Arba Minch FM 90.9 / አርባ ምንጭ ኤፍ ኤም 90.9

Arba Minch FM 90.9 / አርባ ምንጭ  ኤፍ ኤም 90.9 የአርባ ምንጭ ኤፍ ኤም 90.9 ሬድዮ የህብራዊነት ድምፅ በመሆኑ ያዳምጡታል ይናገሩበታልም !

ተጨማሪ 3 ሺህ 350 ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አምጥተዋልአርባምንጭ፡መስከረም 22፣2018 ዓ.ም (ኤፍኤም 90.9)በተሻሻለው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት እና በተስተካ...
02/10/2025

ተጨማሪ 3 ሺህ 350 ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አምጥተዋል

አርባምንጭ፡መስከረም 22፣2018 ዓ.ም (ኤፍኤም 90.9)

በተሻሻለው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት እና በተስተካከለው የፊዝክስ ውጤት ተጨማሪ 3 ሺህ 350 ተማሪዎች አልፈዋል አለ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት።

ትምህርት ሚኒስቴር በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና አማካይ ውጤታቸው 49 ነጥብ 50 እስከ 49 ነጥብ 99 በመቶ ያመጡ ተማሪዎች ወደ 50 በመቶ እንዲጠጋጋ መወሰኑ ይታወሳል፡፡

በዚህ መሰረትም የ2017 ትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ከ300 ወደ 297 ዝቅ ብሏል፡፡

በተጨማሪም በበይነ መረብ በተፈተኑ በተወሰኑ ተማሪዎች ላይ የፊዚክስ ውጤት ወደ መቶኛ ያልተቀየረላቸው እንዲሁም ወደ መቶኛ ሲቀየር በነጥብ ቤት የነበሩ ቁጥሮች ያልተደመረላቸው ተማሪዎች እንደነበሩ ተጠቅሷል፡፡

በዚህም ተማሪዎቹ ተያያዥ መረጃዎች ላይ ቅሬታቸውን አቅርበው ውጤታቸው መስተካከሉ ነው የተገለጸው፡፡

ይህን ተከትሎም 3 ሺህ 350 ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ያመጡ ሲሆን ÷ በ50 ከመቶና በላይ ያመጡ አጠቃላይ ተፈታኞች ቁጥርም 52 ሺህ 279 ደርሷል፡፡

ያለፉ ተማሪዎች ቁጥር በመቶኛ ሲገለጽም 8 ነጥብ 9 በመቶ ሆኖ መመዝቡን የአገልግሎቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

"የታደሰ ጂኦ-ስትራቴጂያዊ ቁመና በሁሉም ኢትዮጵያ የጋራ ትጋት" በሚል መሪ ቃል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል። አርባምንጭ፡መስከረም 21፣...
02/10/2025

"የታደሰ ጂኦ-ስትራቴጂያዊ ቁመና በሁሉም ኢትዮጵያ የጋራ ትጋት" በሚል መሪ ቃል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

አርባምንጭ፡መስከረም 21፣2018 ዓ.ም(ኤፍኤም 90.9)

"የታደሰ ጂኦ-ስትራቴጂያዊ ቁመና በሁሉም ኢትዮጵያ የጋራ ትጋት" በሚል መሪ ቃል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

በስልጠና መድረክ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ምክትል አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወይዘሮ ወላይቴ ቢቶ በሀገራዊ ጉዳይ በጋራ መመካከርና ለሀገር ጥቅምና ብልጽግና መትጋት የሚያስፈልግ መሆኑን አንስተዋል።

የአገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ለማሳለጥ ትልቅ አቅም ይፈጥራል ያሉት ምክትል አፈ-ጉባኤዋ አዳዲስ አስተሳሰቦችን በማመንጨትና በመፍጠር ለተሻለ ስኬት ለመነሳት አመለካከቶችን በማስተካከል የአንድን ተቋም የአሰራር ስርአት በማዘመን የተቋሙን ራዕይ፣ተልዕኮና እሴቶች በተሻለ መንገድ እንዲሁም በስትራቴጂ በመምራት ለተቋሙ የላቀ ስኬት የሚያበቃ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

