Arba Minch City

Arba Minch City This is the official page of arba minch city page

ሰበር !የወረዱት ክለቦች ክስ ለመመስረት መዘጋጀታቸውን አሁን መረጃ ደርሶኛል። መቐለ 70 እንደርታ ፣ አርባምንጭ ከነማ፣ ምድረ ገነት ሽረ እና ድሬዳዋ ከተማ ..ሊግ አክሲዮን ማህበሩ ..ፍት...
31/07/2026

ሰበር !

የወረዱት ክለቦች ክስ ለመመስረት መዘጋጀታቸውን አሁን መረጃ ደርሶኛል።

መቐለ 70 እንደርታ ፣ አርባምንጭ ከነማ፣ ምድረ ገነት ሽረ እና ድሬዳዋ ከተማ ..ሊግ አክሲዮን ማህበሩ ..ፍትሀዊ ባልሆነ መንገድ አወዳድሮናል ህጉን ስላከበርን .. እንድንወርድ ተገደናል ..የዛሬ የአክሲዮን ማህበሩ ውሳኔ ማረጋገጫ ነው ለእኛ ክለቦቹ .ብለው እንደሚያምኑ ያነጋገርኳቸው አሰልጣኞች እና የክለብ አመራሮች ተናግረዋል።

የሊግ አክሲዮን ማህበሩ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ጥላ ስር የሚሰራ በመሆኑ፣ ክለቦች ቅሬታቸውን ለፌዴሬሽን እንደሚያቀርቡ እና ከሊጉ መውረዳቸው እንዲቀርላቸው ይጠይቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። 👀

ጋዜጠኛ አብይ ዘላለም

ታዳጊ ኤልሳቤት ደስታ አዲስ አበባ ከገባች በኋላ በታወቀችው የሜክአፕ አርቲስት "Touch by Marzel" የተደረገላት ልዩ የውበት እንክብካቤና ሜክአፕ ድምቅ አድርጓታል።
31/07/2026

ታዳጊ ኤልሳቤት ደስታ አዲስ አበባ ከገባች በኋላ በታወቀችው የሜክአፕ አርቲስት "Touch by Marzel" የተደረገላት ልዩ የውበት እንክብካቤና ሜክአፕ ድምቅ አድርጓታል።

በአርባምንጭ ከተማ ዛሬ ሐምሌ 24 የደረሰ ጉዳት አሽከርካሪዮች በዝግታ እና በማስተዋል አታሽከርክሩ ይህ አይነቱ ጉዳት በከተማ ምክር ቤት በፀደቀው ደንብ መሰረት  #ከ1ሚሊዮን ብር በላይ ቅጣ...
31/07/2026

በአርባምንጭ ከተማ ዛሬ ሐምሌ 24 የደረሰ ጉዳት

አሽከርካሪዮች በዝግታ እና በማስተዋል አታሽከርክሩ ይህ አይነቱ ጉዳት በከተማ ምክር ቤት በፀደቀው ደንብ መሰረት #ከ1ሚሊዮን ብር በላይ ቅጣት አለው

~ ሐምሌ 24/2018

Via Yishak Abraham

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ  7ኛውን ዙር ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. አከናውኖ ውጤቱን ለሕዝብ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። ይሁንና በ11 ምርጫ ክልሎች የምርጫ ውጤት ሊያዛ...
31/07/2026

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ኛውን ዙር ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. አከናውኖ ውጤቱን ለሕዝብ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። ይሁንና በ11 ምርጫ ክልሎች የምርጫ ውጤት ሊያዛባ የሚችል ጉልህ የሆነ የምርጫ ሕግ ጥሠት መፈጸሙ በማስረጃ ስለተረጋገጠ ድጋሚ ምርጫ እንዲካሄድ መወሠኑም እንዲሁ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሠረት ቀደም ሲል በ11 ምርጫ ክልሎች የ7ኛው ዙር ምርጫ ላይ ያልተሣተፉ አዲስ አስፈጻሚዎችን ገለልተኝነታቸውንና መሥፈርቱን ማማላታቸውን አረጋግጦ በጊዜያዊነት ለመቅጠር ይፈልጋል።

በመሆኑም መሥፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች የተያያዘውን ማስፈንጠሪያ https://nebe election.org/recruitment በመጠቀም ከዛሬ ሐምሌ 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት እንድታመለክቱ ቦርዱ ያሳውቃል።

