03/09/2026
የሶዶ ከተማ አስተዳደር የጋሞ ብሔር ዘመን መለወጫ “ዮ...ማስቃላ” በዓል ጥሪ ተቀበለ
የሶዶ ከተማ አስተዳደር በጋሞ ዞን በሚከበረው “ዮ...ማስቃላ” የጋሞ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል ላይ እንዲታደሙ የቀረበላቸውን ጥሪ ተቀብሏል።
ጥሪውን የሶዶ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ መንግሥቱ ትግሮ እና የከንቲባ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፊስሐ ፀጋዬ በጋራ በመሆን ተቀብለዋል።
ጥሪውን ያቀረቡት ከጋሞ ዞን እና ከአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር የተወጣጡ የልዑካን ቡድን አባላት የሆኑት የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ልዩ አማካሪ አቶ ተስፉጺሆን ዘነበ፣ የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ መምሪያ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ቡዙነህ እና የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ አብነት ተስፋዬ ናቸው።
በወቅቱም የዞኑ አመራሮች ጥሪውን በመቀበል ለመላው የጋሞ ዞን ሕዝብ “እንኳን ለ“ዮ...ማስቃላ” በዓል በሰላም አደረሳችሁ” በማለት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።