በብሔራዊ ጥቅምና የጂኦ-ስትራተጂ ቁመና የሚያውጠነጥን ሀገራዊና ዓለም አቀፍ ጉዳዮችን የዳሰሰ የስልጠና ሰነድ በምክትል ቢሮ ኃላፊ ማዕረግ በፋይናስና አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ በአቶ አማሩ ሃቱዬ እየቀረበ ይገኛል።

ስልጠናው አዳዲስ አስተሳሰቦችን በማመንጨትና በመፍጠር ለተሻለ ስኬትና መነሳሳት የሚፈጥሮ መሆኑ በሰነዱ ተመላክቷል ሲል የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ዘግቧል ።

‎ባለፉት የለዉጥ አመታት የተመዘገቡ ድሎችን ለማስቀጠል የአመራሩን የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም ማጎልበት ያስፈልጋል- አቶ ገ/መስቀል ጫላ‎‎አአርባምንጭ ፡መስከረም22፣2018ዓ.ም(ኤፍኤም 90...
02/10/2025

‎ባለፉት የለዉጥ አመታት የተመዘገቡ ድሎችን ለማስቀጠል የአመራሩን የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም ማጎልበት ያስፈልጋል- አቶ ገ/መስቀል ጫላ

‎አአርባምንጭ ፡መስከረም22፣2018ዓ.ም(ኤፍኤም 90.9)

‎የአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ ከብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቅ/ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በየደረጃው ለሚገኙ የክልሉ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።

‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገ/መስቀል ጫላ በስልጠናው መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት በክልሉ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተገኙ የልማት ስኬቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የአመራሩን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ማጎልበት ይገባል ብለዋል።

‎ባለፉት ሰባት የለውጥ ዓመታት በክልልም ሆነ በሀገር ደረጃ ለተመዘገቡ ስኬታማ የልማት ድሎች በአመራሩ መካከል የተፈጠረዉ አዳጊ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ትልቅ አቅም መፍጠሩንም ጠቁመዋል፡፡

‎ለክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የተዘጋጀው የአቅም ግንባታ ስልጠና ዋና ዓላማም ክልላዊ ብሎም ሀገራዊ ኃላፊነትን በብቃት የሚወጣ አመራር ለመፍጠር መሆኑን ተናግረዋል።

‎የስልጠናው ተሳታፊ አመራሮች ስልጠናውን በትኩረት በመከታተል ለቀጣይ ስራዎች መሳለጥ እንደ ዕድል ሊያዉሉት እንደሚገባም አቶ ገ/መስቀል አሳስበዋል።

‎የክልሉ መንግስት የአመራሩን አቅም ለማጎልበት ተከታታይ የአመራር የአቅም ግንባታ ስልጠና እያዘገጀ ሲሰጥ መቆየቱን አስታዉሰዋል።

‎አመራር የሚሰለጥነው የሰዉ ኃይል፣ ሕዝብ እና ሀብት ስለሚያስተዳድር እንዲሁም የጊዜ አጠቃቀምን ስለሚገራ መሆኑን ገልፀዉ በክልሉ ይህንን ወደ ዉጤት ለመቀየር የሚያስችል ባህልና እሴት መኖሩን አስረድተዋል።

‎ለተከታታይ ሶስት ቀናት በሚሰጠዉ ስልጠና የክልል ማዕከል ከፍተኛ አመራሮች፣ የዞን እና የሪጂኦ ፖሊስ ከተሞች አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት በመሳተፍ ላይ ናቸው።

‎ምንጭ ፡ የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ

አዲሱ የመንግሥት ሰራተኞች የደመወዝ እርከን ይፋ ሆነ‎አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲሱ የመንግሥት ሰራተኞች የደመወዝ እርከን ይፋ ሆኗል።የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚ...
02/10/2025

አዲሱ የመንግሥት ሰራተኞች የደመወዝ እርከን ይፋ ሆነ

‎አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲሱ የመንግሥት ሰራተኞች የደመወዝ እርከን ይፋ ሆኗል።

የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) ለፋና ዲጂታል እንዳረጋገጡት፤ ለመንግሥት ሰራተኞች የተደረገው የደመወዝ ማሻሻያ ከዚህ ወር ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል።

ኮሚሽኑ ይፋ ያደረገው አዲሱ የደመወዝ እርከን እንደሚከተለው ቀርቧል።

ከተማን ስናዘምን ለልጆቻችን የሚመች እና የሚመጥን ሀገር እየሰራን ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)አርባምንጭ፡መስከረም 22፣2018 ዓ.ም(ኤፍኤም90.9)ከተማን በዕቅድ መስራት ...
02/10/2025

ከተማን ስናዘምን ለልጆቻችን የሚመች እና የሚመጥን ሀገር እየሰራን ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

አርባምንጭ፡መስከረም 22፣2018 ዓ.ም(ኤፍኤም90.9)

ከተማን በዕቅድ መስራት ያስፈልጋል፤ ከተማን ስናዘምን ለልጆቻችን የሚመች እና የሚመጥን ሀገር እየሰራን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የጅግጅጋ ከተማ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝቱ ወቅት ከጥቂት ጊዜ በፊት ጅግጅጋን ጎብኝተው እንደነበር ገልጸው፤ አሁን ያየነው ጅግጅጋ ከዚህ ቀደም ካየነው በእጅጉ የተለየ ነው ብለዋል፡፡

የኮሪደር ልማት ለዜጎች ስራ በመፍጠር ቱሪዝሙን በማነቃቃት እና የሰዎችን የአኗኗር ዘዬ በማሻሻል እየተጫወተ ያለው ሚና ከፍተኛ መሁኑን ተናግረዋል፡፡

በከተማዋ 60 ኪሎሜትር የውስጥ ለውስጥ መንገድ 10 ኪሎሜትር የእግረኛ መንገድ 10 ኪሎ ሜትር የብስክሌት መስመር እንዲሁም በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ ቤቶች ተገንብተው መመልከታቸውን ጠቅሰዋል፡፡

እንዲሁም በከተማዋ የመብራት መሰረተ ልማት መስፋፋቱን እና ባለፉት ጥቂት ዓመታት የመብራት ተጠቃሚነት በአራት እጥፍ ማደጉን ጠቁመዋል፡፡

ከተሞች በፕላን ባለመገንባታቸው የችግር መንስኤ ሲሆኑ እንደሚታይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተው፤ ከተሜነት የሚያስፈልገው ለተሳለጠ አገለግሎት ነው ብለዋል፡፡

እንደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ዘገባ ከተማን ስናዘምን የምንሰራው የነገ የልጆቻችን መኖሪያን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል፡፡

በዘንድሮ የትምህርት ዘመን የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ  በቂ ዝግጅት በማድረግ ወደ ሥራ መገባቱ ተገለፀ ‎‎አርባምንጭ፡መስከረም22፣2018ዓ.ም(ኤፍኤም 90.9)‎‎የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር...
02/10/2025

በዘንድሮ የትምህርት ዘመን የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በቂ ዝግጅት በማድረግ ወደ ሥራ መገባቱ ተገለፀ

‎አርባምንጭ፡መስከረም22፣2018ዓ.ም(ኤፍኤም 90.9)

‎የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር በትምህርት ዘመኑ ውጤት ለማስመዝገብ ከወትሮ በተሻለ ሁነታ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል ።

‎ ተማሪ ደገፉ ዳንኤል በአርባ ምንጭ ከተማ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ10ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን ፤ በትምህርት ዘመኑ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ጠንክሮ እንደሚሠራ ተናግሮ ምቹ የመማሪያ አከባቢ እየተፈጠረ መሆኑን ጠቁሟል።

‎ በክረምት ልዩ ትኩረት በመስጠት ዝግጅት በማድረግ እንደቆዬች የምትናገረው ደግሞ በፊውቸር ሆፕ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ኑኃሚን ተካልኝ ናት ።