የምልመላ መሥፈርት፡-
• ዕድሜው/ዋ ከ18 ዓመት በላይ የሆነ/ች፣
• የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ች፣
• የትምህርት ዝግጅት፦ 12ኛ እና ከዚያ በላይ የሆነ/ች፣
• የሥራ ቦታ፦ ቦርዱ ባቋቋማቸው የምርጫ ጣቢያዎች፣
• የክልሉን የሥራ ቋንቋ መናገር እና መጻፍ የሚችል/ምትችል፣ •
(ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ)

የምርጫ ክልሎቹ ዝርዝር
1. ኦሮሚያ (ባቱ ዝዋይ)
2. ሶማሌ (ደራ ቶሌ)
3. ሶማሌ (ሀርገሌ)
4. ሶማሌ (ዳሮር)
5. ሶማሌ (ሀዲጋላ)
6. ሶማሌ (አዋሬ)
7. ሲዳማ (አሮሬሳ)
8. አሮሚያ (ቤጊ)
9. ማዕከላዊ ኢትዮጵያ (ጠምባሮ)
10. ማዕከላዊ ኢትዮጵያ (ሶሮ 1)
11. ደቡብ ኢትዮጵያ (ጨንቻ)

አዲስ የመንገድ ግብር ...?!በመንግሥት በተገነቡ መንገዶች ላይ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ላይ አዲስ ዓመታዊ የመንገድ ግብር ለመተግበር የሕግ ረቂቅ እየተዘጋጀ መሆኑ ተነግሯል።እንደ ኢትዮ ...
31/07/2026

አዲስ የመንገድ ግብር ...?!

በመንግሥት በተገነቡ መንገዶች ላይ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ላይ አዲስ ዓመታዊ የመንገድ ግብር ለመተግበር የሕግ ረቂቅ እየተዘጋጀ መሆኑ ተነግሯል።

እንደ ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘገባ፣ ግብሩ ከተሽከርካሪዎች ዓመታዊ ቴክኒካል ምርመራ (ቦሎ) ጋር ተያይዞ የሚሰበሰብ ሲሆን፣ የሚከፈለው መጠንም እንደ ተሽከርካሪው ዓይነት፣ ዕድሜ እና የካርቦን ልቀት መጠን ይወሰናል ተብሏል።

በዚህ መሠረት ከፍተኛ የካርቦን ጭስ የሚያመነጩ አሮጌ ተሽከርካሪዎች ከፍተኛ ግብር ሊከፍሉ ሲችሉ፣ አዳዲስና ዝቅተኛ የካርቦን ልቀት ያላቸው ተሽከርካሪዎች ደግሞ ዝቅተኛ ክፍያ እንዲፈጽሙ ይጠበቃል።

ዘገባው እንደሚያስረዳው፣ ይህ አሰራር በበርካታ አገራት ተግባራዊ ሲሆን፣ ለመንገድ ጥገናና ልማት ተጨማሪ የገቢ ምንጭ በመፍጠር የመንገድ መሠረተ ልማትን ለማጠናከር ያግዛል።

በተጨማሪም ግብሩ በፌዴራል፣ በክልሎች እና በከተማ አስተዳደሮች ደረጃ እንዲሰበሰብ በማድረግ የአካባቢ አስተዳደሮችን የበጀት አቅም ለማጠናከር እንደሚያስችል ተገልጿል።

ሆኖም የግብሩ መጠን፣ የአፈጻጸም ዝርዝር እና የሚጀምርበት ቀን ገና በይፋ አልተገለጸም፤ የሕግ ረቂቁ የሕግ አውጪ ሂደቱን ካጠናቀቀ በኋላ ይፋዊ መረጃ እንደሚቀርብ ይጠበቃል።

በትምህርት ዘርፍ የተሰማሩ ተቋማት የትምህርት ጥራትና ፍትሃዊነት እንዲረጋገጥ ህጋዊ መመሪያንና ወጥነት ያለው የአሰራር ስርዓትን ሊከተሉ እንደሚገባ ተጠቆመየአርባ ምንጭ ከተማ ትምህርት መምሪያ...
30/07/2026

በትምህርት ዘርፍ የተሰማሩ ተቋማት የትምህርት ጥራትና ፍትሃዊነት እንዲረጋገጥ ህጋዊ መመሪያንና ወጥነት ያለው የአሰራር ስርዓትን ሊከተሉ እንደሚገባ ተጠቆመ

የአርባ ምንጭ ከተማ ትምህርት መምሪያ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ምዝገባን እና የትምህርት ክፍያን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
*****
አርባምንጭ፥ ሐምሌ 23/ 2018 ዓ፣ም (አርባምንጭ ከተማ መ/ኮሚኒኬሽን አገልግሎት)

