Great Afar

Great Afar ▒F░O░L░L░O░W▒
┊ ▕▔╲▂▂▂╱▔|
━━╮╭┈╮⠀╭┈╮╭
╰╰┃▏╭╮⠀╭╮▕┃
┃⠀┃▏┈┈▅┈┈▕
┃⠀┃▏┈╰┻╯┈▕
┃⠀╰▓▒░M░E░▒

አፋር እና ቀይ ባህር  : ረዘመ ያለ ፅሁፍ By :- A.professor Kalil Îbn Alì ...🖋መግቢያ አፋር የዛሬው  ኢትዮጵያ፤ ኤረትራ እና ጁቡቲ ሳይፈጠር ከሳውኪን ወደብ (Arab-...
10/03/2025

አፋር እና ቀይ ባህር : ረዘመ ያለ ፅሁፍ

By :- A.professor Kalil Îbn Alì ...🖋

መግቢያ

አፋር የዛሬው ኢትዮጵያ፤ ኤረትራ እና ጁቡቲ ሳይፈጠር ከሳውኪን ወደብ (Arab-Peninsula) እሰከ አዱላስ ወደብ ከባቡል መንደብ እስከ ዘይላዕ ወደብ በባለቤትነትና በብቸኝነት ለብዙ ሺ አመታት (Immemorial years) የቆየና የኖኑ ህዝብ ነው።

የዛሬው የኢትዮጵያን፣ የጅቡቲን እና የኤርትራን ክፍሎች የሚያጠቃልለው የአፋር ትሪያንግል ቀደምት ተወላጅ የሆነው የአፋር ህዝብ በቀይ ባህር አካባቢ ታሪካዊ የንግድ ትስስር ውስጥ ትልቅ ሚና ተጫውቷል። በጥንካሬያቸው እና በባህል ሃብታቸው የሚታወቁት አፋርዎች ቀኝ ገዥዎችና ወራሪዎች በመምጣታቸው በፊት ከጥንት ገዜ ጀምሮ በዚህ ስትራቴጂካዊ ጉልህ ስፍራ በበላይነትና በስኬት የኖረና የመራ ህዝብ ነው። በአፍሪካ ፣ በአረብ ባሕረ-ገብ መሬት እና በህንድ ንዑስ አህጉር መካከል የሸቀጦች እና የባህል ልምዶች ልውውጥ ውስጥ ወሳኝ አማካኝና አገናኝ በመሆን ለብዙ አመታት አገልግለዋል። በባህር ንግድ መስመሮች ውስጥ በተለይም ከአንደኛ - ሰባተኛውው ክፍለ-ዘመን #የአክሱም ግዛት ከፍተኛ ደረጃ ላይ በነበረበት ወቅት በባህር ንግድና ኢኮኖሚ ላይ የነበራቸው ተሳትፎ እንደ ቅመማ-ቅመም፣ ጨርቃጨርቅ እና የከበሩ ድንጋዮች የሸቀጦች ግብይት ዋና ተዋናዮች የነበሩና ይህም በክልላዊም (regional) ሆነ በአለምአቀፍ ሁኔታዎች ውስጥ የነበራቸው ጠቀሜታና አስፈላጊነታቸው አጠናክሯል ። የአፋር ህዘብ ከአክሱም ዘመነ መንግሰት ጋር ቅርብ ግንኙነት ስለነበረው በዘመኑ የአክሱም ግዛተ መንግሥት መሳካትና መጠናከር ዉስጥ የአፋር ሚና በጣም ጉልህ እንደነበረ የታሪክ ድርሳናት ያስረገጣሉ።
............................................................................

(ሀ):- የአፋር ህዝብ እና የቀይባህር ቁረኝነት በአለም አቀፍ ከታሪክ ፀሀፊያን አንደበት:-

የአፋር ህዝብ ለዘመናት በአፍሪካ ቀንድ የባህር ላይ ታሪክ ውስጥ በጥልቅ የተካተተ የቀይ ባህር ጠረፍ አካባቢዎች የማይደራደር ጠባቂ ህዝብ ነው ።የአፋር ህዝብ በዚህ ወሳኝ የንግድ እና የፍልሰት ኮሪደር ላይ የበላይነታቸው የጀመረው በቀኝ ገዥዎች የተፈጠሩት እንደ ኤርትራ እና ጅቡቲ እንድሁም አሁን ያለችው ኢትዮጵያና ሌሎች ዘመናዊ ሀገራት ከመፈጠሩ በፊት ከብዙ ሺህ አመታት በፊት እንደነበረ የተለያዩ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ።


አንጋፋው የፋራንሳይ የቋንቋና የታሪክ ተመራማሪ ዲዲየር ሞሪን (2012)፡ "Dictionnaire historique des Afar (1285-1982) በሚል ርዕስ ባሳተሙት መፅሐፋቸው በአርኪኦሎጂ ግኝታቸው የአፋርን ህዝብ ቀደምትነት ከቀይ ባህር ጋር የተቆራኘ መሆኑን ቀጥሎ ባለው መልኩ ገልፀውልናል :- ''አፋሮች በቀይ ባህር ተወላጆችና ቀደምት ባለቤቶች በመሆናቸው ባህላዊ እና ግዛታዊ ቀጣይነት ከጥንት ጀምሮ አስጠበቋል። በዳንካሊያ አካባቢ የሚገኙት የቃል-ታሪካቸውና የአርኪኦሎጂ ቅርሶች የአፋር ህዝብ ከቀይ ባህር ሥነ-ምህዳርና ንግድ ጋር የቆየና የተሳሰረ ሥልጣኔ መኖሩን ያረጋግጣል።'' በማለት አትተዋል

ከዚህ ጋር ተያይዞ በአፍሪካ ቀንድ ጥንታዊ ስልጣኔዎች ላይ ያተኮረው ጣሊያናዊው አርኪዮሎጂስት እና የታሪክ ምሁር ሮዶልፎ ፋቶቪች ይህንን በሰፊው በተጠቀሰው: የጥንታዊ መንግስታት በሰሜን አፍሪካ ቀንድ (1999) በተሰኘው ፅሑፋቸው ላይ ዳስሷል። እንዲህ በማለት በመፅሀፋቸው ያስረግጣል።

