Husamedin issa "ሁሳመዲን ኢሳ"

Husamedin issa "ሁሳመዲን ኢሳ" Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Husamedin issa "ሁሳመዲን ኢሳ", Digital creator, Asosa.

አሽቃባጭ ሳይሆን ጠያቂ   ለሆነ ለኔ አይነቱ ትዉልድ                                    ፣፣እንቢ ማለት እብሪት ሳይሆን   መርሀዊ አቋም ነዉ!!
16/09/2025

አሽቃባጭ ሳይሆን ጠያቂ ለሆነ ለኔ አይነቱ ትዉልድ
፣፣
እንቢ ማለት እብሪት ሳይሆን መርሀዊ አቋም ነዉ!!







በመተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ተካሄደ።በግልገል በለስ ከተማ በተካሄደው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክ...
14/09/2025

በመተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ተካሄደ።

በግልገል በለስ ከተማ በተካሄደው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክርቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ መለሰ ኪዊ፣ የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አትንኩት ሽቱ፣ የግልገል በለስ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አሳየ አበበና ሌሎች አመራሮችና ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

Husamedin Issa







Highlights

በግልገል በለስ ከተማ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው።""""""""""""""""""""""""""" (ግልገል በለስ:-መስከረም 4/2018 ዓ...
14/09/2025

በግልገል በለስ ከተማ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው።
"""""""""""""""""""""""""""

(ግልገል በለስ:-መስከረም 4/2018 ዓ/ም) በግልገል በለስ ከተማ የግድቡን መጠናቀቅ አስመልክቶ ''እምርታና ማንሰራራት''በሚል መሪ ቃል የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው።

በውይይት መድረኩ የመተከል ዞንና የግልገል በለስ ከተማ አስተዳደር አመራሮችን ጨምሮ የከተማዋ ነዋሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አትንኩት ሽቱ ኢትዮጵያውያን በተባበረ ክንድ ያጠናቀቅነው የህዳሴ ግድብ የመቻላችን ማሳያ መሆኑን ገልጸው በሌሎች የልማት ስራዎችም መደገም አለበት ብለዋል።

በግድቡ ግንባታ ያሳየነውን ወኔና መነሳሳት በዞኑ ውስጥ የሚገኙ የልማት ስራዎችን በማሳለጥ የብልጽግና ጉዞን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

የግልገል በለስ ከተማ አስተዳደር ክቡር ከንቲ አቶ አሳየ አበበ፤ የኢትዮጵያዊያን አንድነታችን ምልክት፣ የኅብረታችን ነጸብራቅ፣ የአፍሪካዊያን ብሩህ ዘመን ማብሰሪያ የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተጠናቆ በመመረቁ መደሰታቸውን ገልፀዋል።

አክለውም ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መቻላችንን ያረጋገጥንበት ስራ መሆኑን ገልፀው ግድቡን ከልማት በላይ የሚያደርጉት በርካታ ቱሪፋቶች እንዳሉት ተናግረዋል።

በተጨማሪም ከግድቡ መጠናቀቅ ጋር ተያይዞ የሚመጣውን ጸጋ በአግባቡ በመጠቀም ከተማዋን ምቹና ተወዳዳሪ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ ከዛሬ ጀምሮ የተለያዩ መርሃ ግብሮች እየተካሄዱ ይገኛሉ።

በመድረኩ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ አቶ መለሰ ኪዊን ጨምሮ የዞኑና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሬች ተገኝተዋል መረጃዉ የግ/በለስ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ነዉ።

Highlights




|🇪🇹 ኢትዮጵያ |🇪🇹ህዳሴ በልጆቹ ህብረት እዉን ሆኗል|🇪🇹
09/09/2025

|🇪🇹 ኢትዮጵያ |🇪🇹
ህዳሴ በልጆቹ ህብረት እዉን ሆኗል|🇪🇹

በ2017 በጀት ዓመት ጽ/ቤታችን በፖለቲካ እና በዉስጠ ፓርቲ ስራዎች የተሻለ አፈጻጸም በማስመዝገብ ይህን ዕዉቅና ማግኝት ችለናል።ዕዉቅናዉ ለ2018 በጀት አመት ይበልጥ በትጋት እንድሰራ የሚ...
31/08/2025

በ2017 በጀት ዓመት ጽ/ቤታችን በፖለቲካ እና በዉስጠ ፓርቲ ስራዎች የተሻለ አፈጻጸም በማስመዝገብ ይህን ዕዉቅና ማግኝት ችለናል።
ዕዉቅናዉ ለ2018 በጀት አመት ይበልጥ በትጋት እንድሰራ የሚያበረታታ በመሆኑ በራሴ እና በጽ/ቤቱ ስም ምስጋናየን አቀርባለሁ።

Highlights
Husamedin issa "ሁሳመዲን ኢሳ"
Husamedin Issa


04/08/2025

Ashadeli Hassen

የቀድሞዉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ሰብስቤ ንሳፄ ጋስ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተዉ ዛሬ ሠኔ 19 ቀን 2017 ዓ.ም በ78 ዓመት ዕድሜያቸው ህ...
26/06/2025

የቀድሞዉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ሰብስቤ ንሳፄ ጋስ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተዉ ዛሬ ሠኔ 19 ቀን 2017 ዓ.ም በ78 ዓመት ዕድሜያቸው ህይወታቸው በማለፉ የቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት የተሰማዉን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻል፡፡

ጥር 8 ቀን 1946 ዓ.ም በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ማንቡክ ቀበሌ የተወለዱት ክቡር አቶ ሰብስቤ ንሳፄ ዕድሜ ዘመናቸውን ስለ ሀገር አንድነትና ስለ ህዝብ ተጠቃሚነት ሲባል አሳልፈው የሰጡ ዕውነተኛ የህዝብ ልጅ ነበሩ፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በማምቡክ ቀበሌ ማንቡክ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የጀመሩት ክቡር አቶ ሰብስቤ የሀገራቸውን ዳር ድንበር ለማስከበር እና የህዝባቸውን ክብር ለማስጠበቅ ሲሉ የሚወዱትን ትምህርት አቋርጠው በ1969 ዓ.ም የውትድርናውን ዓለም ተቀላቅለዋል፡፡

ለ15 ዓመታት ያህልም የተሰጧቸውን ወታደራዊ ግዳጆች በመፈፀም ሀገራቸውን እና ህዝባቸውን በቅንነትና በታማኝነት አገልግለዋል፡፡

በደርግ ውድቀት ማግሥት የተፈጠረውን ፌዴራላዊ አደረጃጀት ተከትሎ በቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች ያገለገሉ ሲሆን

👉 ከጥር 1986 እስከ ሰኔ 1987 የመተከል ዞን አስተዳደር ዋና ፀሀፊ

👉 ከሐምሌ 1987 እስከ 1992 ኢኮኖሚ ዘርፍ ኃላፊ
ከ1992 እስከ 1995 የክልሉ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ

👉 ከ1995 እስከ 1997 የቀድሞው የቤጉህአዴግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት ኃላፊ

👉 ከ1997 እስከ 2000 የክልሉ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ኃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነዉ ማገልገላቸው የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ክቡር አቶ ሰብስቤ ንሳፄ ዕድሜ ሳይገድባቸው፣ አመራርነት ሳያግዳቸው ያቋረጡትን የአንደኛ ደረጃ ትምህርት በመቀጠል በአሶሳ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት እንዲሁም የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአሶሳ መሰናዶና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተከታትለው አጠናቀዋል፡፡ በአካውንቲንግ ዲፕሎማ በሊደርሺፕና ማነጅመንት ደግሞ በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀዋል፡፡ “ቤዋ” በሚል ርዕስ የጉሙዝን ህዝብ ታሪክ፣ ምንጩንና ባህሉን መሠረት ባደረገ አግባብ ከአማርኛ ወደ ጉምዝኛ እና እንግሊዝኛ የተተረጎመ ከ25 ሺህ በላይ ቃላትን የያዘ መዝገበ ቃላት አሳትመዋል፡፡ በዚህ ረገድ ለበርካታ ወጣቶችና አመራሮች አርዓያና ምሳሌ ለመሆን ችለዋል፡፡

አቶ ሰብስቤ ንሳፄ ከ29/8/2000 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 11/8/2004 ዓ/ም ባሉት 5 ዓመታት የክልሉ ምክትል ርዕሰ-መስተዳደር እንዲሁም ከ1993 ዓ.ም እስከ 2007 ዓ.ም ባሉት 3 ተከታታይ የምርጫ ዓመታት የህዝባቸውን የውክልና ድምፅ በማግኘት የክልሉ ምክር ቤት አባል በመሆን ህዝብና መንግሥት የጣለባቸውን ከፍተኛ አደራና ዕምነት በከፍተኛ የህዝባዊነት ስሜት በመፈፀም ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል፡፡

የ6 ወንዶችና የ4 ሴት ልጆች አባት የሆኑት ክቡር አቶ ሰብስቤ ንሳፄ ከመንግሥት እኚህ ታላቅና ታሪካዊ ሰው በክልሉ በነበራቸው የአመራርነት ዘመን ብቻ ሳይሆን ኃላፊነታቸውን ለተተኪዎች ካስረከቡ በኋላ በነበሩ ዓመታትም ጭምር እንደ ግለሰብ ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ይፈፅሟቸው የነበሩ መልካም ተግባራት እንደተጠበቁ ሆኖ ለክልሉ ሠላም፣ ልማትና ዕድገት፣ ለህዝቦችም ፍትሃዊ ተጠቃሚነት አቅማቸው የፈቀደውን ሁሉ አበርክተዋል፡፡ ለአካባቢ ሰላምና መረጋጋት በሀገር ሽማግሌነት፣ በመካሪ አባትነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡ እንዲህ አይነቱን ሰው ማጣት በእርግጥም እንደ ክልል ትልቅ ጉድለት ነው፡፡

የቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት በእኝህ ታላቅ ሰው ህልፈት የተሰማዉን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸዉ ሁሉ መፅናናትን ይመኛል፡፡




@ቤጉ

17/06/2025

Address

Asosa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Husamedin issa "ሁሳመዲን ኢሳ" posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share