‎በፊውቸር ሆፕ አካዳሚ የመካከለኛ ደረጃ ተማሪዎች ምክትል ርዕሰ መምህር አቶ ደሣለኝ ጎአ ፤የ2018 የትምህርት ስራውን ውጤታማ ለማድረግ ተገቢው ግብዓት በማሟላት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል ።

‎ትምሀርት ቤቱበሥነ-ምግባር የታነፀን ዜጋ ማፍራት ዋነኛ አላማቸው እንደሆነ ጠቅሰዋል።

‎ዘንድሮ ትምህርትን በጊዜ ከማስጀመር ጀምሮ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን የሚናገሩት የአርባ ምንጭ 2ኛና መሠናዶ ትምህርት ቤት ዋና ርዕሰ መምህሪ አቶ ስለሽ ካሣ ፤ ከአምናው በተሻለ ሁነታ ዝግጅት ተደርጎ ሥራ መጀመሩን ገልፀዋል።

‎በት/ቤቱ ከ1ሺህ 337 በላይ ተማሮችን በመቀበል ከመስከረም 5 ጀምሮ የትምህርት ሥራ መጀመሩን የጠቁሙት ርዕሰ መምህሩ ፤ ቀደም ሲል ሲስተዋል የነበረውን የትምህርት ስብራት ለመጠገን ከመማር ማስተማር ጀምሮ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

‎ አቶ መለሰ መንዛ በአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ሲሆኑ በ2018 የትምህርት ዘመን ሥራ የ2017 አፈፃፀምን መነሻን ዝግጅት በማድረግ መቆየታቸውን ገልፀዋል ።

‎ትምህርት ቤቶችን ለመማር ማስተማር ሥራ ምቹ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ መቆየቱንም አስረድተዋል።

‎በትምህርት ዘመኑ እንደከተማ አስተዳደሩ ከ46 ሺህ 566 በላይ ተማሮችን ለመቀበል ታቅዶ 83 ከመቶ በመቀበል የትምህርት ሥራ መጀመሩን አስረድተዋል ።

‎አንድ መፅሐፍ ለአንድ ተማሪ በሚል በህብረተሰብ ተሳትፎ ከ 9 ሺህ 792 በላይ መጽሐፍት በማሳተም ለተማሪዎች ማሰራጨታቸውን ጠቅሰዋል ።

‎ዘጋቢ ፡ አበበ ዳባ

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ብዙ አደናቃፊ ችግሮችን አልፎ ለምርቃት መብቃቱ እንዳስደሰታቸው ያነጋገርናቸው የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩአርባምንጭ ፡መስከረም 21፣2018ዓ.ም(...
01/10/2025

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ብዙ አደናቃፊ ችግሮችን አልፎ ለምርቃት መብቃቱ እንዳስደሰታቸው ያነጋገርናቸው የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩ

አርባምንጭ ፡መስከረም 21፣2018ዓ.ም(ኤፍኤም 90.9)

በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የጋንታ ቦንኬ ቀበሌ ነዋሪና የቀበሌዋ ሥራ አስኪያጅ አቶ ማጆሬ ማይጫ፤ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በግላቸው ከማዋጣት ባለፈ በሃብት ማሰባሰቡ በኩል ህብረተሰቡን ሲያስተባብሩ መቆየታቸውን ተናግረው ግድቡ ብዙ አደናቃፊ ችግሮችን አልፎ በመመረቁ ደስ ብሎኛል ብለዋል።

ሌላኛው የቀበሌዋ ነዋሪ አቶ ገላነህ ገረመው ፤ እሳቸውም ሆኑ ቤተሰባቸው ለግድቡ ማዋጣታቸውን ጠቅሰው የህዳሴው ግድብ በመመረቁ ደስ ብሎኛል፤ ሀገሬን ያስጠራው ይህ ግድብ ለልጅ ልጅ ያስቀመጥነው ቅርስ ነው፣ ነው ያሉት።

