
14/05/2025
ከእግዚአብሔር ጋር ጉዞ ዋጋ አለው!
ኖህ መርከብ መስራት በጀመረ ጊዜ ዝናብ አልነበረም። እኔ እና እናንተም ዛሬ ስንተጋ ነገን በማለም ነው።
በራዕይ ውስጥ የብዙሃን እምነት እና ድጋፍ ከድል ማግስት እንጂ ከድል ፊት የቀደመ አለመሆኑን ጠንቅቄ አውቃለሁ።
የዛሬ 9 ዓመት ገደማ የሃይስኩል ተማሪ እያለሁ፤
በወቅቱ የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዞን ደረጃ በነበረበት ወቅት
በአንድ ትንሽዬ ካሜራ፣በአንድ ፕሮጀክተር እና በአንድ አነስተኛ የላፕቶፕ ኮንፒውተር
የተለያዩ ዞኖች፣ወረዳዎች እና የገጠር ከተማዎችን በመዞር
የክርስቲያን ተማሪዎች ህብረቶችን በማቋቋም
የመንፈሳዊ ትምህርቶችን እና በተፅዕኖ ፈጣሪነት ህይወት ላይ የሚያተኩሩ ሁለንተናዊ ለውጥ ለማምጣት የሚስችሉ ትምርቶችን እና ስልጠናዎችን በማዘጋጀት እና በማስተማር በምደክምበት በዚያን ጊዜ ነበር፤
አንድ ነገር ለህዝቤ እና ለማህበረሰቤ ከእግዚአብሔር ጋር በመሆን Qullaambe የተባለ ይህን የመሰለ እና የተወደደ ለሲዳማ ማህበረሰብ የወንጌል ድምፅ የሚሆን የ24ሰዓት የቴሌቪዥን ስርጭት ጣብያን ለማቋቋም በልቤ ለእራሴ ቃል የገባሁት(ራዕይን የወጠንኩት)።
ብዙ ድካም ተስፋ አስቆራጭ ትግል፤ መውጣት መውረድን በፍቃዴ ወደ ህይወቴ ያስገባሁት። እውነት ነው! ከእግዚአብሔር ጋር ጉዞ ዋጋ አለው!
የተወደዳችሁ የሀገሬ ልጆች፣ የሀገሬ መሪዎች እና የወንጌል አርበኛ አባቶች እና እናቶች እንዲሁም የወንጌል ባለ ድርሻ አካለት እና አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ፤
Qullaambe Tvን ለማቋቋም ስተጋ እና ስለፋ አንዳች በዓይን የሚታይ ደመና አልነበረም! ዝናብም የለም!
አቅሜ እግዚአብሔር አምላክ ነበር አሁንም ስቀጥል አቅሜ እርሱ ነው እና አመስግኑልኝ።
ሌላው ስድብ ባይገባኝም ሀሳብ እና አስተያየቶችን ለመቀበል ሁሌም ዝግጁ ነኝ።
ለአሳደገኝ ማህበረሰብ እና ለተፈጠርኩበት ዓላማ የምኖር የህዝብ ልጅ፣ ታናሽ የጌታ ባርያ(አገልጋይ) ነኝ እንጂ ፤
ወሬ እና አሉባልታ ያመጣኝ(የዘራኝ)፣ ትችት የሚያሳንሰኝ፣አድናቆት እና ጭብጨባ የሚያተልቀኝ ሰው አለመሆኔን አፅንኦት ሰጥቼ ለመግለፅ እወዳለሁ።
በመሆኑም Qullaambe Tv የማህበረሰባችን የወንጌል ድምፅ ነው፣ የእኛ ነው ይመለከተናል ለሚሉ ሁሉ፤
መልስን እንድሰጥ፣ ጥያቄን ላቀረቡልኝ የተወደዱ ወጣቶቾ በቅድሚያ ያለኝን ልባዊ ምስጋና እና አክብሮት በመግለፅ፤
እነርሱ ባስቀመጡት መንገድ ነገ ሀሙስ ማታ ከምሽቱ 3;00 ጀምሮ በtik-tok የማህበራዊ ትስስር መድረክ ላይ Live በመቅረብ ለሚነሱልኝ ማንኛውም አይነት ጥያቄዎች እና ሀሳቦች በቅንነት ምላሽን ለመስጠት ዝግጁ መሆኔን ላሳውቃችሁ እና እናንተንም ተገኝታችሁ ሀሳባችሁን እንድታቀርቡ ስል ለመጋበዝ እወዳለሁ።
አገልጋይ ሲሳይ ጢሞቴዎስ
የQullaambe Tv መስራች
እና
የቲዮስ ሚንስትሪ ባለራዕይ