Mathe Mengesha Yute-ማቴ መንገሻ ዩቴ

Mathe Mengesha Yute-ማቴ መንገሻ ዩቴ My mentor and guidance is God!

"አንተ በሌላው ሎሌ የምትፈርድ ማን ነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወድቅ ለገዛ ጌታው ነው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ሊያቆመው ይችላልና ይቆማል።" ሮሜ 14:4"እንግዲህ ከዛሬ ጀምሮ እርስ በርሳች...
23/10/2025

"አንተ በሌላው ሎሌ የምትፈርድ ማን ነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወድቅ ለገዛ ጌታው ነው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ሊያቆመው ይችላልና ይቆማል።" ሮሜ 14:4

"እንግዲህ ከዛሬ ጀምሮ እርስ በርሳችን አንፈራረድ፤ ይልቁን ግን ለወንድም እንቅፋትን ወይም ማሰናከያን ማንም እንዳያኖርበት ይህን ቁረጡ።" ሮሜ 14:13

“ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም። ” — 1ኛ ዮሐንስ 5፥12

ከማይጠፋ ዘር የተወለደ ልጁነት! ዘሩ በቅሏል! እህት ዘሪቱ ከበደን ሳስብ የተረዳሁት ይኼ ነው። መጽሐፏን ሳነብ ሌላውን አውቃለሁ።

ተባረኪ!🙏❤🖤




Madrid እንግላንድ መጥቶ ቀርቶ በቤታቸው አይተውታል። አምና ዋናውን፣ አሁን ደግሞ ሁለተኛውን ማድረድ Humble አድርገን Wanda Metropolitano ሸኝተናል።በዛሬው ጨዋታዎች 43 ጎ...
21/10/2025

Madrid እንግላንድ መጥቶ ቀርቶ በቤታቸው አይተውታል። አምና ዋናውን፣ አሁን ደግሞ ሁለተኛውን ማድረድ Humble አድርገን Wanda Metropolitano ሸኝተናል።

በዛሬው ጨዋታዎች 43 ጎሎች በአንድ ቀን በመቆጠር ከፍተኛ በአንድ ቀን የተቆጠረ ጎል ብዛት ሆኖም ተመዝግቧል።

Gooners❤❤❤

እንደሀገር ትልቅ ሰው በሞት ተነጥቀናል!እኝህ አባት ለሀገራችን ሰላም ዋጋ ከፍለዋል፤ ፊለፊት ሰላምንና ፍቅርን ሰብከዋል። ዛሬ ህልፈታቸውን ስሰማ በከፍተኛ ሀዘን ነው። እግዚአብሔር አምላክ ያ...
19/10/2025

እንደሀገር ትልቅ ሰው በሞት ተነጥቀናል!

እኝህ አባት ለሀገራችን ሰላም ዋጋ ከፍለዋል፤ ፊለፊት ሰላምንና ፍቅርን ሰብከዋል።

ዛሬ ህልፈታቸውን ስሰማ በከፍተኛ ሀዘን ነው። እግዚአብሔር አምላክ ያዘነ ልብ ሁሉ ያጽናና!

Dialysis ማዕከል በቅርበት መከፈቱ ያስመሰግናል!!ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ምክንያቶች ኩላሊት ድካም (Irreversible Kidney Failure) ችግር በወጣቱ ማህበረሰብ ክፍል በሰ...
17/10/2025

Dialysis ማዕከል በቅርበት መከፈቱ ያስመሰግናል!!

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ምክንያቶች ኩላሊት ድካም (Irreversible Kidney Failure) ችግር በወጣቱ ማህበረሰብ ክፍል በሰፊው ይስተዋላል። ይኼን ችግር በቋሚነት ለመፍታት ከሁሉም አካላት ከፍተኛ ጥረትና ተግባር ይጠበቃል።

የኩላሊትን አገልግሎት (Kidney function) በመተካት ብዙ ሰዎችን ሕይወት ለማራዘምና ለኩላሊት ንቅለ ተከላ ጊዜ ለመግዛትና ቅድሜ ሁኔታዎችን ለመጨረስ Dialysis ወሳኝና አይተኬ ሚና አለው።

እንደ ሀዋሳ ከተማ እንደዚህ ያሉ የህክምና ተቋማት (ማዕከላት) መገንባታቸው ኩላሊት ድካም ችግር ለሚያጋጥማቸው ታካሚዎች፣ ለታካሚ ቤተሰብና በህክምና ዘርፍ ላለ ሙያተኛ ከፍተኛ እፎይታ እንደሚሰጡ አምናለሁ።

ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ማዕከሉን እውን በማድረጉ ደስታም ተሰምቶኛል።

ይህ ማዕከል እውን እንዲሆን የተለያየ ሚና የተጫወቱ ወገኖችን ማመስገን እፈልጋለሁ።👏👏👏Well-done🙏



100 ብር ለሕይወት ብርሃን ህንጻ!🛐
14/10/2025

100 ብር ለሕይወት ብርሃን ህንጻ!🛐

13/10/2025
Abdel Fattah El-Sisi...blah blah...blah...taking measures....blah...blah...blah....Not failing to address the nation wit...
12/10/2025

Abdel Fattah El-Sisi...blah blah...blah...taking measures....blah...blah...blah....Not failing to address the nation with void words and statements.

GERD is functioning and in full function. Full stop‼️

Just continue your media propaganda!!Ethiopia will and surely plannig to develop other GERD on its waters! Just enjoy the show!

President Abdel-Fattah El-Sisi warned that Egypt “will not stand idly" in the face of what he called Ethiopia’s “irresponsible approach” to operating the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD), saying Cairo would take “all necessary measures” to defend its water security.

ወንድሜ   (Son of Christ forever)፣ ስለአንተ እግዚአብሔር ይክበር!በምረቃህ ቀን በቦታው እኛም ልንገኝ አንተም ልትገኝ አልቻልክም። ነገር ግን ጸሎትን የሚሰማ፣ በቅርብ ሆኖ የሚ...
09/10/2025

ወንድሜ (Son of Christ forever)፣ ስለአንተ እግዚአብሔር ይክበር!

በምረቃህ ቀን በቦታው እኛም ልንገኝ አንተም ልትገኝ አልቻልክም። ነገር ግን ጸሎትን የሚሰማ፣ በቅርብ ሆኖ የሚረዳ የዘለዓለም አምላክና አባት ይባረክ!

ከኮይሻ (ኮንታ) ስራ ቦታ ጅማ ዩንቨርስቲ 177 ኪሎሜትሮችን በመመላለስ ተምረሃል። ብዙ ዓይነት የምድር ፈተና ተጋፍጠሃል። የምታመልከው አምላክ ድል ሰጥቶሀል። የረዳህ ጌታ ይመስገን።

ምረቃህ በተቃረበ ሰዓት በሞትና በሕይወት መካከል የህክምና እርዳታ ላይ ነበርህ። በተፈጠረው ህመም ተደናግጠን ነበር። በመንገድ ላይ ከሥራ ባልደረቦቼ ጋር የነበረው በዕንባ የታጀበ ጸሎት ለዘመናት የሚረሳ አይሆንም። በጸሎታቸው ሀይልን ያደረጉ የእግዚአብሔር ሰዎች ናቸው። ጸሎታቸው ለዘለዓለም የተሰማ ይሁን!!

በቀኑ ጅማ መድረስ ለእኔ የዓመት ያህል የራቀ ነበር። በዚያ ጣር ወቅት የስጋ ዘመድ በርቀት ምክንያት ቤተሰብ መሆን አልተቻለም። ጅማ የነበሩ የሥራ ባልደረባህ ቤተሰቦች የሚገርሙ የፍቅር ሰዎች ናቸው። ከሥራ ቦታህ ለማስታመም ከኮይሻ ወንጌል አማኞች ህብረት የተመደበ ወንድም አንዳርጌ አስረስ (Andarge Asres) የተባረከ ወንድም ነው። በህብረቱ የነበሩ ወንድሞችና እህቶች እንደጌታ ሰዎች ናቸው። በህብረታቸው የተረገጠ ምድር ሁሉ ይሰጣቸው! በእነርሱ የተጀመረ መንፈሳዊ ሥራ የሚበዛ እና የተባረከ ይሁን።

ዛሬ ደህና ሆነህ ጓወን ለብሰህ ሳይ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ። ስለእግዚአብሔር ፈውስና ታምራት የእኛ ቤተሰብ ምስክር ነው!

እግዚአብሔር መልካም አምላክ ነው!! ያድናል ለስሙ ክብር ያቆማል!!