"የአፋሮች የአክሱማዊት ግዛትን (kingdom of Aksumite) ከሰፊው የአፍሮ-ኢውራሺያ (Afro-Eurasian) የንግድ ሥርዓት ጋር በማገናኘት ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል።የአፋር ህዝብ በቀይ ባህር ወደቦች ላይ የነበራቸው ቁጥጥር የአክሱም ግዛት :- የሮማንና ቤዛንታይን ኤምፓየሮች ፣ የፋርስ (Persian) እና የህንድ ገበያዎችን በቀጥታ በቀይ-ባህር አፋሮች አማካኝነት እንዲያገኝ አስችሎታል፣ ይህም ዕድል የአክሱም ግዛት እንደ ኃያል ኢምፓየር ወይም ግዛት ሆኖ እንዲያድግ አስችሎታል''።

በተመሳሳይ፣ አንጋፋው የታሪክ ምሁር ሪቻርድ ፓንክረስት፣ The Ethiopian Borderlands በሚል ርዕሰ በ(1997)፣ በፃፈው መፅሀፋቸው በአፋር የበላይነት የተያዘው የአዱሊስ ወደብ (Adulis Port) ያለውን ወሳኝ ሚና ዘርዝሯል። “የአዱሊስ ወደብ በአፋር ተጽእኖ ስር የቀይ ባህር ንግድ ዋና ማዕከል በመሆን ሸቀጦቹን በአፍሪካ፣ በሜዲትራኒያን እና በእስያ መካከል እንዲዘዋወሩ አድርጓል። ያለዚህ መዳረሻና መገናኛ ፣ የአክሱም ግዛት ወደ ሃያልና የስልጣኔ ኤምፓየር ማደጉ በእጅጉ ይገደብ ነበር። በማለት የአክሱም መንግስት ሃያልነት እና ስልጣኔ ትልቅ መንሰኤ በአፋሮች የሚተዳደረው የአዱሊስ ወደብ መሆኑን በመግለፅ የአፋር ህዝብ በአክሱም መንግሥት ስልጣኔ እና ዕድገት ላይ የነበረው ሚናን በአፅንኦት አብራርቷል።

የአፋር የኢኮኖሚ የበላይነት ከአክሱም ውድቀት በኋላም እስከ 20ኛው ክፍለዘመን ድረስ ከቀይ ባህር እስከ ዳናኪል ዲፕሬሽን (Danakil depression) ቀጥሏል። የቀይ ባህር እና የኢትዮጵያ ታሪክ ምሁር የሆኑት መርዶክዮስ አቢር ይህንን:- በኢትዮጵያ እና በቀይ ባህር (1980) በሚል ስራቸው ሲዳሰሱት የአፋርን የጨው ንግድ (አሞሌ ጨው) ቅልጥፍና ሲገልጹ፡- " አፋር ከደናኪል ዲፕሬሽን)(Danakil Depression ) ወደ ኢትዮጵያ ደጋማ ቦታዎች እና ከዚያም በላይ በማጓጓዝ ለአፍሪቃ ቀንድ የጨው ንግድ የደም ስር በመሆን አገልግሏል ። የንግድ ተጓዦቻቸው (Caravans) የአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች ከመምጣታቸው ከረጅም ጊዜ በፊት የአገር ውስጥ ኢኮኖሚን ​​አስጠብቆ ቆይቷል።''

እንድሁም በአፍሪካ ቀንድ ላይ ባደረጉት ሰፊ ጥናትና ምርምር የሚታወቁት ታዋቂው እንግሊዛዊው አንትሮፖሎጂስት አይ.ኤም.ሊዊስ '' ይህንን ስር የሰደደ ታሪክ :People's of the Horn of Africa (1998) በተባለው መጽሃፋቸው እንዲህ ሲሉ ገልፀውታል።

''ቅኝ ገዢዎች በአፍሪካ ቀንድ እና በቀይ ባህር ውስጥ ጣልቃ ከመግባታቸው ከረጅም ጊዜ በፊት የአፋሮች ቁልፍ የቀይ ባህር ወደቦች እና የባህር መስመሮችን/መንገዶችን በመቆጣጠር በቀይ ባህር ዳርቻ ላይ ዘላቂ ህልውናን ጠብቀዋል'' ።

ይህ ታሪካዊ እውነታ የአፋርን ግዛት ሉዓላዊነት ብቻ ሳይሆን የረዥም ጊዜ ሚናቸውን እንደ ባህር መርከበኞች፣ ነጋዴዎች እና የባህል አስተዋይነታቸው የሚያሳይ ነው ።

አፋሮች በአፍሪቃ ቀንደ ከመገኘታቸውም/ከመኖሪያቸው ባለፈ የአፋር ህዝብ ከቀይ ባህር ጋር ያለው ግንኙነት በቋንቋ፣በባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መስተጋብሮችን የሚያተቱ ጥናቶች የአፋርን ቀደምትነት በጉልህ የሚያሳይ ነው ። ታኀዋቂዎቹ አፍሪካውያን የታሪክ ተመራማሪዎች ቦኒ ሆልኮምብ እና ሲሳይ ኢብሳ፣ The Invention of Ethiopia (1990) በሚል ርዕስ ያበረከቱት ተፅዕኖ ፈጣሪ ስራቸው : የአፋርን ህዝብ ከቀይ ባህር ጋር ያላቸው ግንኙነት ከባህላቸው እና ከቋንቋቸው ጥልቀት አንጻር አፅንዖት ሰጥተውበታል።

"የኩሽቲክ ቤተሰብ(Cush*tic Family) ቅርንጫፍ የሆነው የአፋርኛ ቋንቋ በአንድ ወቅት የቀይ ባህር የንግድ መረቦችን ይቆጣጠሩ ከነበሩት ነዋሪዎች ጋር ተመሳሳይ መሆናቸው እንድሁም የቋንቋ ውርሻቸው፣ በባህር ላይ ማጥመድ፣ ዓሣን ማጥመድ እና በንግዱ ላይ ካላቸው እውቀትና ክህሎት ጋር ተዳምሮ በአፍሪካ ቀንድ (ክልል) ቀደምት የባህር ዳርቻ ነዋሪዎች እንደ ነበሩ ሚናቸውንና በመሬት ላይ ያለው ተጨባጭ የአርኪኦሎጂ ማስረጃዎች ህያው ምስክር ናቸው ። በማለት ገልፆታል። የተመራማሪዎቹ ምልከታዎችና ማስረጃዎች የአፋር ህዝብ በአከባቢው የሚገኙ ወይም የሚኖሩ ህዝቦች ብቻ ሳይሆኑ በኢኮኖሚና በባህል ልውውጡ ንቁ #መሃንዲሶች ነበሩ የሚለውን ታሪክና ሃሳብ ያጠናክራሉ፣ ይህም የአፋርን የቀይ ባህርን ሚና በአፍሪካ፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና በከዚያም በላይ ወሳኝ ትስስር በመፍጠር የተጠናከረ ነበር ።

