እና በኢትዮጵያ ወታደሮች መካከል በመቶዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች ርቀት መኖሩን የገለፁት ፕሬዝዳንቱ "ግብፅ ኢትዮጵያን ለመረበሽ የምትፈልግበት ምክንያት አይታየኝም። ኢትዮጵያም በሶማሊያ የሚገኙ የግብፅ ሰላም አስከባሪ ኃይልን ለመረበሽ የምትፈልግበት ምክንያት አይታየኝም" ብለዋል
👉🏾 https://www.youtube.com/shorts/Hx59xfdI4aM

24/09/2025
23/09/2025

አሰፋ ጫቦ

ከዕዝራ እጅጉ-(ተወዳጅ ሚድያ)

| ተወዳጅ ሚድያና ኰሚኒኬሽን ለሀገር የሠሩ ሰዎችን የህይወት ታሪክ እየሰነደ ለትውልድ በማስቀመጥ ላይ ይገኛል።ከእነዚህም የሀገር ባለውለታዎች አንዱ አቶ አሰፋ ጫቦ ነበሩ።

አቶ አሰፋ ጫቦ ከአባቱ ከጫቦ ሣዴ ሃማ ያሬና ከእናቱ ከማቱኬ አጀን ከተራራ አናት ላይ ከሚገኝ ሜዳማ ቦታ ላይ ጨንቻ ከተማ ነው የተወለደው፡፡ከጋሞ ሰንሰለት ተራራዋች አንዱ ጫፍ ላይ የሚገኝ ጠረጴዛ ነው ይላታል ጨንቻን ሲገልጣት ከ2-6ኛ ክፍል እዚያው ጨንቻ የተማረ ሲሆን በዘጠኝ ዓመቱ የጨንቻ ገብርዔል ዲያቆን በመሆንም አገልግሏል።

በድቁናው ባገኘው ካፒታልም ጥቂት የዶሮና የበግ ግልገል ገዝቶበታል። ሐሙስ ሐሙስን እየጠበቀ ኤዞ ገበያ ዶሮና እንቁላል አየነገደ ይውል ነበር። ከእነሱም ውስጥ ት/ቤት ድረስ እየተከተሉ ያስቸግሩት የዶሮና የበግ ግልገልም ነበረው። እንደፈረንጆቹ pet መሆናቸው ነው፡፡

የ8ኛ ክፍል ትምህርቱን በሻሸመኔ በኋላ ታሪኩን ሲያውቅ ስሙን ካላስቀየርኩ ብሎ ከታገለበት ከአጼ ናኦድ ት/ቤት ከ39 ተማሪዎች አንዱ በመሆን ነበር የተከታተለው።

የተዋቀረበትን ዋልታና ካስማ ያየበት ቆይታው በጋሞ ውስጥ ካሉ 40 ከሚሆኑ ‹ካዎ›ች አንዱ በሆኑት በዘመዱ በቀኛዝማች ኢሌታሞ ኢቻ ቤት በኖረበት ወቅት ነበር፡፡

ሲገልጻቸውም ‹በኢሌታሞና በሰዋች መሀከል የግንኙነት አጥር የለም፡፡ ወግ ሳያበዙ ለሕዝብ አሳቢና ተቆርቋሪ ናቸው ነው› የሚላቸው የጋሞ ካዎ የሚፈራ ሳይሆን የሚከበር ነው ይለናል፡፡ ገና በልጅነቱ ለሕዝብ በመስራት እርካታ ማግኘት እንደሚቻልም የተገነዘበው በጉሌታ-አንዱሮ ግብር ተቀባይ ተደርጎ በቀኛዝማች ኤሌታሞ ሲመደብ ነው፡፡

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ከአዲስ አበባ ከኮከበ ጽባህ አቋርጦ ሲቪል አቪዬሺን ተቀጥሮ ባህር ዳር ሄደ፡፡ ‹ሀ› ብሎ የመጀመሪያውን ስራውንና የመጀመሪያ ልጁንም ያገኘው ጎጃም ነበር፡፡ ‹ጎጃሜ ተነቀለ› ብሎ ፖሊስና እርምጃው ላይ ጽፎ ጠፍቶ እስከወጣ ድረስ እዚው ነበር፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሕግ ት/ቤት LLB አግኝቶ የተመረቀ ሲሆን በዓለም አቀፍ የህግ ተማሪዋች ውድድር ከውጭ የምስክር ወረቀት ከንጉሱም የወርቅ ኦሜጋ ሰዓት ተሸልሟል፡፡

