የጽዮን ልጆች

የጽዮን ልጆች እስራኤል ሆይ ስማ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው።

ከሰማይም፡— ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸው። መንፈስ፡— አዎን፥ ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ፥ ሥራቸውም ይከተላቸዋል ይላል ብለህ ጻፍ የሚል ድምፅ ሰማሁ። ራዕይ 14:13መልካ...
24/08/2025

ከሰማይም፡— ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸው። መንፈስ፡— አዎን፥ ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ፥ ሥራቸውም ይከተላቸዋል ይላል ብለህ ጻፍ የሚል ድምፅ ሰማሁ። ራዕይ 14:13

መልካም ዕረፍት አባታችን❤😍

Share it!!
23/08/2025

Share it!!

አድን/2*/ በምድረበዳ በጥልቁ ያሉትንየሱስ ጽድቅ የተራቡ የተጠሙትን
17/08/2025

አድን/2*/ በምድረበዳ በጥልቁ ያሉትን
የሱስ ጽድቅ የተራቡ የተጠሙትን

14/08/2025

ያውቅበታል ውብ ማድረግን ሁሉን በጊዜው/4*
የአመታት እንባ በእሱ ይታበሳል
የዘመናት ጩኸት ለካ ይመለሳል

በታማኙ ኢየሱስ ይመለሳል
ከታማኙ ጌታ መልስ ይመጣል/2*

በምህረቱ ባለጠጋአቤቱ እኔ ማን ነኝ ቤቴስ ምንድነውበእኔ ላይ የምህረትህ የደግነትህ ባለጠግነት የተገለጠውምህረት እየበዛልኝጥበቃህ ሳይለየኝበፍቅር የተቀበልከኝጌታ ሆይ እኔ ማን ነኝ1. አንዳች...
10/08/2025

በምህረቱ ባለጠጋ

አቤቱ እኔ ማን ነኝ ቤቴስ ምንድነው
በእኔ ላይ የምህረትህ የደግነትህ ባለጠግነት የተገለጠው
ምህረት እየበዛልኝ
ጥበቃህ ሳይለየኝ
በፍቅር የተቀበልከኝ
ጌታ ሆይ እኔ ማን ነኝ

1. አንዳች ታሪክ የለኝ በኩራት የምናገረው
ከምህረትህ በቀር ዛሬን አቆመኝ ምለው
ካንተ ፀጋ በቀር አሻገረኝ የምለው
እንደ ብርቱ ቆሜ ዛሬ የምዘምረው
በእኔ ብርታት ሳይሆን የሱስ በምህረትህ ነው
እኔ ችዬ ሳይሆን አንተ አግዘኸኝ ነው

አላልፈውም ያልኩትን ምህረትህ አሳለፈኝ
አልችለውም ያልኩትን በፀጋህ ተሻገርኩኝ
ይህ ከባድ ነው ያልኩትን ደግፈህ አሻገርከኝ

ምህረትህ ከለለኝ (እየሱሴ)*4
ፀጋህ አሻገረኝ (አባዬ)

2. ያ የማይታለፍ የመሰለው ለሊት
ባንተ በቸርነትህ ብርሃን የወጣበት
ያ እንዳይነጋ የረዘመው ለሊት
ባንተ በምህረትህ ብዛት ነጋበት

በምህረትህ ባለፀጋ*2 እየሱስ
በቸርነትህ ባለፀጋ*2 እየሱስ

እንደ አበደ ሰው የሚያደርገኝ
ክብሬን አስጥሎ ሚያዘምረኝ
ብዙ ምህረት በህይወቴ አለ
ያኔ በመስቀል የተከፈለ

ያየሁ ነኝ ብዙ ምህረት ያየሁ ነኝ
ያየሁ ነኝ ብዙ ደግነት ያየሁ ነኝ
ያየሁ ነኝ ብዙ ቸርነት ያየሁ ነኝ
ያየሁ ነኝ ብዙ በጎነት ያየሁ ነኝ
ሲረዳኝ አይቻለሁ
ሲያግዘኝ አይቻለሁ
ደግፎኝ አይቻለሁ
ምህረቱን እዘምራለሁ
አይቻለሁ የሱን ምህረት አይቻለሁ
አይቻለሁ ብዙ ደግነት አይቻለሁ
አይቻለሁ የሱን ቸርነት አይቻለሁ
አይቻለሁ ብዙ በጎነት አይቻለሁ

ዛሬ ላለሁበት መሠረቴ
የመቆሜ ምክንያት ለኔ ብርታቴ
ታሪኬን ለውጦት ነው እንዲህ ያማረብኝ
ከቶ የማልዘነጋው ውለታ አለብኝ

እንዴት ልርሳው ከየት እንዳነሳኝ
አልዘነጋም ማን እንደነበርኩኝ
አመዴን/ትቢያዬን ከላዬ አራግፎልኝ
ለዚህ ክብር እኔን እንዳበቃኝ

ልርሳው ብል እንኳን ችዬ እንዳልረሳው /የማልረሳው/
በህይወቴ ሞልቷል /በዝቷል/ የእርሱ ውለታው
ያሳለፈኝን ያንን ዘመን
እኔስ አልረሳም ደግነቱን /ውለታውን/