09/10/2025
ዛሬ በጣም ተከፍቼ ውያለሁ!ከማዘንና ከመጸለይም ውጪ ሌላ የታየኝም ነገር የለም።እህቴ ስምረት ዮሴፍ በስጋ እንደተለየችን ከተነገረኝ ደቂቃ ጀምሮ ልበ ከባድ ህመምና መከፋት ውስጥ ውሏል።በሲዳማ...
04/10/2025

ዛሬ በጣም ተከፍቼ ውያለሁ!

ከማዘንና ከመጸለይም ውጪ ሌላ የታየኝም ነገር የለም።

እህቴ ስምረት ዮሴፍ በስጋ እንደተለየችን ከተነገረኝ ደቂቃ ጀምሮ ልበ ከባድ ህመምና መከፋት ውስጥ ውሏል።

በሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሥራ ስትጀምር (ሲትቀጠር) የሚመራው ተቋም አንዱ ቤተሰብ እንደምሆናት እንዳረጋግጥ ተጠይቄ ነበር። ምን ያህል የፈለገችው መልስ አግኝታ እንደነበር ባላረጋግጥም ደስተኛ መሆኗን አውርታን አበረታተን አልፈናል።

ስራዋ ላይ ጥንቁቅና ታታሪ ልጅ ናት። ቢሮ መግባቷን እንጂ ድምጻና አረማመዷ ከመጠን በላይ ለሰው ልጅ አሳቢ ያስብላል። ገንዘብ እንዳለው ሰው እንኳን ስትሆን አንድ አፍታም ቢሆን አላየሁም። ስነ-ስርዓቷና ለመንፈሳዊ ነገር ያላት አቋም ሁለም የልጅ ብልህ ያስብላል።

መታመሟንና ህክምና ላይ እንዳለች አንድ ቤተሰብ ከነገረኝ 4ኛ ቀን ውስጥ ወደ ያገለገለችው ጌታ ተጠርታ መሄዷን ሰማሁ። ከምድራዊ ቤተሰብ ተለይታ ትልቅ ቤተሰብንም አግኝታለች።

የቅዱሷን ሞት በእግዚአብሔር ፊት የተከበረ ነው። ይኼን እውነታ ከመቀበል ውጪ ሌላ ተስፋ የለንም።

የእግዚአብሔር ስም ብሩክ ይሁን!

ለእህቷና ለወንድሟ፣ ለቤተሰብ፣ ለሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ቤተሰብ መጽናናትን እመኛለሁ።

Qoqqowoho, Hawaasanna Zoonnate biilto assini'neri baalu, Danchare Loossine Daga'ne Hornya Buuxisiissinanni Gede Maganu W...
04/10/2025

Qoqqowoho, Hawaasanna Zoonnate biilto assini'neri baalu, Danchare Loossine Daga'ne Hornya Buuxisiissinanni Gede Maganu Wolqa Ikko'ne!!

03/10/2025

85 በመቶ የሚሆኑትን ምሩቃን የሥራ ዕድል ባለቤት ያደረገ ተቋም

በ1996 ዓ.ም ተጠሪነቱን ለሐዋሳ ተግባረ ዕድ ኮሌጅ በማድረግ ተቋቋመ፤ በ1996 ዓም ራሱን የቻለ ኮሌጅ ሆኖ ተመሠረተ፤ በ2003 ዓ.ም ደግሞ ‹‹ፖሊ ቴክኒክ›› የሚል ስያሜን በማግኘት እንደ አዲስ ተደራጀ፡፡

ይህ በአጠቃላይ 27 ዓመታትን ያስቆጠረው የሐዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተቋማዊ ጉዞ ነው፡፡ ኮሌጁ በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ከ2መቶ ሺ በላይ ሰልጣኞችን አብቅቶ ለሥራ ገበያው ማቅረቡን የኮሌጁ ዲን አቶ መልካሙ ባራሳ ይናገራሉ፡፡

የበቃ የሰው ኃይል ማፍራት፣ የሰልጣኝ አሰልጣኝ ልማት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር ኮሌጁ በዋነኛነት የሚከውናቸው ተግባራት ናቸው፡፡

ከክህሎት ልማት አንፃር በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የተቀረፀውን አዲሱን የዘርፉ እሳቤ ለመተግበር የሚያስችሉ ተግባራትን እየከወነ እንደሚገኝ አቶ መልካሙ ባራሳ ያስረዳሉ፡፡