በ 1960 የሕግ ተማሪ ሆኖ በአፍሪካ አዳራሽ የቀድሞ ተማሪዎች ማህበር ስብሰባ ላይ ከመጮህ ጀምሮ ይህው እስከእልፈተ ሞቱ ድረስ ለአገርና ለወገን ዋይታውን አላቋረጠም ነበር ፡፡ በአጠቃላይ የአጥቢያ ፍ/ቤት ጸሐፊ፤ የበጅሮንድ ጽ/ቤት ተላላኪና ጸሐፊ የአየር መርማሪ (metrology) የሕግ አማካሪ ሆኖ ሰርቷል፡፡

በፖለቲካው መስክ ከተማሪዎች ንቅናቄ ባሻገር የሁለት ድርጅቶች መስራችና መሪ ሲሆን ከ 1966-1967 የልጅ እንዳልካቸው አዲሱ ካቢኔና የደርግ አውራጃ አስተዳዳሪ ሆኖ ጋርዱላ ሄዶ ነበር፡፡ በጄኔራል መብራቱ ፍስሃ ታስሮ እስከተባረረ ድረስ የፖለቲካ ድርጅት መስራችና መሪ፤ የአውራጃ አስተዳዳሪ የመንግሰትና የባለስልጣን አማካሪ፤ የሕዝብ ተከራካሪ በመሆን በለውጡ ውስጥ ሰርቷል፡ ፡

በኋላም በራሱ ከግቢ የመራቅ ጥያቄ አነሳሽነት ‹‹በችሎታው መጠን ሥራ ይሰጠው›› የሚለውን ሻምበል ፍቅረስላሴ ወግደረስ የፈረመበትን ደብዳቤ ይዞ መገናኛ ሚኒስቴር ወረደ፡፡ ከዚያ ነው እንግዲህ በየካቲት 1971 ዓ.ም መጀመሪያ ወደ ደርግ ጽ/ቤት ታፍኖ ተወስዶ ከዚያም በማዕከላዊ ታስሮ ከ 10 ዓመት ከ 6 ወራት ከ 6 ቀናት በኃላ የተፈታው፤ ማዕከላዊ እስር ቤት የሰው ገበያ ነበር ብሎ ሲገልፀው በ10 ዓመት የእስር ዘመኔ ውስጥ ከ100.000ሺ በላይ ሰው አይቼበታለው ይለናል ካያቸውም ውስጥ በባህርይ፣ በቁመና፣በአለባበስና በስነምግባራቸው ጥሩ አድርጎ በመጽሐፉ ውስጥ ይገልጻቸዋል፡፡

እንደተፈታም የአስኮ ጫማ ሱቅ የነበረበት ፎቅ ላይ የጥብቅናና የንግድ አማካሪ ቢሮ በመክፈት ሙግቱን አስረዝሞ ገንዘብና ጊዜ ከማባከን ይልቅ አስቀድሞ በድርድርና ከፍ/ቤት ውጭ ለመጨረስ ያደረገው ጥረትም ከዚሁ ከራሱ ማንነት የመነጨ ነው፡፡ በሽግግር መንግስቱ የምክር ቤት አባል በመሆንም በ 1983 አርባ ምንጭ ሄዶ ነበር። ሁሉም አልሆን ሲለው ያለውዴታ በግድ አሜሪካ በስደተኝነት መጥቶ መኖሩን ጀመረ፡፡

በተፈጥሮው ሰው መጥላት የማይፈልገው አንጋፋው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፣ ቀጥተኛው፣ ብዕረኛው አቶ አሰፋ ጫቦ የ 73 ዓመት ባለዕድሜው የአራት ልጆች አባትና የዘጠኝ ልጆች አያት ነበር ፡፡

