Arbaminch General Hospital

Arbaminch General Hospital ይህ የአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ትክክለኛው የፌስቡክ ገጽ ነው!

@@☘️   ☘️@@@በአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል በቅርቡ ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሊሆን ያለው   የመጀመሪያውን የተሳካ ቀዶ ጥገና ማድረጉን አሳወቀ።ይህ የሕክምና ማዕከል ለተወሰ...
22/09/2026

@@☘️ ☘️@@@

በአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል በቅርቡ ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሊሆን ያለው የመጀመሪያውን የተሳካ ቀዶ ጥገና ማድረጉን አሳወቀ።

ይህ የሕክምና ማዕከል ለተወሰኑ ጊዜያት ግንባታው ሳይጠናቀቅ ቢቆይም በአፋጣኝ እንዲጠናቀቅ በማድረግ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን በከፍተኛ ጥረትና ፍጥነት የተሠራ መሆኑን ያበሰሩት የሆስፒታሉ ዋና ሥራአስኪያጅ ዶ/ር አምባቸው ዱማ ይህ የቃጠሎ ሕክምና ማዕከል በሙሉ አቅሙ አገልግሎቱን ሊሰጥ የተዘጋጀ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በቅርቡ ለምረቃ እንደሚበቃም ተናግረዋል።

ሥራ አስኪያጁ አክለውም ይህ ማዕከል እንደሀገር ካሉ ጥቅት ከተደራጁ ቃጠሎ ህክምና ማዕከላት አንዱ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ተመሪቆ በሙሉ አቅሙ አገልግሎት ሲጀምር የሕብረተሰባችንን አላስፈላጊ መጉላላትን የሚያስቀር እና የሆስፒታሉን ደረጃ በእጅጉ የሚያሳድግ መሆኑንም ጭምር ገልፀዋል።

መስከረም 12/2019 ዓ.ም
አርባምንጭ

እንኳን   “ዮ ማስቃላ” በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!“ዮ ማስቃላ” ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲሱ ብሩህ ዘመን የምንሸጋገርበት፣ የልምላሜና የተስፋ ብስራት የሚበሰርበት ደማቅና ልዩ የዘመን መለወጫ...
22/09/2026

እንኳን “ዮ ማስቃላ” በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

“ዮ ማስቃላ” ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲሱ ብሩህ ዘመን የምንሸጋገርበት፣ የልምላሜና የተስፋ ብስራት የሚበሰርበት ደማቅና ልዩ የዘመን መለወጫ በዓላችን ነው ሲሉ በመናገር የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

አዲሱ ዘመን የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር፣ የብልፅግናና የአንድነት ዘመን ይሁንልን!
Hashshu sarron Gaththides!!!
ዮ... ዮ... ዮ ጋሞ ማስቃላ!

🚨🚨🚨 🚨🚨🚨🚨  !!
21/09/2026

🚨🚨🚨 🚨🚨🚨🚨
!!

 ! ! 🎉‎   በሥርዓት ማነቆዎችን በማሻሻል (System_Bottleneck_Flow_Reform –  ) ላሳየው አስደናቂ አፈጻጸም የጤና ኢኖቬሽን ሽልማት (Health Innovation Awar...
19/09/2026