አልረሳም ያን ዘመን
>> ያለፍኩትን
አልረሳም ምህረቱን
>> ደግነቱን
>> ያለፍኩትን
>> ውለታውን
አንደበቴ ከሚናገረው በላይ
ከንፈሮቼ ከሚያወሩልህ በላይ
ሰዎች እኔን ሲያዩ ምህረትህን ያያሉ
ሰዎች እኔን ሲያዩ ቸርነትህን ያያሉ
ሰዎች እኔን ሲያዩ ያሳለፍከኝን ያያሉ
ሰዎች እኔን ሲያዩ በአንተ ይፅናናሉ
ሰዎች እኔን ሲያዩ ደግነትህን ያያሉ
ሰዎች እኔን ሲያዩ ታምራትህን ያያሉ
ሰዎች እኔን ሲያዩ አንተን ያመሰግናሉ
ሰዎች እኔን ሲያዩ ለክብርህ ይዘምራሉ
አንተ እንደረዳኸኝ ያያሉ
አባት እንደሆንከኝ ያያሉ
እንደ ደጋገፍከኝ ያያሉ
ዛሬን እንዳቆምከኝ ያያሉ
ምስጋናህ ይዘመርልኝ
ማዳንህ ይነገርልኝ
አንተ እንደረዳኸኝ
እኔ ምስክር ነኝ ።

25/05/2025


በሐዋሳ ሚሊኒየም አደባባይ በተካሄደው 18ኛው ዙር ዓመታዊ ጉባዔ ላይ 702 ሰዎች ወደ መዳን መጥተዋል።

" እግዚአብሔርም በምድር ሁሉ ላይ ይነግሣል፤ በዚያ ቀን እግዚአብሔር አንድ፥ ስሙም አንድ ይሆናል። "(ትንቢተ ዘካርያስ 14:9)
16/03/2025

" እግዚአብሔርም በምድር ሁሉ ላይ ይነግሣል፤ በዚያ ቀን እግዚአብሔር አንድ፥ ስሙም አንድ ይሆናል። "
(ትንቢተ ዘካርያስ 14:9)

ታላቁ ሃይል በዋራ ቤቴል ኢየሱስ ክብሩን ገለጠበወዳጆቹ ፊት ተለወጠ መልኩ አንጸባርቆ ስያበራበዚያች በቅዱሱ ተራራማንም አልቆመም በፊቱ ስገልጥ በግርማ መለኮቱወደቁ ሐዋርያቱእኔ ጴጥሮስ፡ዮሐንስ...
05/03/2025

ታላቁ ሃይል በዋራ ቤቴል

ኢየሱስ ክብሩን ገለጠ
በወዳጆቹ ፊት ተለወጠ
መልኩ አንጸባርቆ ስያበራ
በዚያች በቅዱሱ ተራራ
ማንም አልቆመም በፊቱ
ስገልጥ በግርማ መለኮቱ
ወደቁ ሐዋርያቱ
እኔ ጴጥሮስ፡ዮሐንስ ተስኗቸው ማየቱ።
አሁንም አምላኬ በቅዱስህ ስፍራ
በጻድቃን ጉባኤ በጽዮን ተራራ
ልጆችህ በሚሰበሰቡበት ከወገን ከነገድ
ያ ታላቁ ሃይልህ በዋራ ቤቴል ይውረድ።

✍ በወ/ም ተክሌ ታደሰ

እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን እያላን እነሆ በጉጉት ስንጠባበቅ የነበረውን በኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን አለታ ቅርንጫፍ ሰበካ ዓመታዊ ኮንፈረንስ ለመካሄድ ጥቅት ስዓታት ብቻ መቅረቱን እ...
09/01/2025

እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን እያላን እነሆ በጉጉት ስንጠባበቅ የነበረውን በኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን አለታ ቅርንጫፍ ሰበካ ዓመታዊ ኮንፈረንስ ለመካሄድ ጥቅት ስዓታት ብቻ መቅረቱን እየገለፀን ይህንን የበረከት ኮንፈረንስ ወንድሞች እህቶች ታላቅ የእግዚአብሔር ጉብኝት ያለበት ጉባኤ እርሷና ዘመድ አዝማድ አዳዲስ ነፍሳትንም ጭምር መጥተው እንድካፈሉ ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች

አድራሻ አለታ ወንዶ ከተማ እናት አጥቢያ ግብ ውስጥ ነው።

31/12/2024
Big shout out to my newest top fans! Gzaw Egese
31/12/2024

Big shout out to my newest top fans! Gzaw Egese

31/12/2024

እንዘጋጅ ኢየሱስን ለማየት!!

Address

Negele Borena
Awassa

Telephone

+251941008089

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የጽዮን ልጆች posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share