Yetseda HIWOT RADIO Program

  • Home
  • Yetseda HIWOT RADIO Program

Yetseda HIWOT RADIO Program Hiwot Events and promotion activites page

13/05/2025
እኚህ ሀዋሳዎች ምንኛ በረቱአንዱ ለአዳማ አንደኛውም ለአዲስለአመት መሻገሪያ መባ አበረከቱዳግማዊ አሰፋ በምስራቅ ተጉዞ አዳማ ይገኛል፦ይቅር ሳንባባል አመቱ እንዳያልፈን፣ቂምና ጥላቻን እዚሁ አ...
28/08/2024

እኚህ ሀዋሳዎች ምንኛ በረቱ
አንዱ ለአዳማ
አንደኛውም ለአዲስ
ለአመት መሻገሪያ መባ አበረከቱ

ዳግማዊ አሰፋ በምስራቅ ተጉዞ አዳማ ይገኛል፦

ይቅር ሳንባባል አመቱ እንዳያልፈን፣
ቂምና ጥላቻን እዚሁ አስቀርተን ፣
በአሮጌው ካኖረነው ስለሚፈነዳ፣
አዲስ ወይናችንን በአዲስ አቁማዳ፣
ከልብሳችን ይልቅ ልቦናችን ይጽዳ።
እያለ ይጣራል

በለው ገበየሁም በዋና ከተማ አዲስ አበባ ላይ፦
ከየአኗኗራችን በማንኪያ ቆንጥሮ
ፊደልን በመልኩ በስርአት ሰድሮ
የተሸፈነውን ማንነታችንን፣
ያልተገለጠውን የየውስጣችንን፣
መሆን ያለበትን የወደፊታችንን፣
እንኳን መሃይም ሆንኩ በሚል የዳቦ ስም
የየልባችንን ይነግረናል በግጥም

እንግዲህ ያለውን የሰጠ ንፉግ አይባልም ብለን ሁለቱንም አይኖቻችንን ልከንላችኃል በዚያ ያላችሁ እንድትጠቀሙ ይሁን🥰🥰🥰

አስደሳች ዜና  ከሜሪጆይ ሀዋሳ የህክምና ማዕከል # ነጌሌ አርሲ ጠቅላላ ሆስፒታል እና የህክምና ኮሌጅ ከፍተኛ ስፔሻሊስቶች ሀኪሞችን ከውጭ ሀገር በማስመጣት ከህክምና ማዕከላችን ጋር በመተባበ...
26/08/2024

አስደሳች ዜና ከሜሪጆይ ሀዋሳ የህክምና ማዕከል
# ነጌሌ አርሲ ጠቅላላ ሆስፒታል እና የህክምና ኮሌጅ ከፍተኛ ስፔሻሊስቶች ሀኪሞችን ከውጭ ሀገር በማስመጣት ከህክምና ማዕከላችን ጋር በመተባበር
👉 የአይን ሞራ ግርዶሽ ነፃ የህክምና ድጋፍ ለማድረግ የቅድመ ማጣራት ምዝገባ በዛሬው ዕለት ጀምሮአል።
👉 ለአንድ ሳምንትም ቀጥሎ ይሰነብታል።
👉 በመሆኑም ይህን ዕድል ለመጠቀም ዲያስፖራ መንደር ሜሪጆይ አረጋዊያን ማዕከል ጊቢ በሚገኘው የህክምና ማዕከላችን በስራ ሰአት በአካል በመምጣት አሊያም
በስልክ ቁጥሮቻችን 046-2-21-87-14/0955-46-46-46 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
በዚህ አጋጣሚ ቀደም ሲል አሮጌ አየር ማረፊያ የነበረው ሜሪጆይ ሀዋሳ ህክምና ማዕከል ወደ ዲያስፖራ አረጋዊያን ማዕከል መዛወሩን ለማሳወቅ እንወዳለን!
ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ! ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ🙏

ይድረስ በመላው አለም ለምትገኙ ኢትዮጵያዊያን🙏ቤተሰብ ለአመታት ባልተመለሰ ጥያቄ ተጨንቋል!
11/08/2024

ይድረስ በመላው አለም ለምትገኙ ኢትዮጵያዊያን🙏ቤተሰብ ለአመታት ባልተመለሰ ጥያቄ ተጨንቋል!