ከዚህ በተጨማሪ የአፋር ህዝብ በቀይ ባህር ላይ ያለው ፋይዳ የጎላ ነጋዴ በመሆናቸውም ጎልቶ የሚያሳይ እንደ #ትሪሚንግሃም በእስልምና እና በአፍሪካ ታሪክ ላይ የተካነ ታዋቂው እንግሊዛዊ ምሁር ''Islam in Ethiiopia (እስላም በኢትዮጵያ)'' (1952) በተሰኘው መፅሃፋቸው ላይ ስለ አፋር ህዝቦች በቀይ ባህር ላይ የነበራቸው የኢኮኖሚያዊ የበላይነትን በተመለከተ ተጨማሪ ግንዛቤን በማጠናከር እንድህ በማለት ይገልፃል። "የአፋር ህዘብ ስልታዊ አሰፋፈር በቀይ ባህር ጠረፍ አካባቢ በአረብ ባሕረ ስላጤ፣ በአፍሪካ ቀንድ እና በአፍሪካ-ውስጥ መካከል የንግድ በሮች ጠባቂዎችና ባለቤቶች እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። ወደቦቻቸው የወርቅ፣ የዝሆን ጥርስና ሌሎች ውድ ዕቃዎች መለዋወጫና ማስተላለፊያ ሆኑ፣ ይህም በአካባቢው ያላቸውን ተፅዕኖ አጠናክሮላቸዋል።'' በማለት የኣፋር ህዝብን የቀይ ባህር እስትራቴጂክ እና ስልታዊ አሰፋፈርን እንድሁም በኢኮኖሚና ንግድ ላይ የነበራቸው የበላይነት አመላክቷል።
................................................................

(ለ):- የአፋርን የጂኦፖለቲካል አሰፋፈር እና ፈተናዎች

ይሁን እንጂ ይህን ሁሉ የአፋርን የቀይ ባህር ጠረፎች እና የኢኮኖሚን ቁጥጥር ዝምብሎ ያለ ፈተና የመጣ አልነበረም ። የአፋርን ራስ በራስ ማስተዳደርን እና የአፍሪቃ ቀንድ ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል የቅኝ ግዛት እና ኢምፔሪያል ምኞቶች በተከታታይ ለብዙ አመታት በተለያዩ መንገዶች የመጡ ቢሆንም፣ የአፋር ህዝብ በተከታታይ የሚመጣ የውጭ የበላይነትን በትጋት በመከላከል በፅኑ ተቋቁሟል። ይህንን ሀሳብ የሚያጠናክረው ታዋቂው የታሪክ ምሁር #ጆናታን ሚራን በRed Sea Citizens: Cosmopolitan Society and Cultural Change in Massawa (2009)'' በተሰኘው ስራው የአፋርን ፀረ-ቅኝ ገዥዎች ተጋድሎ እንድህ ብሎ ዘግቧል፡-

“አፋሮች የኦቶማንን (የቱርክ) ፣ የግብፅን እና በኋላም የአውሮፓ ወረራዎችን በባህር ዳር ግዛቶቻቸው ላይ በመቃወም በፀረ-ቅኝ ግዛት ተቃውሞ ግንባር ቀደም ነበሩ። እ.ኤ.አ. በ1875 የግብፅን ወረራ በመቃወም ያደረጉት ሕዝባዊ አመጽ ነፃነታቸውን ለማስጠበቅ ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነበር።

ይህ ተቃውሞ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ብቻ የተወሰነ አልነበረም። በ20ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ላይ እንኳን እንደ #ሱልጣን ያሲን ሃይሳማ እና የአፋር ናሽናልስትና መሪ የነበሩት ያሲን ሞሃሞዳና በመሳሰሉት ሰዎች የሚመሩ ንቅናቄዎች የአፋርን ህዝብ በማበረታታት የአንድነት እና የራስን እድል በራስ የመወሰን ትልቅ እስከ ዛሬ ድረስ ዘርግተዋል።

የአፋር ህዝብ በታሪካቸው በርካታ የውጭ ተግዳሮቶች ገጥሟቸዋል፣ ከነዚህም መካከል በአጎራባች ጎሳዎች እና ኢምፓየሮች ግዛታቸውን ለመቆጣጠር ሙከራ አድርገዋል። እነዚህ ጫናዎች ቢያጋጥሟቸውም እስከ 20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ድረስ የራስ ገዝ አስተዳደርን ጠብቀው ቆይተዋል፣ ይህም ከአውሮፓውያን ቅኝ ገዥ ኃይሎች እና ከኢትዮጵያ ገዥዎች ጋር በተደረጉ ፍልሚያዎች እና ግጭቶች በንቃት በመፋለም የውጭውን ሀይሎች የበላይነት በመቃወምና በመጋፈጥ ከፍተኛ ተቃውሞ አሳይተዋል። ይህን ተቃውሞ ከሚያጎሉ ታሪካዊ ክስተቶች መካከል በ1875 በስዊዘርላንድ ጀብዱ ቨርነር #ሙንዚንገር የሚመራው የግብፅ ወራሪ ላይ በአፋር አውሳ አካባቢ በተለምዶ ''ጋማሪ'' የሚባል (በአሁኑ የአፋር ክልል በአውሲ ረሱ አፋምቦ ወረዳ አካባቢ) በሱልጣን መሀመድ ሃንፍሬ (ኢላልታ) የሚመራው የአፋር ተዋጊዎች ከእነ ጦር መሪያቸው #ሙንዚንገርን ጨምሮ አንድ ሳይወጣ የተደመሰሰበት ክስተት የአፋርን ነፃነታቸውን እና ማንነታቸውን ለማስጠበቅ ያላቸውን ቁርጠኝነት በግልጽ የሚያሳይ ታሪካዊ ክስተት ነው ።
በሌላው ታሪካዊ ክስተት ለ30 አመታት ያህል የቀጠለው የጣሊያን ወረራ ታቃውሞ የአፋር በጊሪፎ ሱልጣን (ቢዱ ሱልጣን )፣ በሱልጣን ሃይስማ አሃው እና በልጆቻቸው ሱልጣን መሀመድ ሃይሳማ እስከ ሱልጣን ያሲን ሃይሳማ ዘመን ድረስ የተደረገው የረጅም ጊዜ መከላከል እና ዉጊያ ነበር ። የአፋር የፀረ-ቅኝ ግዛት ስሜት እና የአፋር ህዝብ በፋሽስት-ኢጣሊያኖች ላይ ለ30 አመታት ባደረገው ተጋድሎ በሺህ የሚቆጠሩ የአፋር ተወላጆች ህይወታቸውን ያጡ ቢሆንም በሙሶሎኒ የሚመራው የጣልያን ሃይሎች በአፋር እልህ አስጨራሽ ጦርነትና መስእዋትነት በአፋር በኩል/ወደ መሀል አገር እና ግዛቶች ማለትም ወደ መሀል ኢትዮጵያ እንዳይገቡ አድርጓል። በዚሁ እልህ አስጨራሽ የማንነት እና ክብርን። አሳልፎ ያለመስጠት ተጋድሎ ከሙሶሎኒ ሀይሎች ጋር ለብዙ አመታት ባደረገው ከባድ ጦርነት በ1931 ቢዱ በተባለች ቦታ በ39 አመቱ ተሰውተዋል ።
......................................................................

