
14/04/2025
በአማራ ህዝብ ስም እንታገላለን የሚሉ የሰፈር አለቆች በጥቅም እና በስልጣን ጥማት እርስ በእርስ የተባሉ ይገኛሉ። ይህ የጽንፈኛዉ ቡድን ገና ከጅምሩ በሶስት ተከፍሎ የተመሰረተ ሲሆን፤ አሁን ስንጥቁ ሰፍቶ እርስ በእርሱ ጦር የሚዘማመት፤ እርስ በእርስ በሴራ የሚተላለቅ መሆኑ የአደባባይ ሚስጢር ከሆነ ቆየ።
ከሰሞኑ ደሞ ሌላ የዚህን ቡድን ልዩነት የሚያሰፋ በአማራ ህዝብም ላይ ትልቅ መከራን ሊያመጣ የሚችል ክስተት ተፈጥሯል።
በዚህ ክስተት ምክኒያት የዚህ ጽንፈኛ ቡድን #ልዩነቶችን እየሳፋ የመጣበት ምክንያት ከህወሓት ጋር እንሰራለም አንሰራም በሚለዉ ሲሆን ይህም ልዩነት በከፍተኛ ሁኔታ ሰፍቶ አመራሮችን ማሳደድ የጀመሩበት ደረጃ ደርሰዋል።
ባሳለፍነዉ ሳምንትም በደቡብ ጎንደር ሲንቀሳቀስ የነበረውን በፋኖ ከፍያለው ደሴ የሚመራውን ቡድን የዘመነ ካሴ ታጣቂዎች እራሱን ፋኖ ከፍያለው ደሴን ጨምሮ መደምሰሳቸዉ የዚህ ክፍፍል አንዱ መዘዝ ነዉ።