04/07/2025
#ዓሹራ
☑️ ከረመዷን ቀጥሎ ከጾሞች ሁሉ በላጩ የአላህ ወር የሆነው አሁን ያለንበት የሙሐረም ወር ነው። ከሙሐረም ወር ውስጥ 10ኛው የዓሹራ ቀን መጾም ያለፈውን አንድ አመት ወንጀል ያስምራል። የሚውለውም ነገ ቅዳሜ ነው።
⚠️ የአላህ ባሮች ሆይ! ዛሬ እንደ ዋዛ የምናሳልፋቸው ቀኖች ነገ ላይገኙ ይችላሉና እንዲህ በትንሽ ስራ የሚገኙ ትልቅ ምንዳዎችን አንለፍ
🗓️ ለዛሬ ስለ ዓሹራ ፆም እናኛለን፡-
ሁሌም ቢሆን ስለ ዲናችን ወቅቱን የጠበቀ ትኩረት ሊኖረን ይገባል። በሐጅ ወቅት ስለሐጅ፣ ወዘተ ብናተኩርና ብንማማር በዚያ ጉዳይ የበለጠ እንድንጠቀም ያደርገናል
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
📗 አቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፈልን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡-
"ከረመዷን ቀጥሎ ከጾሞች ሁሉ በላጩ የአላህ ወር የሆነው ሙሐረም ነው"። (ሙስሊም 2812)
☑️ ከሙሐረም ወር ውስጥ ደግሞ 10ኛው ቀን በላጭ ቀን ነው፣ ይህ 10ኛው ቀን "ዓሹራ” ይባላል። በዚህ ቀን መጾሙ ያለው ምንዳ ያለፈውን አንድ አመት ወንጀል ያስምራል።
📗አቢ ቀታዳህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፉት፣ የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡-
"የዓሹራ ቀን መጾም ያለፈውን አንድ አመት ወንጀል ከአላህ ያስተሰርያል"። (ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 7, ሐዲስ 1810)
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
📗በሌላ ሀዲስ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- “የአሹራ ቀን ፆም ያለፈውን አመት ኃጢአት እንደሚያብስ ከአላህ እጠብቃለሁ።” (ሙስሊም ዘግበውታል: 1162)
☑️ ዓሹራን መጾም ያለፈውን ዓመት ወንጀል እንደሚያሠርዝ ተጠቅሷል። ይህ ምህረት ጥቃቅን ወንጀሎችን ነው የሚመለከተው ወይስ ከበባዶችንም ጭምር የሚለውን አስመልክተው ኢማም አንነወዊይ የሚከተለውን ብለዋል:-
💬 "የዓረፋ ጾምም ይሁን የዓሹራ ሌሎችም ወንጀልን ያስምራሉ የተባሉ ኢባዳዎች ጥቃቅን የሚባሉ ወንጀሎችን በሙሉ ያሰርዛሉ ጥቃቅን ወንጀሎች የሌሉበት እንደሆነ በምትኩ መልካም ስራዎች ይመዘገቡለታል አላህ ዘንድም ያለው ደረጃ ይጨምራል ጥቃቅን ወንጀሎች የሌሉበት ሆኖ አንድ ወይም ከዛ በላይ ከባድ ወንጀል ያለበት እንደሆነ ወንጀሉን ያቀለዋል ብለን አሏህ ላይ ተስፋ እናደርጋለን”።
📗አቢ ቀታዳህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተናገረው፣ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "የዐረፋ ቀን ጾም አላህ ዘንድ ያለፈውንና የሚመጣውን (የሁለት) ዓመት (ትናንሽ) ኃጢአቶችን ያስምራል፣ የዐሹራእ ቀን ጾም ደግሞ ያለፈውን አንድ ዓመት (ትናንሽ) ኃጢአት ያስምራል" (ሙስሊም 1976)
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
☑️ ዓሹራ ፆም የሚጾምበት ምክንያት፡-
📗ዐብደላህ ኢብኑ-ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ አሉ፡-
"የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወደ መዲና ሲገቡ አይሁዶችን በዐሹራእ ቀን ሲጾሙ አገኟቸው፡፡ ይህን ቀን የምትጾሙት ለምንድነው? ብለው ሲጠይቋቸው እነሱም፡-
ይህ ታላቅ ቀን ነው! አላህ ሙሳንና ተከታዮቹን ከፊርዐውንና ሰራዊቱ በማዳን እነሱን በባሕር ያሰጠመበት ቀን ስለሆነ ሙሳም ለአላህ ምስጋናን ለማድረስ ጾሞታል እኛም እንጾመዋለን ብለው መለሱ፡፡
የአላህ መልክተኛውም (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)፡- ለሙሳ (ወዳጅነት) ከናንተ ይልቅ እኛ የቀረብንና የተገባን ሰዎች ነን እኮ! በማለት እሳቸውም ጾሙት ሶሓባዎቻቸውንም እንዲጾሙ አዘዙ”። (ሙስሊም 2714)
ነብዩ (ﷺ) ወደ መዲና ከመሄዳቸው በፊት በመካ ዓሹራን ይጾሙ ነበር። ወደ መዲና በተሰደዱ ጊዜ አይሁ