(ሐ):- የአሁኑ የኣፋር ህዝብ ሁናቴ እና የቀይ ባህር ውጥረት

በዘመናችን የአፋር ህዝብ ከማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ጋር እየተጋፈጠ እና እየተባባሰ የመጣውን የፖለቲካ ተለዋዋጭነት እና ውጫዊ ጫናዎች ተባብሶበታል ። በንግድ በተለይም በቀይ ባህር ጠረፍ እና በጨው ምርት ላይ የነበራቸው የበላይነት በተከታታይ በማሽቆልቆል የብዙ ሺ አመታት የአፍሪቃ ቀንድንና እና የቀይ ባህር ጠረፎችን በባለቤትነት እና በበላይነት ይመሩ የነበረው የአፋር ህዝብ ዛሬ በቀኝ ገዥዎች የተፈጠሩት የአፍሪቃ ቀንድ አገራት ማለትም በኢትዮጵያ፣ በኤርትሪያ እና በጁቡቲ መንግስታት ያለፍላጐታቸው ተከፋፍለውና ተገልለው ይገኛል። በምስራቅ አፍሪቃ እና በቀይ ባህር አካባቢ ከእነ አካተው እንድጠፉ የተደረገውን የውጭ እና የውስጥ ወረራን ተቋቋመው እስካሁን ድረስ በታሪክ ከነበሩበት አካባቢዎች ፈንክች ሳይል፣ ባህላቸው ፣ ቋንቋቸው፣ እና ማህበራዊ ማስተጋብራቸው ጠብቀው አይበገሬነቱን አስረግጠዋል።

የአፋር ህዝብ በአካል በሶስቱም በአርተፊሻል መስመር የተከለሉ አገሮች የሚገኝ ቢሆንም በመንፈሳቸው የተለያዩ አገር ሰዎች ነን ብሎ አስቦ አያውቅም። አፋሮች በሶስት አገራት ስገኙ ሁሉም በደንበሮች የሚገናኙና በመካከላቸው ሌላ ባዕድ የሆነ አካል ስለላስገቡ እስካሁን ድረስ ማህበራዊ ግንኙነታቸው ማስቀጠል ችሏል።

የአፋር ህዝብ በጦርነት እና በሀይል መርታት እንዳማይቻል የተረዳው ገዢዎች በተለይም የኢትዮጵያ ገዥ ነግስታት አፋርን በጦርነት አለመንካትና ወደ ዘመናዊነት እንዳይቀላቀሉ ፣እንዳይማሩ፣ በኢኮኖሚው እንዳያድጉ ፣ እንዳይነቁ ተብለው በሪጅናል ደረጃም ከዕድገት ፖሊሲዎችና እና ስትራቴጂዎችም ጭምር እንድገለሉ ተደረገው በአሁን ጊዜ በሶስቱም አገሮች በዝቅተኛ የእድገት ደረጃ ላይ ይገኛል። የአፋር ህዝብ በሶስቱም አገሮች የሚገኘው የአፋር ህዝብ ከፖለቲካዊ ፣ የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተሳትፎ ተገለለውና ምንም አይነት ሚና እንዳይኖረው ተደርጓል።

በኤርትራ አፋር ታሪካዊ እርስት የሆኑ አካባቢዎች ላይ ዲሞግራፍን እስከመቀየር እና የአፋር ህዝብ ለዘመናት በጦርነት እንኳን ያልተፈናቀለበትን የባህር ጠረፎችን ለቀው እንድሄዱ በሲስተማቲክ አስገዳጅነት እየተፈናቀሉ ይገኛሉ ። ከኤርትራ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የአፋር ቤተሰቦች ወደ ኢትዮጵያ፣ ወደ የመን፣ ወደ ሱዳን ወደ ጅቡቲና ሌሎች አገሮች ተሰደዋል፣ እየተሰደዱም ይገኛል ። ይህንን በመቃወም የቀይ ባህር ነፃ አውጪ ተጋድሎዎች ማለቲም የRed Sea Afar Democratic organization(RSADO), እና Eritrean Afar National Congress (EANC) ትግሎች ከተጀመረ ብዙ አመጣጥ አስቆጥሯል።


በጅቡቲ እንደዚሁ ትልቁን የመሬት ቆዳና የቀደሙ ነዋሪዎች የሆኑት የአፋር ህዝብ ለፈረንሣይ ስላልተጎባደደ ብቻ የጅቡቲን ዲሞግራፊ በመቀየር የፖለቲካ እና ኢኮኖሚያዊ የበላይነት በአካባቢው ታሪካዊ ይዞታዎች ያልነበራቸው የኢሳ-ሶማሌ ጎሳ አባላት እንድይዙ ተደረገው የአፋር ህዝብ በፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ረገድ ያላቸው ሚና በጣም ደካሜ ሆነዋል።

ይህንን የተቃወመው የጅቡቲ ህዝብ ግዲያ፤ እስር እና መሳደድ ደርሶባቸዋል። ይህንን ጭቆናን በመቃወም (Front for Restoration of Unity and Democracy (FRUD) ወደ የትጥቅ ትግል ገብቶ መታገል ከጀመረ ብዙ አመታት አስቆጥሯል። የአፋር ህዝብ ለብዙ ዘመናት የኖሩበት የቀይ ባህር ዳርቻዎችና ወደቦች ከፍተኛ ጂኦፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላቸው አካባቢዎች ናቸው ።

በታሪክ የአፋር ህዝብ በዛሬይቱ ኤርትረና ጅቡቲ በባህር ዳርቻዎች ሰፍኖ የኖሩበት በመሆኑ በእነዚህ ወደቦችና አካባቢዎች ላይ የሚነሱ ማናቸውም የይገባኛል ጥያቄዎች ለዘመናት የመሬቱ ተቆርቋሪና ነዋሪ ሆኖ የቆየውን የአፋር ህዝብን መብትና ታሪካዊ ህልውና ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆን አለበት።