Naol(ናኦል) Hospital Hawassa:                ዶ.ር ትዕዛዙ ተፈራ                                             ሲኒየር  ኮንሰልታንት  የጠቅላላ...
12/07/2024

Naol(ናኦል) Hospital Hawassa:
ዶ.ር ትዕዛዙ ተፈራ ሲኒየር ኮንሰልታንት የጠቅላላ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ፥ የፕላስስቲክ ሪኮንትራክቲቭ ቀዶ ህክምና ስብ ስፔሻሊስት.
*Tezazu Teffera Tekle MD Consultant General and Plastic and Reconstructive Surgeon
*Smile Train Partner GS ACS 2010
*Assistant professor of Surgery
👉ላለፉት ሁለት አስራት አመታት በላይ በሺዎች የሚቆጠሩ የተሳካ ቀዶ ጥገናዎችን ያከናውኑ (High Volume Surgeon)
👉በሙያቸው አለም አቅፍ ሽልማቶችን ያገኙ
👉በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ፋኩሊቲ በርካታ ተተኪ ሀኪሞችን በማፍራት ያበረከቱና እያበረከቱ የሚገኙ በዘርፉ በሀገራችን ካሉ ተጠቃሽ ሀኪሞች መሃል ናቸው፡፡

ዶክተር ሳምሶን ጀማል
ሲኒየር ኤክስፐርት የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት፥የሴት ብልት ፥የቱቦና ፊንጢጣ መላላት ቀዶ ጠጋኝ፡፡
Senior Expert Obstetrician Gynecologist & Female pelvic Floor Reconstructive Surgeon.
👉 ከ 20 አመት በላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ቀዶ ጥገናዎችን በተሳካ ሁኔታ ያካሄዱ (High Volume Surgeon)
👉በዲላ፥ ሆሳእና እንዲሁም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል በእናቶችና ህፃናት ጤና የትምህርት ክፍሉን ጭምሮ የሙያ አሻራቸውን ያኖሩ፥
👉ለበርካታ ተተኪዎች መፍራት እንዲሁም ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ሙያቸውን ፈልገው ለሚመጡ እናቶች በቅንነትና በልዩ እንንክብካቤ እያገለገሉ የሚገኙ ጉምቱ ባለሙያ ናቸው፡፡

25/01/2024

እናግዛት
በተለይ አርባምንጭ ያላችሁ በቅርበት ብታገኟት🙏
እህታችን በውስጥ የላከችልኝ መልዕክት ነው፦
ቸግሮኛል የአንድ ጊዜ ብቻ እገዛችሁን እፈልጋለሁ ትላለች።
የምኖረው አርባ ምንጭ ነው። በጤና ሳይንስ በድግሪ ተመርቄአለሁ COCም አልፌአለሁ ነገር ግን ተወዳድሬ ስራ ለማግኘት ጂንካ ሄጄ ያለፍኩበትን ማስረጃ ለማምጣት የትራንስፖርት ቸገረኝ።
በተጨማሪም አባቴ ማረሚያ ገብቶ ስለነበር ተቸግራ ያስተማረችኝ እናቴና ቤተሰቤ በአሁኑ ጊዜ የአስቤዛም እየቸገረን ነው። በተማርኩበትም ይሁን ሌላ ስራ ብቻ እስካገኝ አግዙኝ። ብድራችሁን ለእናንተም ባይሆን ለሌላ ለተቸገረ እመልሳለሁ ትላለች።
ስራም ያላችሁ ዕድሉን ብታመቻቹላት ከፈጣሪ ታገኛላችሁ!
1000155832553
ፍሬሕይወት ዓለማየሁ
📞0934760113ደውሉላት
የአቅማችሁን አግዟት!
አንድ ዜጋ ማዳን ቀላል አይደለም!
🙏ስለምታደርጉት አመሰግናለሁ🙏
🙏ተባረኩልኝ🙏🙏🙏❤❤❤

በመላው አለም ለምትገኙ የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ🙏በአሉ የሰላም ፣ የምህረት፣ የፍቅርና የመተሳሰብ እንዲሆንልን ሕይወት ኢቨንትስና ፕሮሞሽን አጥብቆ ይመ...
19/01/2024

በመላው አለም ለምትገኙ የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ🙏በአሉ የሰላም ፣ የምህረት፣ የፍቅርና የመተሳሰብ እንዲሆንልን ሕይወት ኢቨንትስና ፕሮሞሽን አጥብቆ ይመኛል🙏👏❤