የከተማው ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አብርሐም አምሳሉ ለአገልግሎታችን በላኩት መግለጫ በውስን የግል ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ምዝገባና የትምህርት ወርሃዊ ክፍያ ሂደት የትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የትምህርት ቤቶች ፈቃድ አሰጣጥ እና እድሳት መመሪያ ቁጥር 992/2016 ህጋዊ አሰራርን ያልተከተለ እንደሆነ ገልፀዋል።

መመሪያው በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የተሰማሩ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ወጥነት ባለው የአሰራር ስርዓት እንዲመሩ፣ የትምህርት ጥራትና ፍትሃዊነት እንዲረጋገጥ እንዲሁም የተማሪዎችና የወላጆች መብት እንዲጠበቅ ግልጽ ድንጋጌዎችን የያዘ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተገለፀው መመሪያ አንቀጽ 11 ንኡስ አንቀጽ 1 መሠረት የመመዝገቢያ ክፍያ ከወርሃዊ ክፍያ 25% መብለጥ የሌለበትና አስቀድሞ ለተቆጣጣሪው መስሪያ ቤት ቀርቦ ይሁንታ ማግኘት የሚገባው ሲሆን፤ በአንቀጽ 11 ንኡስ አንቀጽ 3 እና 4 መሠረት ደግሞ ለማንኛውም የክፍያ ጭማሪ ከትምህርት ዘመኑ መጠናቀቅ 3 ወራት ቀደም ብሎ ለወላጆች ማሳወቅ፣ ከወላጅ ኮሚቴና ቢያንስ ከ51% ወላጆች ጋር ተወያይቶ በቃለ ጉባኤ ማጽደቅ እና ለመምሪያው ማሳወቅ ግዴታ ሆኖ መደንገጉን አብራርተዋል።

አክለውም የትምህርት መምሪያው በከተማዋ ባካሄደው ጥናት መሠረትም አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች በቂ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ሳይኖር እንዲሁም የምዝገባና የክፍያ ተመናቸውን እንዲሁም ማሻሻያ ለማድረግ አስቀድሞ ለመምሪያው ጥያቄ ሳይቀርቡ መመሪያ ቁጥር 992/2016 አንቀጽ 11 የተቀመጡትን ህጋዊ መስፈርቶች ሳይከተሉ እየሰሩ እንደቆዩ አውስተዋል።

የትምህርት መምሪያው እየተሰዋለ ያለውን ህገ-ወጥ አሰራሮች ለማረም፤ የተማሪዎችንና የወላጆችን መብት ለማስከበር እና የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ምዝገባን በስርዓት ለመምራት እንዲቻል ይህንን የቅድመ ጥንቃቄና የእርምት ማስተካከያ መግለጫ ለመስጠት መገደዱን ለአገልግሎታችን በላኩት መረጃ ጠቅሰዋል።

በመግለጫው መሠረት በአርባምንጭ ከተማ ትምህርት መምሪያ ስር ተመዝግበው በትምህርት ዘርፍ በህጋዊ ፍቃድ እየሰሩ የሚገኙና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግል ትምህርት ቤቶች የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ምዝገባን እና የትምህርት ክፍያ የሚከተሉትን ሂደቶች ማሟላት እንዳለበት ተገልጿል።

በ2017 ዓ.ም ለ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የተደረገው የወርሃዊም ሆነ የመመዝገቢያ ክፍያ ጭማሪ ትክክል ባለመሆኑ፣ ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሚካሄደው ምዝገባና መማር ማስተማር በ2018 ዓ.ም ሲከፈል የነበረውን ክፍያ ያለምንም አይነት ተጨማሪ ጭማሪ ማስከፈል እንዳለባቸው ጠቅሷል።

በሌላ በኩል የምዝገባ ጊዜን አስመልክቶም ሁሉም መንግስታዊ ያልሆኑ ትምህርት ቤቶች የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ምዝገባን በትምህርት ካላንደሩ መሠረት ከነሐሴ 13/12/2018 ዓ.ም ጀምሮ ማካሄድ ይኖርባቸዋል። ከዚህ ቀን ቀድሞም ሆነ ከካላንደሩ ውጭ ምዝገባ ማካሄድ ፍጹም የተከለከለ እንደሆነም አሳውቋል።

