27/05/2026
ከአፋር በረሀ እስከ መካ የደረሰችው ጫማ ስንቱን ሚሊኒየር ፣ ስንቱን ዝነኛ ስንቱን ባለስልጣን እንደበለጠችው አስቡት፣
ነብዮ መሀመድ (ሰአወ) ሁሉም የሰው ልጆች እኩል ናቸው እሚበላለጡት አላህን በመፍራት ብቻ ነው አሉ። ሰርግ ለመሄድ መዘነጥ የግድ ነው። ድግስም ይሁን ስብሰባ ወይም አሉባሌ ቦታ ሁሉ ለመሄድ
ብዙ ሺ ተወቶ ይለበሳል። የአላህ ቤት ለመሄድ ግን መዘነጥ መንጠባረር መሽሞንሞን አያስፈልግ ባለህ ተብቃቅተህ መሄድ ትችላለህ። ይች ጫማም ሂያው ምስክር ናት። በሀብት የምኮሩ በስልጣን የምትንቀባረሩ ሰዎች የሰውን ልጅ እምበድሉ ከዚህ ከአፋር አባት አርብቶ አደር ማንነት ወስዳችሁ እራሳችሁን ፈትሹ። እኛንም አላህ ይፈቀን ያረብ፣ ልባችንን አላህ ያራራልን 🤲