‹የትዝታ ፈለግ› በሚል ርዕስ ለንባብ ያበቃውን መጽሐፉን በምናነብበት ወቅት ብዙ ወደማናቃቸው ጊዜያትና ግለሰቦች ከመውሰዱም ሌላ የአጻጻፍ ውበቱ እጅግ ያስደንቃል የባህሪይ አቀራረፅ ችሎታውና የአካባቢ ስዕላዊ መግለጫው ያረካል ‹‹ነፍጠኛ›› ማለት አማራ ብቻ ነው ማለት እምነት እንጂ እውነት አንዳልሆነና ‹‹ነፍጠኛ›› በሚል የሚበጠብጠንን ጥያቄ ለመመለስ ናችሁ የተባልነውን ሳይሆን ውስጣችን ገብተን ሆነን ያለነውን እንድናስተውል ይጎተጉተናል፡፡

ዋታካዳ እንደሚጠሩት ‹‹ጋንታይናው›› ‹ጋትዬ› አሰፋ ጫቦ ዛሬ አብዛኛው እየፈራ እየሸሸ ምክንያቱን በሚደረደርበት ወቅት እሱ ምን አቅብጦኝ ከደርግ ጋር ገጠምኩ; ብሎ አያውቅም አምኖ እንጂ ምናምን ፍለጋ ወይም ሰው ገፍቶት እንዳልገባ በግልጽ አስቀምጦልናል እንዲያውም ‹በመሸ በጠባ ቁጥር በጥሼ የምቀጥለው ማተብ› የለኝም ይል ነበር ።

በንባብ የዳበረ የበሰለ መሆኑን ከማሳየቱም ሌላ ስለ አሜሪካ መምጣትና መኖር ያካፈለው ምክር በቀላሉ የሚታይ አይደልም ስለስደቱ ዓለም ችግርና ውጥንቅጥ ሲጽፍም ስደተኛው በሃብት ድህነትና በአእምሮ ድህነት መሃከል ያለው ልዩነት የጠፋበት መምሰሉን ፍንትው አድርጎ አቅርቧል። በአጠቃላይ ጆሮ ጠገብነት ማወቅን አለመተካቱን ያሳውቀናል
ጀግና ፍለጋ ጦር ሜዳ መሪዋች አምባ የፖለቲካ ሰዋች አምባ እንሄዳለን፡፡

ሲገኝ አገር ያውቀዋል ፀሐይ ይሞቀዋል ያልታወቁ በየቤቱ የታጨቁ ተራሰው የሆኑ ያልተሰጣቸውን በመፈጸም የጀግኑ አሉ ይላል ጋሞ ይላል ፤ ጋሞ ግብር ገበረ እንጂ ሥርዓቱን አልገበረም በማለት ጥፋቱን ስህተቱን በማመን መቀበልና ባደባባይ ይቅርታ መጠየቅ የጋሞነት ገላጭ አብሮ የተወለደ የውሰጥ ባህርይ መሆኑን በመተንተን ለየት ስላለው የአገርና የህዝብ አስተዳደር ሥርዓት ሲያጫውተን አንዳንዶቻችን በአገራችን ውስጥ ይህ መኖሩን ባለማወቃችን እንቆጫለን ወደዛሬያችን ለማምጣት በምኞት እንጋልባለን።

ሌላው የጋሽ አሰፋ ትልቅነቱ እንደአንዳንዶቹ ፀሃፊዋች በራሱ አራት ነጥብ ዘግቶ እመኑልኝ ሳይለን ያየሁትና የኖርኩት እንጂ ያጠናሁት አይደልም ይላል በትዝታዋቹ ውስጥ እየሾለከ የሁላችንንም ትዝታ የቆሰቆሰውን ያህል ዛሬ በአገራችን ስለተንሰራፋው ሥርዓትም በማዘን እየገለጸ ወደተሻለ እንድንጓዝ ይማፀነናል፡፡

በእስራት ብዛት የሕዝብ ነጻነት ታፍኖ የቀረበት ዘመንም አገርም አለመኖሩን በማስረገጥ የጋራ ቤታችን የሚፈለገውን መጠነኛ ጥገና በማካሄድ ፈንታ መናድ የመረጡትን አውግዞአቸዋል፡፡ አገራቸውን ባለማወቅ ወይም ለማወቅ ባለመፈለግ ነቀዝ የበላው ቤት እንድትሆን ስለማድረጋቸው በመውቀስ ወደምትፈለገዋ ከስህተቷ ልምድ የቀሰመች አዲሲቷ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጽያን እንድንገነባ ይጣራል፡፡