! ! 🎉
‎
በሥርዓት ማነቆዎችን በማሻሻል (System_Bottleneck_Flow_Reform – ) ላሳየው አስደናቂ አፈጻጸም የጤና ኢኖቬሽን ሽልማት (Health Innovation Award)የእውቅና ሰርትፊኬት ስልተበረከተልን እንኳን ደስ አለን! 🏆
‎የሆስፒታሉ ሰራ አስኪያጅ ዶ/ር አምባቸው ዱማ እንደገለጹት ይህ እውቅና ሆስፒታሉ ወሳኝ የሥርዓት ማነቆዎችን በመፍታት፣ የሥራ አሠራሮችን በማሻሻል እና ለቀጣዩ የተቋማዊ የላቀ ብቃትና የእውቅና ሂደት ጠንካራ መሠረት በመጣል ላሳየው አመርቂ ውጤት የተሰጠ ነው።
‎ይህ ስኬት የሆስፒታሉን ራዕይ በማሳካት የተሳተፉ የሁሉም ሠራተኞች ትጋት፣ ቁርጠኝነት፣ ትብብር እና የማይታክት ጥረት ውጤት ነው። ችግሮችን በመለየት፣ መፍትሔዎችን በመተግበር፣ የሥራ ሂደቶችን በማሻሻል እና የተሻሉ አሠራሮችን በማስቀጠል የተሳተፋችሁ እያንዳንዳችሁ ለዚህ ውጤት የራሳችሁን ወሳኝ አስተዋፅኦ አበርክታችኋል።
‎በሆስፒታሉ አመራር ስም ለመላው የሆስፒታሉ ሠራተኞች ልባዊ የሆነ እንኳን ደስ አላችሁና ከፍተኛ ምስጋና እናቀርባለን።
‎የሆስፒታሉ የጤና አገልግሎት ጥራት ዳይሬክተር አቶ ጠረፉ ተካ እንደገለጹት ይህንን እውቅና እንደ መድረሻ ሳይሆን፣ ወደ ቀጣይ የጥራት ማሻሻያ፣ የኢኖቬሽን፣ የተቋማዊ ልህቀት እና ለማህበረሰባችን የተሻለ የጤና አገልግሎት ለማቅረብ የሚያነሳሳን ትልቅ ስኬት እንደሆነ እንውሰድ።
‎እንኳን ደስ አላችሁ፣ የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ቤተሰብ! 👏🎉
‎በጋራ ሥርዓቶችን እናሻሽላለን።
‎በጋራ ማነቆዎችን እንፈታለን።
‎በጋራ ጥራትንና ልህቀትን እናስፋፋለን።

28th Annual Health Sector Review Meeting (ARM)CALL FOR EXPRESSION OF INTEREST (EOI)The Federal Ministry of Health (MOH) ...
19/09/2026

28th Annual Health Sector Review Meeting (ARM)

CALL FOR EXPRESSION OF INTEREST (EOI)

The Federal Ministry of Health (MOH) invites health-sector stakeholders to express their interest in exhibiting at the 28th Annual Health Sector Review Meeting (ARM), to be held in Hossana from October 21–23, 2026.

Theme: “Transformative Reform for a Sovereign and Resilient Health System”

The exhibition will provide a platform to showcase achievements, innovations, evidence, testimonies, lessons learned, ongoing initiatives, and transformative reforms contributing to the strengthening of Ethiopia’s health system.

Interested organizations are invited to review the full EOI document and submit their expression of interest in accordance with the instructions provided.

For the full Call for Expression of Interest and submission instructions, please visit:
https://www.moh.gov.et/28th_ARM_CALL_FOR_EXPRESSION_OF_INTEREST

Deadline: Within one (1) week of this announcement

የተግባር ሙያ ፈቃድ ፈተና ለወሰዳችሁ የአንስቴዥያ ተመዛኞች በሙሉ___________በጳጉሜ  3/2018 ዓ.ም የተሰጠውን የተግባር ሙያ ፈቃድ ፈተና የወሰዳችሁ የአንስቴዥያ ተመዛኞች ከመስከረም...
16/09/2026

የተግባር ሙያ ፈቃድ ፈተና ለወሰዳችሁ የአንስቴዥያ ተመዛኞች በሙሉ
___________

በጳጉሜ 3/2018 ዓ.ም የተሰጠውን የተግባር ሙያ ፈቃድ ፈተና የወሰዳችሁ የአንስቴዥያ ተመዛኞች ከመስከረም 6/2019 ዓ.ም ጀምሮ https://hple.moh.gov.et ላይ በመግባት የብሄራዊ መለያ ቁጥር(FAN) እና Password በማስገባት የፈተና ውጤታችሁን መመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተመዛኞች ውጤት ከተገለጸበት ዕለት አንስቶ ባሉት 5(አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት በስልክ ቁጥር 952 በመደወል ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ፈተናውን ያለፋችሁ ተመዛኞች ከሃሙስ መስከረም 7/2019 ዓ.ም ጀምሮ ስም ዝርዝራችሁ ወደ ክልል የሚላክ ስለሆነ የሙያ ፈቃዳችሁን 12ተኛ ክፍል በጨረሳችሁበት ክልል ማውጣት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ድንገተኛ የማህበረሰብ ጤና ሕክምና ቡድን (EMT) ከዓለም ጤና ድርጅት እውቅና አገኘ__________የማህበረሰብ ድንገተኛ የጤና ስጋት ሲከሰት ዜጎቻችንን ቀድሞ ለመጠበቅና ...
16/09/2026

