15/03/2024
ሰላም ሰላም ውድ ቤተሰቦች!
በየዕለት አኗኗራችን የድራማ ትሪያንግል ምንድነው?
የድራማ ትሪያንግል በየዕለት ግንኙነቶቻችን ውስጥ ትክክለኛ ግንኙነት የሚምስል ነገር ግን አሉታዊ መስተጋብርን የሚገልጽ ስነ ልቦናዊ ፅንሰ-ሀሳብ ነው፡፡ ይህ ጽንሰ-ሃሳብ ሰዎች በየዕለት ግንኙነቶቻቸው ውስጥ ሳያስቡት ከሚከተሉት ሶስት ሚናዎች ውስጥ ራሳቸውን ሊያግኙት ይችላሉ ይለናል፡፡
እነርሱም፡- የተጎጂ ሚና (the victim role)፣ የተንከባካቢ ሚና (the Rescuer role) እና የአሳዳጅ ወይም የጎጂ ሚና (the Persecutor role) ናቸው:: ይህንንም በቀላሉ ለመረዳት የሚከተለዉን በአንድ ቤተሰብ ውስጥ የተፈጠረ ቀላል የሚመስል የየቀን ቤተሰባዊ የግንኙነት ውጥረት እንመልከት፡፡
እነዚህ ቤተሰቦች በአንድ አነስተኛ ሰፈር ውስጥ የሚኖሩ አቶ ባልቻ (አባት)፣ ወ/ሮ አልማዝ (እናት)፣ እና አሌክስ (ልጅ) ናቸው። እነዚህ ቤተሰቦች በፍቅር፣ በሳቅ እና አልፎ አልፎም በተለመዱ የየዕለት የህይወት ውጣ ውረዶች የሚኖሩ ሲሆን ከስነ ልቡና አንፃር ግን ግንኙነታቸው ሲፈተሽ ጤናማ ግንኙነት አይመስልም።
ታዲያ በዚሁ ቤተሰብ ውስጥ አሌክስ የተባለው ባለብሩህ እና ህልመኛ ታዳጊ ልጃቸው እራሱን በትምህርት፣ ከመደበኛ ትምህርት ውጭ ባሉ እንቅስቃሴዎች እና ከማሀበረሰቡ በሚጠበቁ አንዳንድ የህይወት ልምምዶች ጋር እየታገለ ነበር። በዚሀም የተነሳ ከመጠን በላይ መጨናነቅ እና ያለመቻል ስሜት ስለተሰማው ከወላጆቹ ጋር ያለውን ጥብቅ ግንኙነት በመቀነስ ብዙ ጊዜ ክፍሉ ውስጥ ብቻውን ያዘ ወትራል- ( የተጎጂነት ሚና - The Victim Role)
እንዲሁም በዚሁ ቤተስብ ውስጥ የአሌክስ እናት ወይዘሮ አልማዝ የልጇን የአሌክስን መጨናነቅ እና ከቤተስብ መገለል በማስታዋል አሌክስን ወደክፍሉ በመሄድ ልዩ እንክብካቤ በማሳየት እና የትምህርት ቤት ስራውን ሳይቀር በማገዝ እንዲሁም ልጃቸው ቤት ውስጥ ያሉበትን አንዳንድ ሃላፊነቶች በመወጣት ጭንቀቱን ለማርገብ ይጥራሉ- (የአዳኝ (ላልቶ) -The Rescuer Role)
በተቃራኒው የአሌክስ አባት አቶ ባልቻ ሳያስቡት ለልጃቸውን የአካዳሚክ ስኬት በማሰብ ልጃቸው ከሚጠበቀው በታች በትምሀርት እና በህይወት ደካማ መሆን እንደማይገባው በማሰታወስ አሌክስ ከሚጠበቀው በታች ሲወድቅ ትችት አዘል ምክራቸውን በመሰንዘር እና ብስጭታቸውን በመግለጽ የቤተሰቡን የግንኙነት ይበልጥ አከረሩት። ይህም የአቶ ባልቻ ጥብቅ ባህሪ እና ከፍተኛ የህየወት መመሪያ አይነት ምክር የአሌክስን የብቃት ማነስ ስሜት የበለጠ አባባሰው - (የአሳዳጅ ሚና -the persecutor Role)
ታዲያ በቤተሰቡ ውስጥ በየቀኑ አለመግባባቶች እየጨመሩ ሄዱና የድራማ ትሪያንግል ሚናዎች ይበልጡኑ በመክረር ፤ አሌክስም በቤተሰቡ ውስጥ የሚጠበቅበት የህይወት ክብደት ይበልጥ እየተሰማው እና እነዚህን ጫናዎች ለመቋቋም እየታገለ ቀጠለ፡፡
የአሌክስ እናት ወ/ሮ አልማዝም ሳያስቡት የተንከባካቢነት ሚና ውስጥ በመግባት አሌክስን ከተጨማሪ ጭንቀት ለመጠበቅ እና በሚችሉት መንገድ ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ መታተ ራቸውን ቀጠሉ፡፡ እንዲሁም የአሌክስ አባት አቶ ባልቻ ሳያስቡት የተቺ፣ የስርዓት አስያዥ እና የተቆጪውን ሚና በመያዝ ሳያውቁ የአሌክስን የውድቀት እና የብቃት ማነስ ስሜት በማባባስ የድራማ ትራያንግል ዑደቱ (አሳዳጅ - ተሳዳጅ እና አዳኝ) በቤተሰቡ ውስጥ ቀጠለ።
አባት----የታባህ እና በርታ😐 !
እናት-----ተወዉ ምን ያድርግህ🙄
ልጅ------ አባዬ መጣብኝ😒 አይነት ማለት ነው
ለበለጠ ዩትዩባችንን ስብስክራብ ያድርጉ