Sidama federation

Sidama federation !!
!

እነዚህ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት በመዲናዋ አዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ በሶማሌ እና በሐረሪ ክልሎች የተለያዩ አካባቢዎች መሆኑም ተገልጿል።ተቋሙ አይኤስ ...
18/07/2025

እነዚህ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት በመዲናዋ አዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ በሶማሌ እና በሐረሪ ክልሎች የተለያዩ አካባቢዎች መሆኑም ተገልጿል።

ተቋሙ አይኤስ በኢትዮጵያ ያለውን የጥፋት ተልዕኮ ለማስፋፋት እና ምልመላ ለማከናወን የሃይማኖት ተቋማትን እንዲሁም ሃይማኖትን እንደ ሽፋን ይጠቀማል ብሏል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት 82 የአይኤስ አባላት በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ

ሲዳማ ቡና በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው የንግድ ምልክት ነው፤አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ (ዶ/ር) ሲዳማ ቡና በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው የንግድ ምልክት ነው፣ በ (WIPO) እውቅና...
17/07/2025

ሲዳማ ቡና በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው የንግድ ምልክት ነው፤

አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ (ዶ/ር)

ሲዳማ ቡና በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው የንግድ ምልክት ነው፣ በ (WIPO) እውቅና የተሰጠው፤ የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ጥበቃ የሚደረግለት የአእምሮአዊ ንብረት አካል ነው።

በ2012 እንደ አዉሮጳዉያኑ አቆጣጠር የጃፓን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ችሎት ሂደቶችን የመከታተል እድል አግኝቼ ነበር። እዛው በነበረኝ ቆይታ የሲዳማ ቡና፣ የሐረር ቡና እና ሌሎችንም የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች የሚያቀርቡት ቡና፤ ከኢትዮጵያም አልፎ ለአለም አቀፍ የአእምሯዊ ንብረት መሆናቸውን በይፋ እውቅና በመስጠት የተወሳነዉን አይቻለሁ፤

ጉዳዩ ክለቡ በህዝባችን ስም ስለመጠራት ከሆነ፤ በፖለቲካ መድረክ ልንወያይ እንችላለን። ነገር ግን፣ በአለምአቀፍ ጥበቃ የሚደረግለት የምርት ስምችን ላይ ጥላቻ ካለ፣ በሁሉም የህግ መንገዶች፤ አለም አቀፍ ፍርድ ቤቶችን ጨምሮ ፍትህን ለመከታተል ተዘጋጅተናል። አንዳንድ ግለሰቦች ስለዚህ ጉዳይ ያላቸው ግንዛቤ በጣም የተገደበ በመሆኑ በችግሩ ላይ ያለውን ነገር አስፈላጊነት አለመረዳታቸው ያሳዝናል። ብሏል

''Sidama Coffee is a globally recognized brand, acknowledged by WIPO as part of Ethiopia’s internationally protected intellectual property. I had the opportunity to oversee legal proceedings at Japan’s highest court, where the ruling favored Ethiopia — officially recognizing Sidama Coffee, Harar Coffee, and others as the intellectual property of Ethiopian farmers in 2012.

If the name of our people is an issue for discussion, we welcome to discuss that on a political platform. However, if there is hostility toward our globally protected brand, we are prepared to pursue justice through all available legal avenues — including international courts.

It’s unfortunate that some individuals’ understanding of this matter is so limited that they fail to grasp the significance of what’s at stake.''

ዶ/ር አምባሳደር ማርቆስ ተክለ

ከሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ የተሰጠ መግለጫ‎ሲዳማ ቡና ለዓለም አቀፉ ስፖርት ገላጋይ ፍ/ቤት/CAS/ ያቀረበው ይግባኝ ተቀባይነትን አግኝቷል !!ሐምሌ 10/2017 ዓ.ም (ባቱስ ቢሮ )‎‎ሲዳማ...
17/07/2025

ከሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ የተሰጠ መግለጫ

‎ሲዳማ ቡና ለዓለም አቀፉ ስፖርት ገላጋይ ፍ/ቤት/CAS/ ያቀረበው ይግባኝ ተቀባይነትን አግኝቷል !!