ከየትኛውም የውስጥና የውጭ ደዌ የመረረና የከፋ ህመም በበታችነት ስሜት ውስጥ መቆየት። የሰው ልጅ  ፣ በኑሮ ደረጃ፣ በትምህርት ደረጃ፣ በስልጣን ደረጃ እና በሌሎችም ሊለያይ ይችላል። ግልጽ ...
15/01/2024

ከየትኛውም የውስጥና የውጭ ደዌ የመረረና የከፋ ህመም በበታችነት ስሜት ውስጥ መቆየት።
የሰው ልጅ ፣ በኑሮ ደረጃ፣ በትምህርት ደረጃ፣ በስልጣን ደረጃ እና በሌሎችም ሊለያይ ይችላል። ግልጽ ነው ይለያያልም። የበታች ነኝ ብሎ ማሰብን የመሰለ ግን ክፉ ደዌ የለም። ምክንያቱም ከላይ የጠቀስናቸው መለያየቶች በጊዜ ሂደት መስተካከል ቢችሉ እንኳን አንዴ እኔ የበታች ነኝ ፣ ሰዎች አይወዱኝም፣ አይቀበሉኝም፣ አያከብሩኝም እና ሌላም የምናስብ ከሆነ ሁሌ ለዚህ አሉታዊ አስተሳሰባችን ተገዢ ስለምንሆን ያለንበትን ደረጃ አምኖ መቀበል ይከብደናል።
ስለሆነም ያ የውስጣችንን ትግል ያሸነፍን የሚመስለን ሌሎች ላይ ሀይለኛ በመሆን፣ በመኮፈስ፣ ከአገልጋይነት ይልቅ መገልገልን በመፈለግ እንጠመዳለን። በመጨረሻም የምንፈልገውን ሰላምና ክብር፣ ፍቅርና መልካም ግንኙነትን አጥተን ከራሳችንም ከሰውም ሳንስማማ ለመኖር እንገደዳለን።
ወዳጄ ሆይ የዚህ ምድር ቆይታችን አጭር ናት ነጻ ሁን፣ ሆደ ሰፊ ሁን፣ ከማንም የማትበልጥ ከማንምም የማታንስ መሆንህን እመን!
"ሰው" ሁንና ደስ እያለህ እለፍ🙏 ማንነትህን በሌሎች አታስለካ! አትለካካ! በቃ ቀለል ብለህ ዛሬን አሁንን ኑር🙏

መላው ኢትዮጵያዊያንና በተለይም የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ2016 የጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል እንኳን አደረሳችሁ🙏በአሉ ለህይወታችን የምንፈልገውን ሁሉ ...
06/01/2024

መላው ኢትዮጵያዊያንና በተለይም የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ2016 የጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል እንኳን አደረሳችሁ🙏በአሉ ለህይወታችን የምንፈልገውን ሁሉ ሳይሆን የሚያስፈልገንን በረከት የሚያሰጠን መልካም እንዲሆንልን እንመኛለን🙏❤❤❤

የ2016 የገና በአልን አስመልክቶ በሀዋሳ ብራይት ኦቲዝም ማዕከል ግሩም ጊዜ አሳለፍን።ኦቲዝምነት "የተለየ አፈጣጠር ይዞ መወለድ እንጂ ህመም አይደለም" ግን ደግሞ የእያንዳዱ ልጅ የአእምሮ ...
04/01/2024

የ2016 የገና በአልን አስመልክቶ በሀዋሳ ብራይት ኦቲዝም ማዕከል ግሩም ጊዜ አሳለፍን።
ኦቲዝምነት "የተለየ አፈጣጠር ይዞ መወለድ እንጂ ህመም አይደለም" ግን ደግሞ የእያንዳዱ ልጅ የአእምሮ አሠራርና አፈጣጠር በጣም የተለያየ በመሆኑ ምክንያት በማዕከል ውስጥ እነዚህን ልጆች ለማወቅና እንደማንኛውም ሰው ወደ ተለመደው አኗኗር ለማምጣት ረጅም ጊዜ፣ ትኩረት እና የሰው ኃይል ይፈልጋል። ለ5ህፃን 1 መምህር ይፈልጋል። በጣም ዋጋ ያስከፍላል። ሆኖም ሁሉም ውድ ከሆነው ከሰው ልጅ አይበልጥም!
በዚህ መንገድ አልፈው እየተማሩ ካሉት የማዕከሉ ተማሪዎች መሀል ሲዘምሩ፣ድራማ ሲያቀርቡ እና ግጥም ሲያቀርቡ ማየት እንደተአምር የሚቆጠር ነው። ዋጋ እየከፈሉ የሚገኙ የማዕከሉ መስራች ወ/ሮ ትዕግስት አበበ፣መምህራኖችና ወላጆች ክብር ይገባቸዋል።
ልትጎበኟቸው፣ ልታግዟቸው ለምትፈልጉ:-
አድራሻቸው ፦ ሀዋሳ ኢንተርናሽናል ስቴዲየም አጠገብ☎️ 0916863189 ነው