የአፋር ማህበረሰብን ያላሳተፈ ማንኛውም በቀይ ባህር ወደቦች እና አካባቢዎች የሚደረጉ የይገባኛልም ሆኔ ለሎች ስምምነቶች ቀጥታ የአፋርን ህዝብ ህልውና የሚነካ በመሆኑ አፋርን ቀጥታ የሚያሳትፍ መሆን አለበት።በነዚህ ወደቦች ላይ ፍላጎት ያለው ማንኛውም መንግስት ወይም አካል ከአፋር የፖለቲካ መሪዎች እና ተወካዮች ጋር በመነጋገር ድምጻቸው እንዲሰማ እና እንዲከበር ማድረግ አለበት።

በነዚህ ወደቦች ላይ ፍላጎት ያለው ማንኛውም መንግስት ወይም አካል ከአፋር የፖለቲካ መሪዎች እና ተወካዮች ጋር በመነጋገር ድምጻቸው እንዲሰማ እና እንዲከበር ማድረግ አለበት። ወደቦች የኢኮኖሚ መናኸሪያ ብቻ ሳይሆኑ የአፋር ህዝብ የማንነት እና የአኗኗር ዘይቤ አካል ናቸው። በውሳኔ ሰጪነትና ተጠቃሚነታቸው ሚና ችላ ማለትና መንፈግ የኢ-ፍትሃዊና ተቀባይነት የሌለው እርምጃ በመሆኑ በአካባቢው ሳላምና መረጋጋትና ተጨማሪ ውጥረቶች እንዳይፈጠሩ እነዚህ ወደቦች በተመለከተ የሚደረጉ ማንኛውም ስምምነቶች እና ፖሊሲዎች ሁሉን አቀፍ ውይይቶች በማድረግ የአፋር ተወላጆች ፍቃድና ተሳትፎ እንዲደረጉ ከአፋር ፖለቲከኞች እና የማህበረሰብ መሪዎች ጋር ምክክር እና ድርድር ተደርጎ መሆን አለበት ።

በመላው ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ጅቡቲ የተስፋፋው የአፋር ህዝብ ከእነዚህ የባህር ዳርቻ አካባቢዎች ጋር የባህል፣ የኢኮኖሚ እና የታሪክ ግኑኝነት በመጋራት በማንኛውም በዚህ ዙሪያ የሚደረጉ ውይይቶች ላይ መሳተፍ ለድርድር የማይቀርብ ያደርገዋል ።
የቀይ ባህር ጠረፍ ወይም ወደቦች የኢኮኖሚ መናኸሪያ ብቻ ሳይሆኑ የአፋር ህዝብ የማንነት እና የአኗኗር ዘይቤ አካል ናቸው።

ከዚህ በተጨማሪም የክልል መንግስታትን (Red Sea Region) እና የኢኮኖሚ አጋሮችን ጨምሮ አለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት የአፋርን ውክልና ከወደብ ጋር በተገናኘ አፋርን የድርድር አካል ማድረግ ያለውን ጠቀሜታ ሊገነዘቡ ይገባል።

የአፋርን ህዝብ ጥቅም ችላ ማለት አሁን ያለውን ውጥረት ከማባባስ እና ለበለጠ መፈናቀል እና መብት መጓደል አስተዋጽኦ ያደርጋል። ፍትሃዊ አካሄድ ዘላቂና ፍትሃዊ መፍትሄ ለመፍጠር ከአፋር ተወካዮች ጋር የኢኮኖሚ ጥቅማጥቅሞችን፣ የአስተዳደር መዋቅሮችን እና የሀብት ክፍፍል ዘዴዎችን መወያየትን ያካትታል። የአፋር ህዝብ ለአያት ቅድመ አያቶቹ ያላቸውን ህጋዊ መብትና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እውቅና መሰጠቱ መረጋጋትን ከማስፈን ባለፈ ለክልላዊ ትብብርና ልማት አስተዋጽኦ ያደርጋል።

አላለቀም ..................

በነገራችን ላይ በክርስትና አስተምህሮ እስላም መንግስተ ሰማያት አይወርስም።  ያላመነ ያልተጠመቀ አይድንም ስለሚሉ።  በእስልምና እምነት ደግሞ ከእስልምና እምነት ውጭ ያለ የጀነትን ሽታ አገኝ...
23/01/2025

በነገራችን ላይ በክርስትና አስተምህሮ እስላም መንግስተ ሰማያት አይወርስም። ያላመነ ያልተጠመቀ አይድንም ስለሚሉ።

በእስልምና እምነት ደግሞ ከእስልምና እምነት ውጭ ያለ የጀነትን ሽታ አገኝም። ስህተት ላይ ጥመት ላይ ያለን አካል በስህተቱ ይፀና ዘንድ ማስመሰል ደስ አይልም።

አብሮነታችን በማህበራዊና አገራዊ ጉዳይ እንጅ ሀይማኖት መቼም የማይታረቅ ተቃርኖ ነው። የአንዱ ጀነት ለሌላኛ እሳት ነውና።

በፍቅር በመከባበር በጉርብትና በልቅሶና ሰርግ በማህበራዊ መስተጋብራችን አብሮነታችን ምልካም መዋዋል የሚበረታታ ነው። እምነት ግን ቀይ መስመር ነው።

እናም ብሽሽቁን ከመስጅዱ አጥር ላይ አርቁት። እንዲህ አይነት ፉገራ የትኛውንም እምነት አይጠቅመውም።

የተኩስ አቁሙ በጋዛ በታወጀበት እለት ጋዛዊያኑ አንድ  ወጣትን ሲሸከሙ የሚያሳይ ቪድዮ አይቼ ነበር።ስለዚህ ሰው ሳጣራ የሚከተለውን አገኘሁ....ዶክተር ሙሐመድ ጧሂር አል-ሙሰዊይ በእንግሊዝ ...
21/01/2025

