Fitsum Tsegaw

Fitsum Tsegaw “ዕዝራም የእግዚአብሔርን ሕግ ይፈልግና ያደርግ ዘንድ፥ ለእስራኤልም ሥርዓትንና ፍርድን ያስተምር ዘንድ ልቡን አዘጋጅቶ ነበር።”
— ዕዝራ 7፥10

01/03/2026

ዕቅበተ እምነት የክርስትናን ያክል ዕድሜ ጠገብ ነው። ለርትእ በመወገን ሐዋርያቱን የቀደመ አልነበረም። ትንሳኤ ሙታንን ሰዎች ሲክዱና ሲጠራጠሩ የጠረቀ ሙግት ያቀረበው የጠርሴሱ ቅዱስ ጳውሎስ ነው። (1ኛ ቆሮ 15)። ክርስቶስ በስጋ የተገለጠ መኾኑ ሲካድ (Docetism) ቀድሞ ሙግት ያቀረበ ቅዱስ ዮሐንስ ነው። (1ዮሐ 1:1-4)። ስለ ተቀበልነው ተስፋ ጥያቄ ሲነሳ ምላሽ ለመስጠት የተዘጋጀን እንድንኾንም ያሳሰበን አእማዱ ቅዱስ ጴጥሮስ ነው። (1ኛ ጴጥ 3:15)።

እቅበተ እምነታዊ ጥናቶች ካበረከቱ ሰዎች መኻል ናቸው። ጆን ሊኒንክስ፣ አለቪን ፕላቲንጋ(የኔ የብዙ ግዜ የመጀመሪያ ምርጫዬ)፣ ፍራንሲስ ሻፈርና አሊስተር ማግራዝም ሰፊ እቅበተ እምነታዊ ስራን ለቤተ ክርስቲያን ያበረከቱ ምሁራን ናቸው። በኛም ሀገር የዶ/ር ተስፋዬ ሮበሌን ትጋትና ጥረት ማንሳት እንችላለን።

በምሁራንና ቤተ ክርስቲያንን በሚወዱ አሳቢዎች ይመራ የነበረው ይኽ አገልግሎት በአላዋቂ ሳሚዎች እየተጠለፈና እየተመረዘ ነው። ነገር በማይጠግቡና በሚያመነዥጉ ዕቡያን እየተጎሳቆለ ነው። ከክብሩ እያሽቆለቆለ ነው። ተልእኮውንና ግቡን እየሳተ ነው። ከእውቀትና እውነት እየፈታ ነው። ከንቱ ብሽሽቃችንና ማለቂያ የሌለው ንትርካችን ዘርፉንና አገልግሎቱን ምን ያክል እንዳስነቀፈ ባወቅን! ክርስትናንንና የወንድማማች ኅብረትን ምን ያክል እንዳጎደፍን ባስተዋልን! ለችኮላችንና ድፍረታችን፤ ለጥበታችንና ርኅራኄ ማጣታችን እቅበተ እምነት ዋጋ ሊከፍል አይገባውም። ለክብር ጥማታችንና ራስን መቆለላችን ምካቴ ክርስትና መደቆስ አይኖርበትም። እውነትን በፍቅር መያዝ ባልሰለጠኑ ሰነፎች እጅ እውነትም እውቀትም ፍቅርም መገፋት አይኖርባቸውም!
ኢብሳ ቡርቃ

21/12/2025

ተሰቅሎ መሞት የሞት ሞት በመሆኑ ክርስትና መስቀልን ምልክቱ ማረጉ በራሱ ግራ አጋቢ ነው። ከዚህ የተነሳ መስቀሉ ስለ ሃይማኖት ያለንን ግንዛቤ ሁሉ ቢያናጋና ጥያቄ ውስጥ ቢያስገባ አይገርምም። ግሪኮውያንም ሆነ አይሁዳውያን በአንድነት የሚቃወሙት ለዚህ ነው! የሰዎች ጥበብ ይህን አያደርግም።...ግን ከሰዎች ጥበብ ይልቅ የእግዚአብሔር ሞኝነት (ሞኝነት የሚመስል ድርጊት) በጥበብ ይልቃል። የእግዚአብሔር ድካም (ድካም የሚመስል ድርጊት) ከሰዎች ብርታት ይልቃል።

ጳውሎስ ፍቃዱ

Address

Awassa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fitsum Tsegaw posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share