10/07/2025
ዜና ዕረፍት 💔
አርባምንጭ ከተማ እጅግ ደግ ልጇን አጥታለች!
በበጎ አድራጎት ሥራዎቹ ይታወቅ የነበረው ወጣት ተወዳጅ መኮንን በድንገተኛ ህልፈት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ የብዙዎችን ልብ በሀዘን አድምቷል።
ተወዳጅ በከተማዋ በተለያዩ የበጎ አድራጎት ተግባራት ግንባር ቀደም ተሳታፊ ሲሆን፣ በተለይም ለመኖሪያ ቤት እጦት የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ እና የበርካታ ድሆችን ሙሉ የህክምና ወጪ በመሸፈን ይታወቅ ነበር።
እነዚህ ደግ ሥራዎቹ የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትንና ፍቅርን አስገኝተውለት ነበር፤ ከተማዋም ሁሌም በአመስጋኝነት ታስበዋለች።
ይህ ድንገተኛ ሞት ለመላው ቤተሰቦቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቹ፣ እና የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ሁሉ ታላቅ ሀዘንን ጥሎ አልፏል።
* ለቤተሰቦቹ
* ለጏደኞቹ
* ለወዳጅ ለወዳጆቹ
መፅናናትን እንመኛለን።
ነፍስህን በአፀደ ገነት ያኑራት! 🙏
©️የአርባምንጭ በጎ ፈቃደኞች ማህበር