Zeynu aba xubale/ አባ ዡባሌ

Zeynu aba xubale/ አባ ዡባሌ Provides Latest informations and personal openions of latest poletical, social and economical situat

27/07/2025
‎ሙሽሮች የተሳተፉበት የአረንጓዴ አሻራ በአልቾ ውሪሮ ************‎በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን በምትገኘው የአልቾ ውሪሮ ወረዳ የተሞሸሩት አቶ ባህረዲን ኑሬ እና ሙንተሀ ሱል...
26/07/2025

‎ሙሽሮች የተሳተፉበት የአረንጓዴ አሻራ በአልቾ ውሪሮ
************

‎በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን በምትገኘው የአልቾ ውሪሮ ወረዳ የተሞሸሩት አቶ ባህረዲን ኑሬ እና ሙንተሀ ሱልጣን በሰርጋቸው እለት ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።

ሙሽሮቹ ከሚዜዎቻቸው እና ከአጃቢዎቻቸው ጋር በጋራ በመሆን ነው አረንጓዴ አሻራቸውን በማሳረፍ ለአካባቢያቸው ምሳሊያዊ የሆነውን ተግባር መፈፀም የቻሉት።

በኢትዮጵያ ዘንድሮ 7.5 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት ሙሽሮቹ "እኛም ኃላፊነት አለብን" በማለት አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።

"በመትከል ማንሰራራት" በ7ኛ ዓመት 700 ሚሊዮን ችግኞች በአንድ ጀምበር የፊታችን ሐሙስ - ሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በመላው አገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በጋራ ይተክላሉ።

በላሉ ኢታላ

#አረንጓዴዐሻራ #ኢቢሲ

11/07/2025
28/06/2025

በዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደርና በዙሪያው ለሚገኙ የሙስሊም ጀመዓ ከዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር እስልምና ምክር ቤት(መጅሊስ) የተላለፈ መልዕክት

ነገ ማለትም ዕለተ እሁድ ልክ ከጧቱ 3ት ሰዓት ላይ በዓለም ገበያ ሁለ–ገብ ስቴዲየም ሶላተል እስቲስቃዕ ስለሚሰገድ በከተማውና በዙሪያው የሚገኘው ሙስሊም ማህበረሰብ በሙሉ በሰዓቱ ተገኝቶ ይሰግድ ዘንድ የከተማ አስተዳደሩ እስልምና ምክር ቤት (መጅሊስ) በአላህ ስም ጥሪዉን ያቀርባል።

መልዕክቱን የሰማ፣ ላልሰማው ማህበረሰብ በማሰማት የድርሻውን እንዲወጣ መጅሊሱ ያሳስባል።

የዓለም ገበያ ከተማ አስተዳደር እስልምና ምክር ቤት (መጅሊስ)! ሰኔ 21/2017

07/06/2025
ኢሰመጉ የተሟሏ ዘገባ ባለማውጣቱና ዝርዝር ጉዳቱን ባለመግለጹ ህዝበ ሙስሊሙን ይቅርታ ጠየቀኢሰመጉ በሙስሊሙ ማህበረሰብ የደረሰበትን ወቀሳ ተንተርሶ በዛሬው እለት መግለጫ አወጥቷል። ኢሰመጉ በ...
26/09/2023

ኢሰመጉ የተሟሏ ዘገባ ባለማውጣቱና ዝርዝር ጉዳቱን ባለመግለጹ ህዝበ ሙስሊሙን ይቅርታ ጠየቀ

ኢሰመጉ በሙስሊሙ ማህበረሰብ የደረሰበትን ወቀሳ ተንተርሶ በዛሬው እለት መግለጫ አወጥቷል። ኢሰመጉ በስልጤ ዞን ቅበት የተከሰተውን ተግባር አስመልክቶ ባወጣው ሚዛኑን የሳተ ዘገባ ምክንያት በርካታ ትችቶችን ያስተናገደ ሲሆን ይህንን በማስመልከት ተቋሙ በዛሬው እለት መግለጫ አውጥቷል።..
ኢሰመጉ በመግለጫው "ነጻና ገለልተኛ" መሆኑን የገለጸ ሲሆን ለየትኛውም ሀይማኖት እንደማይወግንም ገልጿል። በስልጤ ዞን ቅበት የነበረውን ሁኔታም የአንድ እምነት ተወካይ ብቻ ማቅረቡን በመግለጽ "ሌሎቹን ማግኘት ስላልቻለ" እንደሆነ በመግለጫው አስቀምጧል። ስለዚህም መግለጫውን የሁሉም ወገን ማካተት ሳይቻል መውጣቱን ገልጿል።..
በዚህም የደረሰውን ጉዳት በዝርዝር ሳያካትት ባወጣው መግለጫ ለተፈጠረው አለመግባባትም ይቅርታ ጠይቋል። የኢሰመጉን መግለጫ አስመልክቶ ሚዲያችን የህግ ባለሙያ በመጋበዝ ገለልተኝነቱን አስመልክቶ ሰፊ ዘገባ መስራቱ ይታወሳል።..
© ሀሩን ሚዲያ