በመግለጫው የተቀሱትን አሰራሮች ተላልፎ የተገኘ፤ ከታዘዘው በላይ የትምህርት ወይም የመመዝገቢያ ክፍያ የጠየቀ ወይም ከትምህርት ካላንደሩ ውጭ ምዝገባ ያካሄደ ማንኛውም መንግስታዊ ያልሆነ ትምህርት ቤት በመመሪያ ቁጥር 992 /2016 እንቀጽ 19 መሠረት የእውቅና ፈቃድ እስከ መሰረዝ የሚደርስ ጥብቅ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ጥብቅ ማሳሰቢያ እንደሆነም አፅንኦት ሰጥቷል።

ሁሉም መንግስታዊ ያልሆኑ ትምህርት ቤቶች ይህንን መመሪያ በጥብቅ በመተግበር ተማሪዎችን ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ እንዲመዘግቡና የወላጆችን እንግልት ማስቀረት እንደሚገባቸው የገለፀው መምሪያው የክረምት ወራት ሥራ ዕቅድ አፈፃፀምና የቀጣይ ትምህርት ዘመን ምዝገባ ጥቅል ሂደትን አስመልክቶ የድጋፍ ቡድን በየትምህርት ቤቶች በመገኘት ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል ሲል አስታውቋል።

በጌታ ፈቀደ

ሀገራችንን ወክላ  በቅርቡ በሚካሄደው የዓለም አቀፍ የቁንጅና ውድድር ለመወከል የምትዘጋጀው Miss Ethiopia (ሩት)፣ እጅግ ልብ በሚሰብር ሁኔታ እህቷን አጥታለች። የሟች እህቷ የቅርብ ...
30/07/2026

ሀገራችንን ወክላ በቅርቡ በሚካሄደው የዓለም አቀፍ የቁንጅና ውድድር ለመወከል የምትዘጋጀው Miss Ethiopia (ሩት)፣ እጅግ ልብ በሚሰብር ሁኔታ እህቷን አጥታለች።

የሟች እህቷ የቅርብ ጓደኛ በነበረችው አማካኝነት፣ አምና ቤቷ ድረስ ሄዳ እህቷን በአሰቃቂ ሁኔታ የተነጠቀችበት ይህ አጋጣሚ የሁላችንንም ልብ በሐዘን ሰብሮታል።

በዚህ በእጅጉ ከባድ እና መራራ ወቅት ሁላችንም ከሩት እና ከቤተሰቧ ጎን በመቆም አጋርነታችንን ልናሳያት ይገባል።

ፈጣሪ ለሩት እና ለቤተሰቧ መፅናናትን፣ ለሟች እህቷ ደግሞ ነፍሷን በገነት ያኑርልን።

🙏🙏🙏

📷ዘሀበሻ

ፖስተር ቸሬ 🙏

ጉርሻ page

በኢትዮጵያ የኤችአይቪ/ኤድስ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱ እና የኮንዶም ዕጥረት ማጋጠሙ ተገለጸ::በአገሪቱ ቫይረሱ በደማቸው የሚገኙ ሰዎች ቁጥር 700 ሺህ መድረሱ የተገለጸ ሲሆን...
30/07/2026

በኢትዮጵያ የኤችአይቪ/ኤድስ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱ እና የኮንዶም ዕጥረት ማጋጠሙ ተገለጸ::

በአገሪቱ ቫይረሱ በደማቸው የሚገኙ ሰዎች ቁጥር 700 ሺህ መድረሱ የተገለጸ ሲሆን፣ በተለይም ዕድሜያቸው ከ14 እስከ 24 የሆኑ ወጣት ሴቶች እና የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለከፍተኛ ተጋላጭነት መዳረጋቸው ተጠቁሟል።

የኔትወርክ ኦፍ ኔትወርክስ ኦፍ ኤች.አይ.ቪ ፖዘቲቭስ ኢን ኢትዮጵያ (ኔፕ ፕላስ) በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው፣ አሁን ላይ በአገሪቱ ከፍተኛ የኮንዶም ዕጥረት የተከሰተ ሲሆን የኤችአይቪ/ኤድስ ስርጭትም በስጋት ደረጃ እየጨመረ ይገኛል።

1. በአገሪቱ ከግማሽ ሚሊየን በላይ፣ በአሁኑ ወቅት ደግሞ እስከ 700 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው ይገኛል።

2. ቫይረሱ በደማቸው ከሚገኙ ሰዎች መካከል 36 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው። በተለይም ከ14-24 የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወጣት ሴቶች እና የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለስርጭቱ በከፍተኛ ሁኔታ የተጋለጡ ናቸው።