አስተያየት ሰጪዎቹ በቀጣይ ተመሣሣይ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ሲሰሩ ለስኬቱ በቀዳሚነት እንደሚሰለፉ ገልጸዋል።

የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ልዩ አማካሪ ጽ/ቤት የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና መሠረተ ልማት አማካሪ ባለሙያ ቀሲስ ወሳኙ ለማ ለግንባታው ሃብት ከማሰባሰብ አንስቶ በግድቡ ዙሪያ አሉታዊ ሓሳቦች ሲነሱ ህብረተሰቡን በማስተባበር ህዝባዊ ምላሽ በመስጠት ለግድቡ ግንባታ አስተዋጽኦ ሲያበረክቱ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

አብሮነታችን ኃይልና ጉልበት ሆኖን ግድቡ በመመረቁ እጅግ ደስተኛ ማህበረሰብ ተፈጥሯልና ደስ ብሎናል ብለዋል።

አፄ ኃይሌ ሥላሴ እኛ ባንሠራው ቀጣዩ ትልድ ይሠራዋል ብለው በተነበዩት እና የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር እኛው እንገነባዋለን ባሉት መሠረት እውነትም ገንብተን አጠናቀናልና በቀጣይ መንግስት ለሀገር ግንባታ በሚተልማቸው ፕሮጀክቶች በግልም ሆነ እንደ ጽ/ቤት በማስተባበር በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል።

ዘጋቢ፦ ፍሬው ዲጋ

በአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት እየተሻሻለ መምጣቱን የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ተናገሩ‎‎አርባምንጭ፡መስከረም 21፣2018ዓ.ም (ኤፍኤም 90.)‎‎በሆስፒታሉ የሚሰጠውን...
01/10/2025

በአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት እየተሻሻለ መምጣቱን የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ተናገሩ

‎አርባምንጭ፡መስከረም 21፣2018ዓ.ም (ኤፍኤም 90.)

‎በሆስፒታሉ የሚሰጠውን አገልግሎት የተሟላ፣ ጥራቱን የጠበቀና ቀልጣፋ በማድረግ የሆስፒታሉን ደረጃ ለማሳደግ ትኩረት ተሠጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተመላክቷል

‎ለረዥም ዓመታት ከአጥንት ጋር በተያያዘ ህክምና ለማግኘት ወደተለያዩ የህክምና ተቋማት የተመላለሱ ቢሆኑም ተገቢውን ህክምና ያለማግኘታቸውን በማስታወስ ከአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ባገኙት አገልግሎት መርካታቸውን የገለፁት ወ/ሮ ሽብሬ ከበደ ናቸው፡፡

‎የአጥንት ህክምና አገልግሎት በአርባምንጭ ሆስፒታል መጀመሩ በተለይ የኢኮኖሚ አቅም ውስንነት ላላቸው እፎይታ ከመፍጠሩም በተጨማሪ እንግልትና ወጪን እንዳስቀረላቸው ገልፀዋል፡፡

‎በህፃናት ተኝቶ ህክምና ክፍል ልጃቸውን እያስታመሙ የነበሩትን አቶ ኃይሉ ታደሰ ሆስፒታሉ የሚሰጠው አገልግሎት የተሻለ መሆኑን ጠቁመው አልፎ አልፎ የመድኃኒት እጥረት እንደሚስተዋል ጠቁመዋል፡፡

‎ከወላድ ክፍል አግኝተን ያነጋገርናቸው ወ/ሮ ዘላለም ገበየሁ በበኩላቸው አገልግሎት አሠጣጡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ በመምጣቱ መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡
‎ዶ/ር በረከትአብ ከበደ በፅኑ ህሙማን ክፍል ጠቅላላ ሐኪም ሲሆኑ ጥራትን የጠበቀና የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት የተለያዩ ፕሮግራሞችን ተግባራዊ እያደረጉ መሆናቸውን ገልፀዋል።