አካባቢያዊ ፀጋን ያማከለና ፍላጎትን መሰረት ያደረገ ሥልጠና፣ ዲጂታላይዜሽንና የውስጥ ገቢን ማሳደግ ቅድሚያ አግኝተው በኮሌጁ እየተከናወኑ የሚገኙ የሪፎርም ተግባራት ናቸው፡፡

በ2022 ዓ.ም በምስራቅ አፍሪካ መሪ ተቋም ሆኖ የመውጣት ራዕይን የሰነቀው የሐዋሳ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አካባቢዊ ፀጋን የለየ ስልጠናን በመስጠት ረገድም ቀዳሚ ተቋም ነው፡፡

ጨርቃጨርቅና ጋርመንት፣ ሆቴልና ቱሪዝም፣ አውቶሞቲቭ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የውሃ ቴክኖሎጂና የተለያዩ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች በኮሌጁ በዋነኛነት የሚሰጡ የስልጠና መስኮች ናቸው፡፡ በእነዚህ መስኮች ሰልጥነው የሥራ ገበያውን የሚቀላቀሉ ምሩቃን ያለቸው ብቃትና ተወዳዳሪነት ኮሌጁ በብዙ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ አዎንታዊ ገፅታን እንዲላበስ እንዳስቻለው አቶ መልካሙ ይናገራሉ፡፡
ኮሌጁ የISO 2001/2018 የጥራት ሥራ አመራር ስርዓትን ሙሉ በሙሉ በመተግበር የምስክር ወረቀት ባለቤት መሆኑ የስልጠና ጥራት አንፃር ካለበት ደረጃ ይበልጥ እንዲሻገር ዕድል ሰጥቶታል፡፡
የአሰልጣኝ መምህራን ብቃት በአጠቃላይ ስልጠናው ጥራት ላይ ጉልህ ተፅዕኖ ያለው እንደመሆኑ ኮሌጁ በA ደረጃ 47 አሰልጣኞችን መዝኖ ማብቃቱን የኮሌጁ ዲን ይገልፃሉ፡፡

በጨርቃጨርቅና ጋርመንት ዘርፍ በኮሌጁ የተቋቋመው መለስተኛ ኢንዱስትሪ ሰልጣኞች በተጨባጭ የምርት ሂደት አልፈው ስልጠናቸውን እንዲከታተሉ እያደረገም ይገኛል፡፡

ከስልጠናው ጎን ለጎንም የውስጥ ገቢ ከማመንጨት አንፃር ጉልህ ሚና እንዳለው የሚናገሩት ዲን መላኩ በራሳ የተለያዩ ምርቶችን አምርተው ለገበያ የሚያቀርቡና የማማከር አገልግሎት የሚሰጡ ኢንተርፕራይዞች በሰባት ዘርፍ በኮሌጁ መመስረታቸውን ያስረዳሉ፡፡

በኮሌጁ ውስጥ በተቋቋመው የቢዝነስ ኢንኩቤሽን ማዕከል አማካኝነት ሰልጣኞች ተገቢው ግንዛቤ ተፈጥሮላቸው እንዲደራጁ ይደረጋል፡፡ ስልጠናቸውን ካጠናቀቁ በኋላም ለሚመሰርቷቸው ኢንተርፕራይዞች የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍን ከኮሌጁ ያገኛሉ፡፡

ኮሌጁ የምሩቃን የሥራ ማግኘት ዕድልን አስመልክቶ በየዓመቱ ጥናት የሚያካሄድ ሲሆን በዚሁ መሰረት 85 በመቶ ምርቃት ከስልጠና በኋላ የሥራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው ጥናቱ አመላክቷል፡፡

በ2018 የትምህርት ዘመን 1,600 ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማስተናገድ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎቹን አጠናቋል፡፡ ሰልጣኞች በኮሌጅ ቆይታቸው ከሚጨብጡት ክህሎት በተጨማሪ ማንነታቸውን ለመገንባትና ለሙያ ፍቅር እንዲያድርባቸው ለማስቻል የህይወት ክህሎትና የሀገር ወዳድነት ስልጠናዎችን እንዲያገኙ እንደሚደረግ አቶ መልካሙ ባራሳ ያብራራሉ፡፡

መስከረም 23/2018 ዓ.ም ፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: t.me/fdre_mols
TikTok: tiktok.com/
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y

Address

Wolde Amanuel Street
Awassa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mathe Mengesha Yute-ማቴ መንገሻ ዩቴ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share