የተኩስ አቁሙ በጋዛ በታወጀበት እለት ጋዛዊያኑ አንድ ወጣትን ሲሸከሙ የሚያሳይ ቪድዮ አይቼ ነበር።ስለዚህ ሰው ሳጣራ የሚከተለውን አገኘሁ....
ዶክተር ሙሐመድ ጧሂር አል-ሙሰዊይ በእንግሊዝ ለንደን የሚኖር ትውልደ ዒራቃዊ የአጥንት ቀዶ-ጥገና ዶክተር ነው።
ሙሐመድ ከስምንት ወር በፊት ነበር ከእንግሊዝ በጎ ፍቃደኛ ዶክተሮች ጋር ወደ ጋዛ የመጣው።በጋዛም ለ3 ሳምንታት ያለ እረፍት ሲያገለግል ከቆየ በኃላ ጊዜው ስላበቃ ወደ ለንደን ይመለሳል።ወደ ለንደን ለመመለስ ሲነሳ በቁድስ ከተማ ላገኘው ጋዜጠኛ በእምባ ተሞልቶ:-
"እዚህ ኢማን አለ።እዚህ ፅናት አለ።ይህን ህዝብ አልተውም በቅርቡ እመለሳለሁ።ጋዛ ተመልሼ ብሰዋ እንኳን ምንም አይደለም።ይህ ከኔም ከእናቴም ሆነ ከጓደኞቼ ስሜት ከፍ ያለ ነገር ነው።" ብሎ ነበር።
ሙሐመድ በለንደን በርሱና ወንድሞቹ የሚጣሩ በእድሜ የገፉ እናት አሉት።ነገር ግን በጋዛ ያየው ሁኔታ እረፍት ሊሰጠው አልቻለም።
እንዳለውም ሁለት ሳምንት ሳይቆይ ተመለሰ።ይህ ጊዜ የጋዛ ሆስፒታሎች ሳይቀር በከባባድ ጥቃቶች እየተመቱ የነበረበት ሰዓት ነበር።
በጋዛ ቆይታውም እረፍት በሌለው ተከታታይ የስራ ቀናት ከ300 በላይ ከባባድ የቀዶ ጥገና ስራዎችን ሰርቷል።ከሁሉም መነጋገሪያ የነበረውም መርየም ሰባሕ ለተባለችው ህፃን የሰራው ተከላ ነው።የ9 ዐመቷ መርየም በፅዮናዊያኑ የአየር ጥቃት አደጋ ደርሶባት ዶ/ር ሙሐመድ ወደ ሚሰራበት ሹሀዳኡል-አቅሷ ሆስፒታል ስትደርስ እጇ ሙሉ ለሙሉ ተቆርጦ ነበር።ሙሐመድም ለአባቷ የተቆረጠውን እጅ ክፍል እንዲያመጣ ይነግራል።አባትም ወደ ቤቱ ተመልሶ ከፍርስራሾች መሃል የተቆረጠውን የእጇን ክፍል ፈልጎ ያመጣል።አምስት ሰዓታትን ከፈጀ የቀዶ ጥገና ስራም በኃላ ስራው የተሳካ ሆኗል።

ሙሐመድ በዚህ የከፋ ጦርነት ከጋዛዊያኑ ጋር ለአምስት ወራት አሳልፏል።ከሰሜን ጋዛ እስከ ደቡብ ጋዛ በቆየበት 5 ወራትም ውስጥ ፀጉሩን ሽበት ወሮት፤20 ኪሎን ቀንሶ ከለቅሷቸው ጋር አልቅሶ፤ህይወትን ዳግም እየዘራ አሳልፏል።ቤተሰቦቹ በተደጋጋሚ እንዲመለስ ቢወተውቱትም እዚሁ እሰዋለሁ እንጂ አልመለስም ያለው ሙሐመድ በጋዛ ሳለ ነው የተኩስ አቁሙ የተፈረመው።ለዚህም ነው ጋዛዊያኑ ይህን ወጣት በጀርባቸው ተሸክመው ክብራቸውን የገለፁት።ሰው መሳይ መልዓክቶች አሏህ ይውደድላቸው🤲

BBer Hum

👇
👇
👇

I've just reached 900 followers! Thank you for continuing support. I could never have made it without each one of you. 🙏...
21/01/2025

I've just reached 900 followers! Thank you for continuing support. I could never have made it without each one of you. 🙏🤗🎉

ትላንት እስልምናን ለመዋጋት ሶማሊያ ሞቃዲሾ ድረስ ጦር ሰራዊት ሲያሰማራ የነበር ዛሬ በመሬት ቆዳ ስፋት እጅግ በጣም አንሶ በውስጡ የሚገኙ በቁጥር ያነሱ የህ/ሰብ ክፍል ሲበድል ማየት ቢያናደ...
10/01/2025

ትላንት እስልምናን ለመዋጋት ሶማሊያ ሞቃዲሾ ድረስ ጦር ሰራዊት ሲያሰማራ የነበር ዛሬ በመሬት ቆዳ ስፋት እጅግ በጣም አንሶ በውስጡ የሚገኙ በቁጥር ያነሱ የህ/ሰብ ክፍል ሲበድል ማየት ቢያናደድም ነገር ግን አልሓምዱሊላህ ማለት ነው። አልሓምዱሊላህ ዛሬ የበደል ብትራችሁን ልታሳርፉበት የምትችሉት በተወሰነ አጥር ክልል ውስጥ በሚገኝ ማ/ሰብ ብቻ ነው። አንድም ሰው ቢሆን በእናንተ እንዳይበደል ደግሞ ጠንክረን እንታገላችኃለን። ምንግዜም እውነት ከእኛ ጋር በመሆኑ እንደምናሸንፋችሁ አሏህ (ሱወ) ቃል ገብቶልናልና አንጠራጠርም።
አሏህ ወስኖት ለሆነ በሙሉ አልሓምዱሊላህ እንላለን። ለወደፊቱ ደግሞ ጠንክረን እንታገላለን፣ እናሸንፋለን።

ገራሚ ሰበር ዜና 😁ከአንድ ታካሚ ሆድ በቀዶ ሕክምና 57 ብረታ ብረቶች ወጡአዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሣውላ አጠቃላይ ሆስፒታል ከሁለት ሰዓት በላይ በፈጀ ቀዶ ሕክም...
04/01/2025

ገራሚ ሰበር ዜና 😁

ከአንድ ታካሚ ሆድ በቀዶ ሕክምና 57 ብረታ ብረቶች ወጡ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሣውላ አጠቃላይ ሆስፒታል ከሁለት ሰዓት በላይ በፈጀ ቀዶ ሕክምና ከአንድ ታካሚ ሆድ 57 ብረታ ብረቶች ወጡ።
‎ ‎
‎በቀዶ ሕክምናው 28 ሚስማር፣ 8 ብሎን እና ሌሎች የተለያዩ ብረታ ብረቶች መውጣታቸው ነው የተገለጸው፡፡

የቀዶ ሕክምናው በስኬት መጠናቀቁን የሆስፒታሉ አጠቃላይ ቀዶ ሕክምና ሐኪም ዶክተር ጌታነህ በላይ ገልጸዋል።

‎የአንጀት ቀዶ ሕክምናው ከ2 ሰዓት በላይ የፈጀ እንደነበርም የሆስፒታሉ መረጃ ያመላክታል።

ስል FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) ዘገበ

10/12/2024

Baad Xaagitte
****

🔴Qhatarak 🇶🇦Irô caagiidah malaak elle tiysixxigennal Qhatarak 🇶🇦 naharsí malaak Gazzal girâ sooloo sissikuk akah takkennah Ameerikak Irô caagiidah malaakâ luk baar le walal gexsem kee Gazzal girâ soolo takkuh meqe niya tanih tanim qaddoosen.