ሐምሌ 10/2017 ዓ.ም (ባቱስ ቢሮ )

‎ሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተወሰነበትን ዉሳኔ በመቃወም ለዓለም አቀፉ ስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት July 11, 2025 አቤቱታ ማስገባቱ ይታወቃል።

‎ክለቡ ለዓለም አቀፉ ስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት ያስገባው ይግባኝ ተቀባይነት አግኝቶ በኬዝ ቁጥር CAS 2025/A/11595/Sidama Bunna V. Ethiopian Football Federation CAS 17,July በሚል መመዝገቡን ለክለቡ ይፋዊ ኢ-ሜል አድራሻው ላይ በላከው ደብዳቤ አሳውቋል።

‎የዓለም አቀፉ ስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት ከ July 11/2025 ጀምሮ እስከ July 16/2025 ድረስ ከክለቡ በይግባኙ ዙሪያ አስፈላጊ መረጃዎችን እና ማብራሪያዎችን በኢሜል እየጠየቀና ከክለቡም እየተሰጠዉ ከቆየ በኋላ አስፈላጊ መረጃዎች በሙሉ መቅረባቸዉን አረጋግጦ July 17/2025 ጉዳዩን ለመመልከት በይፋ መቀበሉን አረጋግጧል።

‎CAS ጉዳዩን መቀበሉን ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በላከው ኢሜል መግለፁ የታወቀ ሲሆን እንዲሁም ለዓለም የእግር ኳስ ማህበር FIFA እና ለአፍሪካ የእግር ኳስ ኮንፈደረሽን /CAF/ በግልባጭ አሳዉቋል።

‎በቀጣይም አሰራሩ በሚፈቅድ መልኩ የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ቦርድ ለመላው የክለቡ ደጋፊዎች እና የስፖርት ቤተሰብ በሙሉ ጉዳዩ የደረሰበትን እየተከታተለ እንደሚያሳዉቅ እየገለፀ የክለቡ ደጋፊዎች በሙሉ ነገሮችን በትዕግስት እየተከታተሉ እንዲቆዩ ሲል መልዕክቱን ያስተላልፋል።

እንኳን ደስ አለዎት የተከበሩ አቶ ዳዊት ዳንግሶ! መልካምና የተሳካ የስራ ጊዜ እንድሆንሎት እንመኛለን!
17/07/2025

እንኳን ደስ አለዎት የተከበሩ አቶ ዳዊት ዳንግሶ! መልካምና የተሳካ የስራ ጊዜ እንድሆንሎት እንመኛለን!

05/07/2025
የሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ ቦርድ እና የክለቡ የደጋፊዎች ማህበር በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋልሰኔ 28/2017 የሲዳማ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ ቦርድ እና ...
05/07/2025

የሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ ቦርድ እና የክለቡ የደጋፊዎች ማህበር በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል

ሰኔ 28/2017 የሲዳማ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

የሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ ቦርድ እና የክለቡ የደጋፊዎች ማህበር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፈዴሬሽን የሰጠዉን ዉሳኔ አስመልክቶ በጣምራ መግለጫ ሰጥተዋል።

መግለጫ የሰጡት የሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጃጎ አገኘሁ እንደገለፁት የሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ ሰኔ 1/2017ዓ.ም የመላዉ ኢትዮጵያ ጨዋታ በግልፅ ተጫዉቶ በማሸነፍ ዋንጫ ስቀበል በወቅቱ የቀረቡ ቅሬታዎች አለመኖሩን ተናግረዋል።

ቦርዱ የተሰጠዉን ዉሳኔ አምርሮ የሚቃወም መሆኑንና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሰጠውን ዉሳኔ ዳግም እንዲያጠን አሳስበዋል።የሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ ቦርድ ፍትህ ፍለጋ አስፈላጊውን ሁሉ አድርጎ ሁሉንም ህጋዊ የፍትህ አማራጮችን ለመጠቀም ዝግጁ መሆኑንም አቶ ጃጎ አገኘሁ አስረድተዋል።

የሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ ቦርድ አባል አቶ ወሰንየለህ ስምዖን በበኩላቸውየኢትዮዽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሰጠዉ ዉሳኔ ትክክል እንዳልሆነ ገልፀዉ በጨዋታዉ ላይ ምንም አይነት ቅሬታ ባልቀረበበት የተሰጠዉ ዉሳኔ የክለቡን ስነልቦና ለመስበርና የስፖርት ቤተሰብን በመናቅ የተሰጠ ዉሳኔ ስለሚመስል ዉሳኔዉ እንደገና መጤን አለበት ብለዋል።
አክለዉም ህብረተሰቡ በማህበራዊ ሚዲያ በሚሰራጩ በሀሰተኛ ወሬዎች መደናገር እንደለለበትና ሚዲያዎችም ለህብረተሰቡ ትክክለኛውን መረጃ ማስተላለፍ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የሲዳማ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነርና የክለቡ የቦርድ አባል አቶ ፍረዉ አሬራ በበኩላቸዉ ውሳነዉ የስፖርት ቤተሰቦችን ቅር የሚያሰኝ በመሆኑ ዳግም ማጤን እንዳለበት አሳስበዋል።

የሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ የደጋፊዎች ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ ደጄነ ማርቆስ ስናገሩ ከዓመታት ዝጅት በኋላ የተገኘ ዉጤት በመሆኑ ህጋዊ ህደቶችን ተከትለን እስከ መከመጨረሻዉ ታግለን መብታችን ለማሰከበር ዝግጁ ነን ብለዋል።
በአጠቃላይ ወጥነት የጎደለዉና ቀድሞ አሳውቆ ጉዳቶችና ስብራቶች እንዳይኖሩ ከመከላከል ጋር በተያያዘ ሰፊ ክፍተት ያለው በመሆኑ መታረም እንዳለበት ቦርዱና የደጋፊ ማህበሩ በጋራ አሳስበዋል።

ለበለጠ መረጃ
➚ድረ ገጽ፦ https://sidamanrsps.gov.et
➚ፌስቡክ፡- Sidama National Regional State Communication Affairs Bureau
➚ዩትዩብ፦https://youtube.com/.bureau?si=r5EAWg8x4kXmLqQN
➚WhatsApp https://whatsapp.com/channel/0029VadMPA2DDmFbMwfTjG3l
➚ቴሌግራም፦ https://t.me/SidamaCommunicationbureau

⚠️ FIFA Rules on Competition Integrity and Title OwnershipFIFA strictly prohibits the transfer of competition titles, cu...
03/07/2025

⚠️ FIFA Rules on Competition Integrity and Title Ownership

FIFA strictly prohibits the transfer of competition titles, cups, or trophies between clubs outside of sporting results. Here's why such actions are not recognized and may lead to sanctions:

⚖️ 1. Integrity of Competitions

According to Article 18 of the FIFA Statutes:

“Leagues and clubs must ensure that all matches and competitions are played in accordance with the principles of fair play, integrity, and sporting merit.”

🔒 This means:

Titles can only be won through official match results.

Clubs cannot donate, transfer, or assign league trophies to other clubs by agreement or symbolism.

🏛 2. National Associations Must Uphold Integrity

Each national football federation (e.g., the Ethiopian Football Federation – EFF) is mandated by FIFA to:

Operate independently, without political or emotional interference.

Enforce that titles and trophies are awarded only based on match outcomes.

Reject symbolic gestures that undermine competition fairness or statistical accuracy.

📚 3. Historical Record and Recognition

FIFA, CAF, and national federations:

Only recognize the team that officially won on the field.

Will not register any symbolic "title transfer" in historical records.

Maintain a strict database of winners based on sporting results.

📌 Example:
If Club A wins the league but later announces that they are "giving the trophy" to Club B, only Club A will remain the official champion.

🟥 4. Potential Violations

Such actions may constitute:

Bringing the game into disrepute

Sporting fraud or manipulation

Violation of Article 27 (FIFA Code of Ethics)

Undermining the authority of the federation

FIFA or CAF may launch an integrity investigation and impose:

Warnings or fines

Suspensions

Disqualification of clubs or officials

🔍 Enforcement Example:

If the EFF were to recognize a symbolic "trophy transfer" between clubs, it could trigger:

Review by CAF and FIFA

Questions of impartiality and

 # 👇   ከውሳኔው በኋላ አሱ በሚመራበት ሀገር ላይ የተለያዩ ጨዋታዎችን ሲያደርጉና በተለይ በተለይ እራሱ በሜዳ ሄዶ የታደመበትና በመጨረሻም በራሱ እውቅና ሰጥቶ ዋንጫና ሜዳሊያ በሸለመበት ...
02/07/2025

