
11/03/2025
የክልሉ መንግስት በማይመጥነዉ ጥቃቅን ጉዳይ ላይ ከመጠመድ ይልቅ፤ ለተነሱት ጥያቄዎች የተሻለ መፍትሔ ማቅረብ ይገባዋል።
ባለመስራት ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ በማጣት ይህን ያህል የተቸገሩ በመሆናቸው ይመስለኛል።
የተነሱ ጥያቄዎች የለፖለቲካ ምላሽ የምፈልጉ ሆኖ ሳለ ዙሪያ መለስ ሽማግሌዎች ተመልምለው የመጡትን ሰብስበው የፖለቲካ ጥያቀዎች እንድላወሱ በመፍቀዱ መንግስት የመጀመሪያውን ነጥብ እንዲጥል አድርጓል።
አሁንም በተመሳሳይ ባልሰለጠነ መንገድ በምንም መመዘኛ የማይዛመድ ነገር፣ ተራ ግለሰቦችን(ባለሀብት ተብየዎችን) ሰብስቦ የመልስ ምት (attacking against person) ለማድረግ መሞከር፣ አስፈላጊ አይደለም። ይባስ ብለዉ ግለሰብን ለማጥቃት ignorant ሰብስቦ “የክልሉ ትግል ወቅት ዬት ነበሩ” እያስባለ፣ በይፋዊ ማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ማስተላለፉ፣ አንድ መንግስት ነኝ ባይ ዘንድ የማይጠበቅ፤ ለህዝባችንም የማይመጥን ተግባር ሆኖ አግኝቻለሁ።
በትግል ወቅትማ የት ነበሩ ከተባባለ ማን ምን ሲያደርግ ነበር በምለዉ ለብዙዎች ዘንድ ብዙ መልስ ስለምኖር አያስከድም። እንዶዉም ያኔ “ቻቡሎ” (Gobba gosa gaadhitanni no) ዘፈን ትዝ ይለኛል። ያኔ ግን አሁን ስልጣን የተቆጣጠረው ሃይል ዬት ነበር ብባል አብዛኛው የደኢህዴን ደጃፍ ስመላለስ የነበረ መሆኑን መዘንጋት አያስፈልግም።