‎ከ4 ሚሊዮን በላይ ለሚሆን የህብረተሰብ ክፍል የሚሰጠውን አገልግሎት የተሟላ፣ ጥራቱን የጠበቀና ቀልጣፋ በማድረግ የሆስፒታሉን ደረጃ ለማሳደግ ትኩረት ተሠጥቶ እየተሰራ መሆኑን የገለፁት የሆስፒታሉ ሥራ-አስኪያጅ ዶ/ር አምባቸው ዱማ ናቸው፡፡

‎ አክለውም በሆስፒታሉ ቀደም ሲል ተጀምረው የተቋረጡ አገልግሎቶችን የማስቀጠል፣ አዳዲሶቹን የማስጀመርና የማዘመን ሥራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

‎ዘጋቢ:- ተነሳ ተረፈ

የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ውስጣዊ አንድነትን ማጠናከር ይገባል -አቶ ዱፄ ታምሩአርባምንጭ፡መስከረም 21፣2018ዓ.ም(ኤፍኤም 90.9)በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል '' የታደሰ ጂኦስትራቴ...
01/10/2025

የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ውስጣዊ አንድነትን ማጠናከር ይገባል -አቶ ዱፄ ታምሩ

አርባምንጭ፡መስከረም 21፣2018ዓ.ም(ኤፍኤም 90.9)

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል '' የታደሰ ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመና፣ በሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ትጋት!” በሚል መሪ ቃል ለአመራሩና ለመንግሥት ሰራተኞች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል ።

በወቅቱ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ፤የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤተ ኃላፊ አቶ ዱፄ ታምሩ፣ሀገር የጋራ ናት ብለዋል። ።

የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ውስጣዊ አንድነትን ማጠናከር እንደሚገባ የገለፁት አቶ ዱፄ፣ለዚህም የጋራ ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል ።

የሀገር ብልጽግና የሚረጋገጠው መላው የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በሁለንተናዊ መንገድ ለማስከበር በአንድነት ሲረባረቡ ነው ብለዋል።

በወቅቱ ከጂኦ-ስትራቴጂያዊ ኩስመና ወደ ታደሰ ቁመና'' በሚል ሃሳብ ያጠነጠነ ሰነድ ያቀረቡት ደግሞ የርዕሰ መስተዳድሩ ፕሮቶኮልና የመንግስታት ግንኙነት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ባህሩ ሙላት ናቸው ።

አቶ ባህሩ በዚህ ጽሁፋቸው እንዳመለከቱት፥መንግስት የኢትዮጵያን ብልፅግና በሁለንተናዊ መንገድ ለማረጋገጥ በሁሉም መስክ ትኩረት ሰጥቶት እየሰራ እንደሚገኝ አንስተዋል።

አንደ ክልልሉ ኮሚዩኒኬሽን ዘገባ ጂኦ-ስትራቴጂያዊ ኩስመና ወደ ታደሰ ቁመና'' በሚል ለአመራሩና ለመንግሥት ሰራተኞች እየተሰጠው ባለው ስልጠና ፣የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት እና የአቅም ግንባታና ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ሠራተኞችና የስራ ሀላፊዎች " ይገኙበታል ።

የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃቤታዊ አገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን ወደ ስራ መግባቱን ገለጸ‎‎አርባምንጭ፡መስከረም20፣2018ዓ.ም(ኤፍኤም 90.9)‎‎የአገልግሎቱ መጀመር ብልሹ አሰራርን...
30/09/2025

የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃቤታዊ አገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን ወደ ስራ መግባቱን ገለጸ

‎አርባምንጭ፡መስከረም20፣2018ዓ.ም(ኤፍኤም 90.9)

‎የአገልግሎቱ መጀመር ብልሹ አሰራርን እና የተገልጋዮችን እንግልት በመቅረፍ የማዘጋጃ ቤታዊ ገቢን አሟጦ በማባሰብ ተጨማሪ አቅም ይፈጥራልም ተብሏል።

‎ኢትዮጵያ በያዘችው የተቋማት ሪፎርም ስራ ለዘመናት በአገልግሎት አሰጣጥ ዘርፍ የተከማቹ እና የተደራረቡ ብልሹ አሰራሮችን እየፈታች ትገኛለች።