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ድንገተኛ የማህበረሰብ ጤና ሕክምና ቡድን (EMT) ከዓለም ጤና ድርጅት እውቅና አገኘ
__________

የማህበረሰብ ድንገተኛ የጤና ስጋት ሲከሰት ዜጎቻችንን ቀድሞ ለመጠበቅና ሲከሰትም በበቂ ሁኔታ ለመቆጣጠር የሚያስችል አቅም እየተፈጠረ መምጣቱን እና ውጤታማ መሆኑን የሚያረጋግጥ እውቅና ነው፤ ለኢትዮዽያ የህክምና ዘርፍ ልዩ የኩራትና የደስታ ቀንም መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ገልጸዋል።

የተገኘው ስኬት በጤና ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (EPHI) እና በባለድርሻና አጋር አካላት የጋራ ቅንጅትና ትብብር አማካኝነት ለዓመታት በተከናወነ አመራርነት፣ ኢንቨስትመንት፣ ሥልጠናና እና ድጋፍ የተገኘ በመሆኑ እንደ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ሁሉንም አካላት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ሚኒስትሯ አመስግነዋል፡፡ በቀጣይም የተገኘውን ውጤት በማላቅ እና ትጋታችንን በመጨመር ለሌሎች የጤና ግቦች መሳካት ትብብራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

እውቅናው በጥብቅና ገለልተኛ በሆነ አካል ዓለም አቀፍ ማረጋገጫ ሂደቶችን በበርካታ መመዘኛዎች ተፈትሾ መረጋገጡን የገለጹት ደግሞ የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሀይሉ ናቸው። የኢትዮጵያ ቡድንም በበሽታ ወረርሽኞች፣ በተፈጥሮ አደጋዎችና በሰብዓዊ ቀውሶች ወቅት በጥራት፣ በዝግጁነት፣ በፈጣን የማሰማራት አቅምና በድንገተኛ የማህበረሰብ ጤና ምላሽ በመመዘን የተገኘ ውጤት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የWHO ተወካይ ዶ/ር ፍራንሲስ ቺሳካ ካሶሎ በበኩላቸው ይህ ስኬት ኢትዮጵያ ማህበረሰቦቿን ከድንገተኛ የጤና ስጋት በተጠናከረ ዝግጁነትና ፈጣን ምላሽ አቅም ለመጠበቅ ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል ነው ብለዋል። በዚህም የኢትዮጵያ መንግስትንና ጤና ሚኒስቴርን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከኅዳር 3–5 ቀን 2019 ዓ.ም. (3–5 November 2026) በአዲስ አበባ የሚካሄደውን 7ኛውን ዓለም አቀፍ የEmergency Medical Teams Meeting ለማስተናገድ ዝግጅት እያደረገች ትገኛለች። በWHO የአፍሪካ አህጉር ሲካሄድ የመጀመሪያው ጊዜ ይሆናል።

ከመጠን በላይ ስኳር፣ ጨው እና ስብ የያዙ ምግቦችን በመቀነስ ፍራፍሬ፣ አትክልት፣ ጥራጥሬ እና በፕሮቲን የበለፀጉ ምግቦችን እንዲሁም በቂ ውሃ በየቀኑ በመውሰድ ጤናማ አመጋገብን ይከተሉ!   ...
15/09/2026

ከመጠን በላይ ስኳር፣ ጨው እና ስብ የያዙ ምግቦችን በመቀነስ ፍራፍሬ፣ አትክልት፣ ጥራጥሬ እና በፕሮቲን የበለፀጉ ምግቦችን እንዲሁም በቂ ውሃ በየቀኑ በመውሰድ ጤናማ አመጋገብን ይከተሉ!