# 👇

ከውሳኔው በኋላ አሱ በሚመራበት ሀገር ላይ የተለያዩ ጨዋታዎችን ሲያደርጉና በተለይ በተለይ እራሱ በሜዳ ሄዶ የታደመበትና በመጨረሻም በራሱ እውቅና ሰጥቶ ዋንጫና ሜዳሊያ በሸለመበት ጉዳይ ላይ ዋንጫ ከተወሰደ ከሳምንታት በኋላ ወደኋላ በመሄድ ጨዋታዎችንና በራሱ የሰጠውን ዋንጫ የሚነጥቅ ውሳኔ የሰጠው በፊፋ አሰራርና ህግ መሠረት ስነስረዓታዊ ፍትህ ወይም procedural justice የጣሰ መሆኑንና የስፖርት ግልግል ፍ/ቤት ወይም ውድቅ ያደረገባቸው የተለያዩ ኬዞች አሉ👇👇👇

1. በ2001 GC, ፋይል ቁጥር CAS 2001/A/317 AEK Athens SK Slavia Prague V. UEFA
የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር (UEFA) መጀመሪያ ጨዋታው ሲካሄድ ዝም ብሎ አጫውተው በኋላ ላይ የተቀጡ ተጨዋቾች በመሳተፋቸው ምክንያት ውጤቱን የሰረዘበት ጉዳይ ወደ ቀርቦ የግልግል ፍ/ቤቱ ቃል በቃል ሲተረጎም:
"UEFA ከጨዋታው በፊት በመጀመሪያ እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው መጫወት የሌለባቸውን ተጫዋቾችን ካጫወተ በኋላ ውጤቱን ውድቅ ማድረጉ የስነስረዓት ፍትሃዊነትን ወይም procedural fairness የጣሰ ነው የUEFA ውሳኔ ብሎ ውድቅ አድርጎበታል።

☝️ ነው።

2. በ2005, ፋይል ቁጥር CAS 2005/A/983&984 Maccabi Haifa V. UEFA ላይ EUFA ማካቢ የተባለ ተጨዋች መጫወት የለሌበትን የተለያዩ ጨዋታ ከተጫወተ በኋላ UEFA ዝም ብሎ ቆይቶ በኋላ ወደኋላ የወሰነውን ውሳኔ ውድቅ ያደገበት ነው። የእስፖርት የግልግል ፍ/ቤቱ ወይም CAS ውድቅ ያደረገበት ምክንያት አንደ ጨዋታው እንዲቀጥል የለቀቀው ወደኋላ ሄዶ ውድቅ ማድረግ ተገማችነትንና የስነስረዓታዊ ፍትህ የሚቃረን ነው በሚል ነው።

3.2010 ላይ ስሙ ያልተጠቀሰ ክለብ እና የሆነ ሀገር ፌደሬሽን ጋር በተደረገው ክርክር ፋይል ቁጥር CAS 2010/A/2187 ላይ ፌደሬሽኑ የሆነ ክለብ የተቀጡ ተጫዋቾችን ሲያጫውት እያየ ከቆየ በኋላ በሆነ ጊዜ የክለቡን ውጤት ውድቅ ያደረገበት ሲሆን, CAS "ፌደሬሽኑ ግራ ማጋባት ሂደት ውስጥ የራሱ አስተዋፆ ስላለው ውድቅ ማድረጉ ተገቢ አይደለም ብሎ ወስኗል። ቃል በቃል "Federation contributed to the confusion" በሚል ውድቅ አድርጎበታል።

4. በ2008, ፋይል ቁጥር CAS 2008/A/1583፣ Danilov v. Football Association of Serbia ጉዳይ ላይም የግልግል ፍ/ቤቱ ማህበሩ ከራሱ ድርጊት ጋር የሚጋጭ ተመሳሳይ ውሳኔ ውድቅ አድርጎበታል።

5. በ2013፣ ፋይል ቁጥር CAS 2013/A/3091 – Al-Masry SC v. Egyptian FA በሆነ ውሳኔ የግብፅ እግር ኳስ ማህበር አል ማስሪ በተሰኘ ክለብ ላይ ዘግይቶ እርምጃ በመውሰዱ ምክንያት ብቻ የግልግል ፍርድ ቤቱ (CAS) ውሳኔውን ሽሯል። ውሳኔውን የሻረበት ምክንያት "finality of competion result, lack of prompt decision, unpredictability and lack of procedural fairness" የሚል ነው። ሀሳቡ በመሰረቱ፣ አንድ ውድድር እንዲካሄት እስከተፈቀደ ድረስ ውጤት ቀድሞ እየታወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው በመጀመሪያ ሳይከለከል በኋላ ወደኋላ ሄዶ መሠረዝ አይቻልም።via professor tesema

Address

Awassa

Opening Hours

Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sidama federation posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share