23/09/2023
የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የደንብ ልብስ ለብሶ sniper ታጥቆ የህዝብ ጠባቂ ፖሊሶችን የሚያስፈራራ   አካል ካለ ሀገራችንን አሁን ስልጣን ላይ ያለው መንግስት ነው እየመራት ያለው ወይስ ሌ...
20/09/2023

የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የደንብ ልብስ ለብሶ sniper ታጥቆ የህዝብ ጠባቂ ፖሊሶችን የሚያስፈራራ አካል ካለ ሀገራችንን አሁን ስልጣን ላይ ያለው መንግስት ነው እየመራት ያለው ወይስ ሌላ ህዝብ የማያውቀው ኃይል ነው እየመራት ያለዉ????? መመለስ ያለበት ጥያቄ ነው።
……… ግን ማነው ምላሽ መስጠት የሚችለው????
የህዝቡን ደህንነት ማስጠበቅ ይቅርና ለራሱ የህግ አካላት ዋስትናና የህግ ከለላ መስጠት እየቻለ ያልሆነው የስልጤ ዞን አስተዳደር ወይስ …… ማን=…?¿????¿¿ ግራ የሆነ ዘመን

17/09/2023
15/09/2023

በስልጤ ዞን ቅበት ከተማ ከተከሰተው ግጭት ጋር ተያይዞ በተለያዩ አካላት እየተሰጡ ያሉ መግለጫዎች ሀላፊነት የጎደላቸው ናቸው ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይክ ሙሐመድ ኸሊል ተናገሩ!..
ሀሩን ሚዲያ፦መስከረም 02/2016 ..
ከሰሞኑ በስልጤ ዞን ቅበት ከተማ አስተዳደር በግለሰቦች መካከል የተከሰተውንና በሂደት ተስፋፍቶ ቁሳዊና ሰብዓዊ ጉዳት ያስከተለውን ግጭት አስመልክቶ አንዳንድ የክርስትና እምነት ተቋማትና ግለሰቦች እየሰጧቸው ያሉ መግለጫዎች ሀላፊነት የጎደላቸውና ችግሩን ለመፍታት እየተሰሩ ባሉ እንቅስቃሴዎች ላይ ጫና የሚፈጥሩ መሆናቸውን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሸይክ ሙሐመድ ኸሊል ተናግረዋል።..
ችግሩ የተከሰተው በሴት ልጆች ላይ ድግምት ተሰርቷል በሚለው ምክንያት ቁርዓን በሞንታርቦ በመከፈቱና በሂደት ቁርዓን የተከፈተባቸው ስፒከሮችና ሞንታርቦዎች ይነሱ አይነሱ በሚል በጸጥታ ሀይሎችና በተወሰኑ ግለሰቦች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት መሆኑን ያነሱት ሸይክ ሙሐመድ ኸሊል የማህበረሰቡን አብሮነት ለማናጋት ያሰቡ ውስን አካላት ይህን ግጭት ወደ ሌላ አቅጣጫ በመውሰድ በከተማዋ ላይ ቁሳዊና ሰብዓዊ ኪሳራ እንዲደርስ አድርገዋል ብለዋል።..
ችግሩ ከተፈጠረበት እለት ጀምሮ እንደ ሙስሊም ተቋም መሪና እንደ አከባቢው ተወላጅ የሀገር ሽማግሌ ከጸጥታ አካላትና ከመንግስት መዋቅሩ ጋር በመሆን ግጭቱን ለማስቆም ሰፊ ስራ እየሰሩ ከተማውን በማረጋጋት ውስጥ መቆየታቸውን ያነሱት ሸይክ መሐመድ ከዚህ በተቃራኒ በአንዳንድ የክርስትና አባቶችና ተቋማት በኩል ግጭቱን አስመልክቶ ከእውነት የራቀ፣ የአከባቢውን ተጨባጭ ያላገናዘበ፣ በፍረጃ የተሞላና፣ ሀላፊነት የጎደለው ሁከት ቀስቃሽ መግለጫ መውጣቱን አንስተዋል። ..
አለመግባባቱ የተፈጠረው በቅበት ከተማ ውስጥ በተወሰኑ የማህበረሰብ አካላት መካከል ከመሆኑም በላይ የግጭቱ ዋነኛ ተጎጂ የእስልምና እምነት ተከታይ የማህበረሰብ ክፍሎችና የሙስሊሙ ተቋም ሆኖ ሳለ ችግሩን በክርስትና እምነት ላይ የተከፈተ ዘመቻ አድርጎ ማቅረብ የእስልምና እምነት ተከታዮችንና የስልጤን ማህበረሰብ በሙሉ የማይገለጽ በመሆኑ ሌላ ግብ ያለው የሚመስል ጭፍን ውንጀላ መሆኑን ሸይክ መሐመድ ገልጸዋል። ..