!!

የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በዓልን ከታካሚዎች እና ከሠራተኞች ጋር በጋራ አከበረ።                                       መስከረም 1/...
11/09/2026

የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በዓልን ከታካሚዎች እና ከሠራተኞች ጋር በጋራ አከበረ።
መስከረም 1/2019 ዓም።
የአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል አዲስ ዓመቱን ከታካሚዎች እና ከሠራተኞች ጋር በጋራ በደማቅ ሁኔታ እያከበረ ይገኛል።

የእንኳን አደረሳቹ መልዕክቱን ያስተላለፉት የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር አምባቸው ዱማ እንዳሉት ይህን በዓል በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብንሆንም ፈጣሪ ፈቅዶ ለመኖር በቅተናልና ውድ ታካሚዎቻችን ያለ ምንም መከፋት በዓሉን ቤት እንዳከበሩ እንዲሰማቸው በማለት ሁሉም ታካሚዎቻችን ፈጣሪ ፈቅዶ ፈጣን መዳን እንዲሆንላቸው በመመኘት የመልካም በዓል ምኞታቸውን አክለው ገልፀዋል።

በተቋማችን በበዓሉ ዕለት የሕብረተሰባቹን ጤና ለመጠበቅ በተቋማችን የተገኛቹ የሁልጊዜም ትጉህ እና ታማኝ ሰራተኞቻችን ለእናንተም መልካም በዓል እንኳን አደረሳቹ እንኳን አደረሰን በማለት ለተቋሙ ሠራተኞች ልባዊ ምስጋናቸውን ችረዋል።

በተጨማሪም የሆስፒታሉ ሚድዋይፈሪ እና ነርሲንግ ዳይሬክተር አቶ በዛብህ በቀለ አክለውም በተቋሙ ውስጥ ጤና ባለሙያው ሌተቀን ለታካሚዎቻችን የምትሰጡት እንክብካቤ እና ፍቅር መቀጠል አለበት በማለት የእንኳን አደረሳቹን መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

አዲሱ ዓመት የታመመው የሚድንበት, ያጣው የሚያገኝበት, የከፋው የሚደሰትበት, የተጋው የሚሸለምበት የሠላም, የፍቅር, የመተሳሰብ, አብሮ የመሥራት እና ፍሬ የማፍራት ዓመት እንዲሆን ተመኘን 🙏

!!🙏

🏥

እንኳን ለ2019 ዓ.ም ዓዲስ ዓመት በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ!🌼🌼🌼አዲሱ ዓመት ለሁላችንም የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር፣ የአንድነት እና የበረከት ዓመት እንዲሆን እንመኛለን!🌼ባሳለፍነ...
10/09/2026

እንኳን ለ2019 ዓ.ም ዓዲስ ዓመት በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ!🌼🌼🌼

አዲሱ ዓመት ለሁላችንም የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር፣ የአንድነት እና የበረከት ዓመት እንዲሆን እንመኛለን!🌼

ባሳለፍነው ዓመት እንደ ተቋም በሕብረት ትጋት የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ በፌደራል,በክልል እንዲሁም በዞን ዕውቅናን ተችረን መልካም ጊዜያትን በጋራ ትጋትና በፈጣሪ እርዳታ የተሻለ ውጤት ማስመዝገባችን ይታወሳል።

በአዲሱ ዓመትም ትጋታችንን በመጨመር መሻሻል የሚገቡ ነገሮችን በማሻሻል ከአምና የተሻለ ውጤት የምናስመዘግብበት ዓመት እንዲሆንልን መልካም ምኞቴን ከወዲሁ እገልጻለው።

አዲሱ ዓመት
#የተስፋና #የደስታ፣ የሚያፈራበት፣ ምኞታችን የሚሳካበት እና ቤታችን በሰላም፣ በፍቅርና በበረከት የሚሞላበት ዓመት እንዲሆንልን እመኛለሁ።

!🌼🌼🌼

ዶ/ር
የአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ሥራአስኪያጅ

Address

Gamo Zone
Arba Minch'

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Arbaminch General Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share