🔴 Ameerikak irô caagiidah malaak iyyeemih Gazzal girâ soolo takkuuy casbit yan mara sittah milaagoonuh kaxxa saami yanim takkay immay Camaas too sittin g*y akke wayuh kaxxa adaf akkuk g*ytimtam qaddoose.

🔴 Camaasak Al Qhassaam elle Tiysixxigennal Asaaku Gazzak Baxaabaxsa le dariifal Israa-il Tankittet maysattaka abak carrisseh tanim Tiysixxige.

🔴 Cuutî gaadilek Maxco gabbaaqeh yan Yacyâ sariiq elle yiysixxigennal Qadan Badih dariifal sugte Ameerikak markabittek nammay Misaa-ilittet carrisseh tanim yiysixxigem kee Tonnaah Ameerikak 3 tekke Logistics Taarre maraakibiy Djiboutî Furdak tewqeh tanit maqar le maysattaka abne axcuk qaddoose.

🔴Israa-ilik Naharsí Malaak Asaaku qimboh addah Israa-il mackamatih Foocal soolem Israa-il Cokmih buxa Umaadoobaak gexxaamah wayto kaal hayteh tanim qaddoosen.



🔴Suuriyal sugte Bashaar Al-Asad xinto tiddigilleemih Israa-il doolat 300 daga takke qaran maysattakooki gexisak g*ytimtam qaddoosem kee Tama maysattakookit Suuriyak kalalí qande luk sugte Silaacittek 80% Taamak iro abak finqisseh tanim Israa-il qande tiysixxige.

Tonnaah Israa-ilik ibí qande Suuriyak Baxaabaxsa le dariifal isí lowsiisih gubat haak g*ytimaamat yaaban baxsa luk Suuriyak inaytâ magaalah tan Dimishqhik 20 k.m Xexxaarat raqta Kutna diqsitta magaalak 3 k.m tan dariifa Israa-il Tankitte culak g*ytimta.

🔴Ameerikah Doolat Suuriya gabat akak radde islaamist kinniimih taagah keenik bohoy linom kee Suuriyak Faxe Qaynatih Tahdiid(bohoy) yemeetek Jurdaan kee Qiraakâ luk gacak faxxiima gacsa edde abenno axcuk Tiysixxige.

🔴 Iraan Doolat Israa-il Suuriyak Kalalí qandeh kambittet abtah tan maysattakooki kee Suuriyak baxaabaxsa le dariifat abtah tan lowsiis gita maliinooy suuriyah curriinoo kee moddaqiinot yaaqateenim kinnuuk baad doolatitte saddam faxximta axcuk seeco xayyoossem kee galli maroh eglah tibbo kaxxaam qagiib nel takke inte.

🔴 tonnaah Cizbullâ gaadile Israa-il suuriyat abtah tan maysattakooki kaxxam saddah tanim qaddoosse.

🔴 lowsiisseh tan Tengele gaadileelah miraaciini Yeyyeeqeh yan maybalaalaqal iyyeemih Suuriyah xintok Suuriyah xaylo Casbit haak Casbí addal uma digaalah maaqattooti beyteh sugteh tan maritteh migaaqitte ayyaaqe loonum qaddoosak Too Qaskar kee Amní abbobtih aracih oytatitte yaceeh yan marah Lakqoh acwa Aaxiginno axcuk yiysixxigen.

10/12/2024

Represent your country with a flag, let's see the country with the highest followers on this platform.

Me~ From Ethiopia 🇪🇹

ቲክ ቶክሮችሩሀማ :- 4 ዓመታት ኩላሊቶቼ ከጥቅም ውጪ ሆነው ወደ ሞት እየሄድኩኝ ባለበት ስአት አሁን ላይ ስማቸውን በሚዲያ መናገር የማልፈገው ቲክቶከሮችን እባካችሁ በLive ግቡ እና ብር ...
09/12/2024

ቲክ ቶክሮች

ሩሀማ :- 4 ዓመታት ኩላሊቶቼ ከጥቅም ውጪ ሆነው ወደ ሞት እየሄድኩኝ ባለበት ስአት

አሁን ላይ ስማቸውን በሚዲያ መናገር የማልፈገው ቲክቶከሮችን

እባካችሁ በLive ግቡ እና ብር አሰባሰቡልኝ ብዬ ለመንኳቸው

እነሱም :-

እሺ Live ገብተን ብር እናሰባስባለን ነገር ግን ከተሰበሰው ብር ላይ 30 ፐርሰንት ኮሚሽን ትከፍያለሽ አሉኝ ::

😮😮😮

ጉርሻ🌴🌴🌴

Great Afar follow like share 🙏

አሜሪካ በአሸባሪነት ፈርጃ ያለበትን ለጠቆመኝ አስር ሚሊየን ዶላር ከፍላለሁ ብላ ስትፈለገው የከረመችው የሶሪያ ታጣቂዎች መሪ አቡ ሞሐመድ አል ጆላኒ ቀጣዩ የሶሪያ መሪ ለመሆን ከጫፍ ደርሰዋል...
09/12/2024

አሜሪካ በአሸባሪነት ፈርጃ ያለበትን ለጠቆመኝ አስር ሚሊየን ዶላር ከፍላለሁ ብላ ስትፈለገው የከረመችው የሶሪያ ታጣቂዎች መሪ አቡ ሞሐመድ አል ጆላኒ ቀጣዩ የሶሪያ መሪ ለመሆን ከጫፍ ደርሰዋል።

CNN የመሳሰሉ የአሜሪካ ሚዲያዎችም ከዚህ በፊት ሲገልፁበት የነበረውን Terrorist, radical jihadist የሚሉ አገላለፃቸውን በማለዘብ Revolutionary ወደሚል እየቀየሩ ነው።

አሜሪካዊው ከ48 ዓመት እስር በኋላ በስህተት መታሰሩ ታወቀሲታሰር የ22 ዓመት ወጣት የነበረው ይህ ሰው አሁን ላይ የ70 ዓመት አዛውንት ሆኗልግለሰቡ ለተፈጸመበት ስህተት 175 ሺህ ዶላር ካ...
21/12/2023