02/01/2024

እናስተዋውቅዎ!!!
🙏 የትኛውን አገልግሎት ይፈልጋሉ?
🙏 ነፍስያዎ መደገፍ የሚፈልገው አገልግሎትስ የቱ ነው?
በሀዋሳ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የበጎ አድራጎት ማህበራትና ተቋማት ጥቆማ
ክፍል 1
1.ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ(ሀዋሳ ሜሪ ጆይ አረጋዊያን ማዕከል፣(ሜሪ ጆይ ወጣቶች ማዕከል) እና (የክሊኒክ አገልግሎት)
👉 መስራች:- ሲ/ር ዘቢደር ዘውዴ(ኢትዮጵያዊት)
👉ተደራሽ የሚያደርጋቸው የህ/ሰብ ክፍሎች:- ህፃናት፣ ወጣቶች፣ አረጋዊያን
አድራሻ:- ዋና ጽ/ቤት እና ክሊኒክ አሮጌ አየር ማረፊያ
:- ወጣቶች ማዕከል አዲስ ከተማ ክ/ከተማ
፦ አረጋዊያን ማዕከል ፥ ዲያስፖራ መንደር
☎️0955-46-46-46/046-2-20-47-05/046-2-12-87-14

2. ሮኆቦት የበጎ አድራጎት ድርጅት
👉መስራች፦ አቶ አዲሴ ማኬቦ(ኢትዮጵያዊ)
👉ተደራሽ የሚያደርገው ፦ ተጥለው የተገኙ ከ1 ቀን ጀምሮ ያሉ ህፃናት ሲሆኑ ፍቃደኛ አሳዳጊ ቤተሰብ እስኪያገኙ በማቆየት ይንከባከባል።
አድራሻ:- ሀዋሳ አላሙራ 2ኛ ደረጃ ት/ት ቤት አጠገብ
☎️0964-12-37-80/0916-03-57-00

3. ጣሊታ ራይዝ አፕ የህፃናት እንክብካቤ ማዕከል(ይርጋለም) እና
ሴፍ ሀውስ (ሀዋሳ)
👉መስራች ወ/ሮ አትክልት ጃንካ(ኢትዮጵያዊት)
👉ተደራሽ የሚያደርጋቸው የህ/ሰብ ክፍሎች፦ ተጥለው የተገኙ ህፃናት ማቆያና መንከባከቢያ እንዲሁም
👉በፆታዊ ጥቃት ምክንያት ለችግር የተጋለጡ ሴቶች ማረፊያና እንክብካቤ ማዕከል
☎️0922-17-48-46/0925-41-54-09

4. ብራይት ኦቲዝም ሴንተር
👉መስራች :- ወ/ሮ ትዕግስት አበበ(ኢትዮጵያዊት)
👉 ተደራሽ የሚያደርገው ፦ ኦቲስቲክ የሆኑ ህፃናትን
አድራሻ፦ ሀዋሳ ኢንተርናሽናል ስቴዲየም አጠገብ
☎️ 0916863189

5. በጎ ልቦች የበጎ አድራጎት ማህበር
👉መስራች ወ/ሮ ሠውነት አሸናፊ (ኢትዮጵያዊት)
👉ተደራሽ ያደረጋቸው የህ/ሰብ ክፍሎች ፦ የተለያዩ በችግር ውስጥ የሚገኙ ሲሆኑ በተለይ በመንግስት ትምህርት ቤት የሚማሩና የምግብ ችግር ያለባቸውን ህፃናት ማህበረሰቡን በማስተባበር ቁርስ መመገብ ።
አድራሻ ፦ ሀዋሳ ባህል አዳራሽ ወጣቶች ማዕከል
☎️0911992312

Address


Telephone

+251912066903

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yetseda HIWOT RADIO Program posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share