3. በአገሪቱ ያለው ከፍተኛ የኮንዶም ዕጥረት ለስርጭቱ መጨመር ተጨማሪ ስጋት ደቅኗል።

ምስረታው 22 ዓመታትን ለማስቆጠር የተቃረበውና ከ500 በላይ ማህበራትን በስሩ ያቀፈው ኔፕ ፕላስ፣ በሚቀጥለው ወር 21ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እንደሚያካሂድ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ታደሰ አስታውቀዋል።

ይህ ጉባዔ በአሁኑ ወቅት ትኩረት በማጣቱ እየተዘነጋ የመጣውን፣ ነገር ግን አሁንም የብዙዎችን ህይወት እየቀጠፈ የሚገኘውን የኤችአይቪ ህመም አስመልክቶ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች የሚሰሩበት ይሆናል።

በተጨማሪም ድርጅቱ ከዚህ ቀደም ሁለት ጊዜ ያካሄደውን "Stigma index research" ጥናት ተከትሎ፣ አሁን ላይ ሶስተኛውን ዙር ጥናት እያካሄደ እንደሚገኝ አስታውቋል።

በሚቀጥለው ወር በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ከኔፕ ፕላስ አባል ማህበራት የተወከሉ 120 ያህል እንግዶች ይሳተፋሉ።

Via Ethio FM
ዘገባ፦ እስከዳር ግርማ
ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም

‎አንዲት እናት 6 ነጥብ 4 ኪ.ግ የምትመዝን ህጻን በሰላም ተገላገለች‎‎  ~ ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም ‎በቤንች ሸኮ ዞን አንዲት እናት 6 ነጥብ 4 ኪ.ግ የምትመዝን ህጻን በሰላም ተገላግላ...
30/07/2026

‎አንዲት እናት 6 ነጥብ 4 ኪ.ግ የምትመዝን ህጻን በሰላም ተገላገለች

‎ ~ ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም
‎በቤንች ሸኮ ዞን አንዲት እናት 6 ነጥብ 4 ኪ.ግ የምትመዝን ህጻን በሰላም ተገላግላለች።

‎በዞኑ የአማን ሻሸቃ ቀበሌ ነዋሪ የሆነችው ወ/ሮ ሳይሉሽ ባህሩ በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች በተደረገላት ክትትል ህጻኑን በቀዶ ህክምና መገላገሏን በሆስፒታሉ የማህጸንና ጽንስ ስፔሻሊስቱ ዶ/ር ቹቹ አረጋ ገልጸዋል።

‎ወ/ሮ ሳይሉሽ ባህሩ በተመሳሳይ ከ6 ዓመት በፊት 2ኛ ልጇን ስትወልድ 5 ኪ.ግ መሆኑንና በቀዶ ጥገና ህክምና እንደተገላገለች ገልጻለች።
Via ፋና

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የተጫዋቾች የክፍያ ህግ ተነሳ   ~ ሐምሌ 23/2018 ዓ/ም በካፒታል ሆቴል የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ 9ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ። በዛሬው የጉባኤ...
30/07/2026

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የተጫዋቾች የክፍያ ህግ ተነሳ

~ ሐምሌ 23/2018 ዓ/ም

በካፒታል ሆቴል የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ 9ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ።
በዛሬው የጉባኤ ውሎ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ የክፍያ ስርዓት መመሪያ ዝግጅት እና ትግበራ ሂደት ከመድረኩ እና ከጉባኤው ተሳታፊዎች በዝርዝር ቀርቧል።

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ ክፍያ ስርዓት መመሪያ መሰረት በ2019 አተገባበር ላይ የጉባኤው አባላት በጥልቀት ከተወያዩ በኋላ ለአፈፃፀም አስቸጋሪ መሆኑን፣ የመንግስት ድጋፍ እንደሚሻ እና ክለቦች በቃል ደረጃ ከመስማማት ውጪ በወጥነት እየተገበሩት እንዳልሆነ ተነስቷል።

በስተመጨረሻም ሁሉም ክለቦች አቋማቸውን እና አማራጮች ያቀረቡ ሲሆን የክለቦች ክፍያ ስርዓት መመሪያው አሁን ባለው ሁኔታ ለ2019 ዓ.ም እንዳይተገበር በድምፅ ብልጫ ተወስኗል ሲል ሃገሬ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

Address

Arba Mintch

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Arba Minch City posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share