‎በደቡብ ኢትዮጵያ ክልልም አሰራሮችን በማዘመን ቀልጣፋና ወጪ ቆጣቢ እየተደረገ ይገኛል ።

‎የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳደር እና የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አበባየሁ የታደሰ ማዘጋጃዎች የሮሮ ማእከል መሆናቸውን ለማስቀረት አገልግሎት የማዘመን ስራ መጀመሩ መሰረታዊ የአገልግሎት ስብራትን ይጠግናል።

‎አክለውም የማዘጋጃ አመራር በመገምገም እና በማባረር ብቻ ስር ሰዶ የቆየውን የአገልግሎት ችግር መቅረፍ አይቻልም ብለው ከተሞች የብልጽግና ስበት ማእከል በመሆናቸው ከኋላ ቀር አሰራር ሊወጡ ይገባል።

‎ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ፤ የማዘጋጃ ቤት አገልግሎትን ማዘመን ህዝቡ በአመራሩና በባለሞያው ላይ ለሚያነሳው ቅሬታ መፍቻ ቁልፍ ነው ብለዋል።

‎አሰራሩ ማዘጋጃም እንደሌሎች ተቋም ወደ ሚመሰገንበት ደረጃ የሚያደርሰው መሆኑን ጠቅሰው በፈርጅ አንድ፤ሁለት እና ሶስት የሚገኙ ከተሞች አቅማቸውን አሰባስበው ወደ ስራ እንዲገቡ አሳስበዋል።

‎የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶ/ር መስፍን መንዛ ፤ የአርባምንጭ ከተማ ማዘጋጃቤታዊ አገልግሎትን ማዘመን የከንቲባ ስራን በግማሽ ይቀንሳል ብለዋል።

‎የቴክኖሎጂው መዘመን ብልሹ አሰራርን በመቅረፍ የማዘጋጃ ቤታዊ ገቢን አሟጦ ለማሰብ ተጨማሪ አቅም ይፈጥራል ብለዋል።

‎የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገዳሙ ሻምበል ፤ ማዘጋጃው ይፋ ያደረገው አገልግሎት የማዘመን ስራ ዜጎች የተሟላ የዲጂታል አማራጮችን በመጠቀም ባሉበት ሆነው በቀላሉ ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል።

‎ ኃላፊው አክለውም ማንኛውም የተቋሙ ባለጉዳዮች የሚያደርጉትን ያልተገባ ምልልስ፣ ረጅም የወረፋ ጥበቃ እና ከወረቀት ጋር ተዛማጅ የሆኑ ስራዎችን ለማስቀረት የሚያግዝ አሰራር ተቋሙ መዘርጋቱ ስር ነቀል ለውጥ ውስጥ ስለመግባቱ ማሳያ ነው ብለዋል።

‎በመድረኩ የተገኙት በጋሞ ዞን የሚገኙ 7 የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች የማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጆች እና የመንግስት ዋና ተጠሪዎች ባላቸው አቅም ማዘጋጃቸውን እንዲያዘምኑ መልእክት ተላልፏል።

‎ ተሳታፊዎችም የአርባምንጭ ከተማ ማዘጋጃ የደረሰበትን ደረጃ አድንቀዋል።

‎ዘጋቢ ፡ አሰግድ ተረፈ

የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃቤታዊ አገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን ወደ ስራ መግባቱን ገለጸአርባምንጭ ፡መስከረም 20፣2018ዓ.ም(ኤፍኤም 90.9)ማዘጋጃ ቤቱ ከወረቀት ንኪኪ ነጻ የሆነ...
30/09/2025

የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃቤታዊ አገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን ወደ ስራ መግባቱን ገለጸ

አርባምንጭ ፡መስከረም 20፣2018ዓ.ም(ኤፍኤም 90.9)