"አብርሃም ሊንከን እንዳለውና ጋሽ አሰፋም በመጽሐፉ ላይ እንደጠቀሰው ‹‹ማንንም ያለቂም እንድንመለከት፣ሁሉንም በልግስና እንድናቅፍ፣በሃቅ ላይ እንድንጸና፣አምላክም ይህንን ሐቅ እንድናይ እንዲረዳን እንማጸን፡፡

ጋሽ አሰፋ ጫቦ ያመነበትን እንደተናገረና እንደሰራ ሃገርና ወገኑን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ እንደደከመ አለፈ፡፡ ይህን ታላቅ ሰው በህይወቱ እያለ በጣይቱ የትምህርትና የባህል ማዕከል ጋብዘን በማስተናገዳችን ክብር ተሰምቶናል ፡፡ ብዕረኞቻችን ጀግኖቻችን ጠበብቶቻችን ሳያልፉ ማክበር ግዴታችን መሆኑን እናምናለን፡፡

ይህን ታሪክ ስናዘጋጅ ቀና ትብብር ላደረጉልንና መረጃ በመስጠት ለተባበሩን ለነፃነት ተስፋዬ ÷ለገዛኸኝ ማሞ እና ለምንይችል እንግዳ የከበረ ምስጋናችንን ማቅረብ እንወዳለን::

~ ጣይቱ የባህል ና የትምህርት ማዕከል

23/09/2025
እንኳን አብሮ አደረሰን!!!!
20/09/2025

እንኳን አብሮ አደረሰን!!!!

ዮዮ ጊፋታ!
ዮ ማስቃላ!
ዮ ጋዜ ማስቃላ!
ዮኦ ማስቃላ!
ዮዮ ባላ ካዳቤ!
ዮዮ ቡዶ ኬሶ!

እንኳን ለወላይታ፤ ለጋሞ እና ለጎፋ ዞን ሕዝቦች የብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓላት በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!

ብዝኃነት እና ህብረ-ብሄራዊነት መለያው የሆነው የሰላም ተምሳሌቱ ክልላችን፤ የበርካታ ውብ ባህሎች እና የኅብር ማንነቶች ባለቤት የሆኑ የየራሳቸው የጊዜ ቀመርና የዘመን መለወጫ በዓላት ያሏቸው ሕዝቦች የጋራ ቤት ነው፡፡

በወርሃ መስከረም መባቻ በዘመናት አብሮነት የተዛመዱ፤ የተጋመዱ እና ባህል እሴቶቻቸውን ተወራርሰው የተሠናሠሉት የወላይታ፤ የጋሞ እና የጎፋ ዞን ህዝቦች በየራሳቸው የጊዜ ቀመር የአዲስ ዘመን ማብሰሪያ፤ የብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓሎቻቸውን በአዲስ መንፈስ፤ በብሩህ ተስፋ ተሞልተው በታላቅ ድምቀት ያከብራሉ፡፡

በዓላቱ እንደየብሄረሰቡ ትውፊትና ባህላዊ ዕሴት፡- በወላይታ 'ዮዮ ጊፋታ'፣ በጋሞ 'ዮ ማስቃላ'፣ በጎፋዎች ዘንድ 'ጋዜ ማስቃላ'፤ በኦይዳ ብሄረሰብ 'ዮኦ ማስቃላ' በዛይሴ 'ቡዶ ኬሶ' እንዲሁም በጊዲቾ 'ባላ ካዳቤ' በሚል በተቀራረበ ወቅት ከዘመን ዘመን ላሸጋገረ ፈጣሪ ምስጋና በማቅረብ ጭምር በአብሮነት የሚከበሩ ድንቅ እሴቶቻችን ናቸው፡፡