አሜሪካዊው ከ48 ዓመት እስር በኋላ በስህተት መታሰሩ ታወቀ

ሲታሰር የ22 ዓመት ወጣት የነበረው ይህ ሰው አሁን ላይ የ70 ዓመት አዛውንት ሆኗል

ግለሰቡ ለተፈጸመበት ስህተት 175 ሺህ ዶላር ካሳ እንደሚከፈለው ተገልጿል

በአሜሪካ ኦክላሆማ ግዛት ይኖር የነበረው ግሊን ፓሉምቦ የተሰኘው ግለሰብ ከ48 ዓመት በፊት ነበር በግድያ ወንጀል ተጠርጥሮ በህግ ቁጥጥር ስር የዋለው።

ይህ ግለሰብ በወቅቱ የ22 ዓመት ወጣት የነበረ ሲሆን ላለፉት 48 ዓመታት ከ18 ቀናት ጊዜውን በእስር ቤት አሳልፏል።

ፓሊምቦ የተጠረጠረበትን የግድያ ወንጀል እንዳልፈጸመ በተደጋጋሚ ለፖሊስ እና ፍርድ ቤቶች ቢናገርም ሰሚ አጥቶ ቆይቷል።

ይሁንና ከሰሞኑ ይህ ሰው የፈጸምከው ወንጀል የለም፣ ላለፉት 48 ዓመታትም የታሰርከው በስህተት ነው ተብሎ ከእስር ተለቋል።

ይህን ተከትሎም ጉዳዩ በመላው ዓለም ትኩረት የሳበ ጉዳይ የሆነ ሲሆን በታሪክ በስህተት ረጅም ዓመታት የታሰረ ሰው ለመባልም በቅቷል።

ግለሰቡ በስህተት በእስር ቤት ለቆየባቸው ዓመታትም 175 ሺህ ዶላር ካሳ እንደሚከፈለው ኒዮርክ ፖስት ዘግቧል።

አሁን ነጻ የተባለው ይህ አሜሪካዊ በአልኮል መጠጥ መሸጫ መደብር ውስጥ ሰው ገድሏል በሚል በከባድ ነውጥ እና ግድያ ወንጀል የሞት ፍርድ ተላልፎበት የነበረ ቢሆንም የአሜሪካ ህግ የሞት ፍርድን እንዳትፈጽም የሚገድብ ህግ መውጣቱን ተከትሎ ውሳኔው ወደ እድሜ ልክ እስራት ሊቀየር ችሏል።(ዓል-ዓይን)

🙏

የሚሰራን ሰው ማበረታታት ይበልጥ የተሻለ ዉጤት እንዲያስመዘግብ ይረዳል  Greater Afar  ..✍️ለዛሬ ስለአንድ ብርቱ ሰው ያስተዋልኩትን በከፊል ላካፍላችሁ ወደድኩኝ 🙏🙏 ም/ኮሚሽ BiB...
20/12/2023

የሚሰራን ሰው ማበረታታት ይበልጥ የተሻለ ዉጤት እንዲያስመዘግብ ይረዳል

Greater Afar ..✍️

ለዛሬ ስለአንድ ብርቱ ሰው ያስተዋልኩትን በከፊል ላካፍላችሁ ወደድኩኝ 🙏🙏

ም/ኮሚሽ BiBilae Acmadዘመናዊ ሰራዊት ግንባታ እንዲሁም የሰራዊቱን የስነልቦና በማደስ ረገድ ጉልህ ሚና እየተጫወተ የሚገኝና ካሰብኩት በላይ በሳል አመራር እንደሆነ በተግባር ያየሁበት ድንቅ ሰው ነው

ምክንያቱም ኮሚሽነር BiBilqe Acmad Koreፍፁም ትሁት እሩህሩህ ፣ ሰራዊቱን አክባሪና አዳማጭ ፤ ሰራ ወዳጅ ታታሪ እንዲሁም ደሞ የመፍትሔ ሰው መሆናቸውን ስናገር ባየሁት ነገር ላይ ተንተርሼ ነው 👌

ያየሁትን ልንገራችሁ ➡ያው ም/ኮሚሽነር ቢልዔ የሰው ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሀላፊ እንደመሆኑ ባለጉዳዮች እንደምበዙበት ግልፅ ነው በቀን በትንሹ ከ30 በላይ ባለጉዳዮችን በተራ በተራ በቢሮው ሲያስተናግድ ባለጉዳዮቹ ጉዳያቸውን ጨርሶ ስወጡ ነገረ ሁኔታቸው ሁሉ ቀለል ብሏቸው በፈገግታ ስወጡ ነው የሚስተዋሉት ከፍትፍቱ ፊቱ ይባል የለ ጉዳያቸው በሰአቱ የማይፈታ እንኳን ከሆነ ጥሩ ፊት በመስጠት

በርግጥ ሁሉንም ሰው ማስደሰት የማይቻል ነገር ቢሆንም ግን ደሞ መልካም መስተንግዶ ቅን ምላሽና ስንቅ የሆነ ተስፋ ስታገኝ ጉዳይህ እንደተሳካልህ ሁሉ ይመስልሃል
በአጠቃላይ ከቢሮው ስወጡ ግን ከፍቶት የሚወጣ ሰው አላጋጠመኝም

ሌላው ቀርቶ ሁሉንም ባለጉዳዮች አስተናግዶ ካልሸኘ የምሳ ሰአት ሁሉ በቢሮው ስያሳልፍ በአይኔ አይቻለሁ 🙏🙏🙏

ከሁሉም የገረመኝ ደሞ
ኮሚሽነር #ቢልዔ ያን ሁሉ ሰው ሲያስተናግድ
የመሰላቸትም ሆነ የመነጫነጭ ባህሪይ በጭራሽ አይታይበትም በቃ ሁሉንም በፍቅር በፈገግታ በቀልድ እያዋዛ ቁምነገር እያስጨበጠ በተቻለው መጠን ችግራቸውን እየቀረፈ በፈገግታ መሸኘት ነው 🙏❤

በአጠቃላይ ኮሚሽነር #ቢልዔ በጣም ልብ-ሰፊና አስተዋይ አመራር መሆኑን ለመገንዘብ ችያለሁ🙏

የተከበሩ ኮሚሽነር በርታ በዚሁ ቀጥልበት
በአጭር ጊዜ ዉስጥ ብዙ ለውጦችን እንደምታስመዘግብ እምነቴ የፀና ነው🙏🙏

አመሰግናለሁ ..🙏🙏

Address

Awash

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Great Afar posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Great Afar:

Share