ማዘጋጃ ቤቱ ከወረቀት ንኪኪ ነጻ የሆነ የቀጥታ
አገልግሎት መስጠት መጀመሩ የተገልጋዮችን እንግልት በተጨባጭ ይቀርፋል ተብሏል።

ማዘጋጃው አገልግሎት የማዘመን ስራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩን በማከናወን ላይ ይገኛል።

ኢትዮጵያ በያዘችው የተቋማት ሪፎርም ስራ ለዘመናት በአገልግሎት አሰጣጥ ዘርፍ የተከማቹ እና የተደራረቡ ብልሹ አሰራሮችን እየቀረፈች ትገኛለች።

የአሰራር ስርዓቱ ዜጎች የተሟላ የዲጂታል አማራጮችን በመጠቀም ባሉበት ሆነው በቀላሉ ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል።

የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃቤታዊ አገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን ወደ ስራ መግባቱ ከዚህ ቀደም ይስተዋሉ የነበሩ አሰራሮችን ያዘምናል ተብሎ ይጠበቃል ።

ዘጋቢ ፡ አሰግድ ተረፈ

‎የመብራት አገልግሎት ቀደም ሲል ከነበረው የተሻለ ቢሆንም የሀይል እጥረት በመኖሩ ምክንያት ሥራቸውን ማስፋፋት አለመቻላቸውን በዋጫ ከተማ የሚገኙ አንዳንድ ማህበራት ተናገሩ ‎‎አርባምንጭ፡መስ...
30/09/2025

‎የመብራት አገልግሎት ቀደም ሲል ከነበረው የተሻለ ቢሆንም የሀይል እጥረት በመኖሩ ምክንያት ሥራቸውን ማስፋፋት አለመቻላቸውን በዋጫ ከተማ የሚገኙ አንዳንድ ማህበራት ተናገሩ

‎አርባምንጭ፡መስከረም20፣2018ዓ.ም(ኤፍኤም 90.9)

‎የወረዳው አስተዳደር ለችግሩ መፍትሔ ለማበጀት የሚሰራ መሆኑን ጠቁሟል።

‎ የዋጫ ከተማ ነዋሪዎች መካከል አቶ ዲልያስ ዲራቶ እና አምባቸው አንጁሎ ፤ በእንጨትና ብረታ ብረት ሥራ የሚተዳደሩ ሲሆን ከዚህ ቀደም የመብራት መቆራረጥ በሥራቸው ላይ ጫና በመፍጠሩ ከደንበኞች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ሲያደበዝዝ መቆየቱን አውስተው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መሻሻሎች መኖራቸውን ተናግረዋል።

‎ሆኖም በኃይል እጥረት በመኖሩ ሥራቸውን ለማስፋፋት አለመቻላቸውን አስተያየት ሰጪዎቹ አክለዋል።

‎የዋጫ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አልማዝ አባይነህ ፤ በከተማዋ የመብራት ተደራሽነት ለማስፋፋትና ማህበራት ያነሱትን የኃይል እጥረት ለመቅረፍ እንደ ከተማ አስተዳደር ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

‎የዳራማሎ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጥሞቴዎስ ጥላሁን ፤ ለቴክኖሎጂ ሽግግርና ለሥራ ዕድል ፈጠራ የመብራት ተደራሽነትና አገልግሎት ወሳኝ ቢሆንም በወረዳው የመብራት ተደራሽነት ዝቅተኛ መሆኑን አንስተዋል።

‎የወረዳው አስተዳደር በቀጣይ ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ህብረተሰቡ መብራትን አስመልክቶ ለሚያሳቸው ጥያቄዎች እልባት ለመስጠት በትኩረት የሚሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

‎አክለውም የመሠረተ ልማት ሥራዎችን በሚፈለጉት ልክ ማሟላት እንዲቻል ህበረተሰቡም የበኩሉን አስተዋፅኦ በማድረግ እንዲተባበር አሳስበዋል።

‎ዘጋቢ ፡ አስናቀ ካንኮ

Address

ARBAMINCH
Arba Mintch
0979711926

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Arba Minch FM 90.9 / አርባ ምንጭ ኤፍ ኤም 90.9 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share