የክረምቱ ጭጋግና ጨለማ ተገፍፎ ብርሃን በሚፈነጥቅበት፤ እርሻው በመኽር አዝመራ አረንጓዴ ለብሶ ብሩህ ተስፋን በሚሰንቅበት ወቅት የሚከበሩት በዓላቱ፤ ፈተና የበዛበት የዝናብ ወቅት ማለፉን በማብሰር አሮጌውን ዓመት ሸኝተው አዲሱን ዓመት በብሩህ ተስፋ የሚቀበሉበት፣ የተራራቁና የተነፋፈቁ የሚገናኙበት እና የተጣሉ የሚታረቁበትም ነው፡፡

በዓላቱ የህዝቦቻችንን ዘመናት የተሻገረ አብሮነት፤ የርስ በርስ መስተጋብር እና ትስስር በሚያንፀባርቁ ተቀራራቢ ይዘት ባላቸው የተለያዩ ስርዓቶች፤ በተለይም የእርቅ፤ የሰላም፤ የአንድነት፤ የመደጋገፍና የወንድማማችነት እሴቶችን ባቀፉ ባህላዊ ሁነቶች የሚከበሩ በመሆኑ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳቸው ከፍተኛ ነው፡፡

በሁሉም አካባቢዎች በዓላቱ ሲከበሩ የተቃቃሩና የተጣሉ ታርቀው፤ ፀብና ቁርሾም በይቅርታ ተሽሮ፤ የጥላቻ ግንብ ፈርሶ፥ ሰላምና ፍቅር ይነግሳል፤ አብሮነትና አንድነት ይበልጥ ይጐለብታል፤ መተሳሰብና መረዳዳትም ያብባል፡፡

በዓላቱ ዘንድሮ በተለየ በመላ ኢትዮጵያዊያን የተደመረ አቅምና የዓላማ ጽናት ታላቁ የሕዳሴ ግድባችንን በድል ባጠናቀቅንበት እና የኢትዮጵያን የማንሠራራት ምዕራፍ ጅማሮ ባበሰርንበት ወቅት የሚከበሩ እንደመሆኑ፤ ከአዲስ ዓመት የብሩህ ተስፋ ስንቅ ጋር ትብብራችንን አጠናክረን ለሌላ ታላቅ ስኬት የምንዘጋጅበት ሊሆኑ ይገባል፡፡

ብዝኃነት ጌጣችን በሆነው ክልላችን፥ በዓላቱ ከሚያለያዩን ይልቅ አንድ የሚያደርጉን በብዝኃነት ውስጥ ያበቡ የአንድነት ግማዶቻችን እጅግ የበዙ መሆኑን በጉልህ የሚያንፀባርቁ ዓውዳቻችንም ናቸው፡፡

በመሆኑም በዓላቱን ስናከብር በጥቃቅን ልዩነቶች የኋላት ከመሳሳብ ይልቅ ከጽኑ የኅብረ-ብሔራዊ አንድነታችን የሚመነጩ የኅብረት፤ የመተባባርና የመደጋገፍ እሴቶቻችንን በማጎልበት ለጋራ ሰላም፤ ልማትና ሁለንተናዊ ብልጽግና በጋር ለመትጋት በመነሳት መሆን ይኖርበታል፡፡

አባቶች ጠብቀው ያቆዩልንን እኚህን ድንቅ የሰላምና የአንድነት እሴቶች ያቀፉ በዓላት ከነሙሉ ባህላዊ ይዘታቸውና ስርዓታቸው ጠብቆ ለቀጣይ ትውልድ ከማሻገር ባላፈ የበዓላቱን አከባበር በማስተዋወቅ በቱሪዝም ዘርፍ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታቸውን ለማሳደግ መስራት ይገባል፡፡

አዲሱ ዘመን ሰላም፤ ፍቅርና አንድነት የሚያብብበት፤ ኅብረትና ትብብራችን ከፍ ብሎ ለታላቅ ስኬት የሚንበቃበት እንዲሆንልን መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ።

መልካም በዓል!
ዮ ዮ ዮ ዮ ዮ..........
ጥላሁን ከበደ
ርዕሰ መስተዳድር

19/09/2025
19/09/2025

Address

አርባ ምንጭ ደቡብ ኢትዮጵያ
Arba Minch'

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when DebubTimes ደቡብ ታይምስ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share