ተከስቶ በነበረው ችግር የአመራር ቤቶችን ጨምሮ የእስልምናና የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖች መኖሪያ ቤቶች ለይ ጉዳት መድረሱን ፕሬዚደንቱ ያነሱ ሲሆን በሌላ በኩል የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑ ከአምስት በላይ ወጣቶች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል በህክምና ክትትል ላይ መሆናቸውንና አንድ ሙስሊም ወጣት ለሞት መዳረጉን አብራርተዋል። ..
ችግሩ ሲከሰት በየተኛውም የክርስትና እምነት ተከታይ ቤተ እምነት ላይ ጉዳት አለመድረሱንና በአንጻሩ በከተማው መሃል በሚገኘው የሙስሊም መስጂድ ላይ ጉዳት መድረሱን ፕሬዚደንቱ ገልጸዋል።..
ይሁንና የተፈጠረው ችግር የእስልምና እምነት ተከታዮችንና የህዝቡን የዘመናት የአብሮነት ታሪክ ለማጥፋትና የአከባቢውን ስም ለማጠልሸት ያለሙ የጥቂት ግለሰቦች ተግባር መሆኑን በመገንዘብ ህብረተሰቡን አረጋግቶ ወደ ሰላም የማምጣት ስራ ላይ ትኩረት መደረጉን ፕሬዚደንቱ ጨምረው ገልጸዋል።..
የከተማዋን ሰላም ለመመለስና ህዝቡን በማረጋጋት በኩል የአከባቢው ህብረተሰብ በከፍተኛ ሁኔታ ትብብር እያደረገ እንደነበር ፕሬዚደንቱ አንስተው በሌሎች የእምነት ተቋማት በኩል ለመፍትሄው ከመተባበር ይልቅ ግጭቱን ሀይማኖታዊ ቅርጽ ለማስያዝና ከእምነት ተቋም የማይጠበቅ ሀላፊነት የጎደለው ተግባር ተፈጽሟል ሲሉ ሸይክ መሐመድ ሂደቱን ኮንነዋል። ..
በስልጤ ማህበረሰብ ውስጥ የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖች በተለያዩ በማህበራዊና በመንግስታዊ መዋቅሮች ላይ ማህበረሰብን እያገለገሉ ከመቆየታቸው ባሻገር ከስልጤ ህዝብ ጋር ተዋልደውና ተጋምደው ለዘመናት የመኖራቸውን ታሪክ ወደ ጎን በመተው ህዝቡን በገፊነት መፈረጅ በምንም መልኩ ተቀባይነት የሌለው ለሰላምና እርቅም እንቅፋት የሚሆን መሰረተ ቢስ ውንጀላ ነው ሲሉም ፕሬዚደንቱ አንስተዋል።..
ለሀገርም ይሁን ለቅበትና አከባቢው ማህበረሰብ ሰላምና ደህንነት የሚያስብ አካል እስከ ቦታው ዘልቆ እውነትን በመረዳት ለአብሮነት መስራት አለበት ያሉት ሸይክ መሐመድ መንግስት በበኩሉ በየተኛውም እምነት ውስጥ የተሸሸጉ አጥፊዎችን ለይቶ ለህግ በማቅረብ ህግ የማስከበር ሚናውን እንዲወጣ ጠይቀዋል። ..
ግጭቱን አስመልክተው አንዳንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክሪስቲያን አባቶችና የስልጤ፣ ሀዲያና ከምባታ ሀገረ ስብከት እንዲሁም የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት አባት ያስተላለፏቸው መልዕክቶችና የሰጧቸው መግለጫዎች የአከባቢውን የእስልምና እምነት ተከታዮችንና ማህበረሰቡን ፈጽሞ የማይገልጹና ዘመናትን ከስልጤ ማህበረሰብ አብሮ ለኖረው የክርስትና እምነት ተከታይ ወገናችን ምንም የማይፈይድና እርስ በርስ ጥርጣሬ የሚፈጥር ተገቢነት የሌለው ውንጀላ መሆኑ ታውቆ በአስቸኳይ እንዲታረምም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዚደንቱ ሸይክ ሙሐመድ ኸሊል አንስተዋል።

¤መረጃው የስልጤ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ነው።..
©ሀሩን ሚዲያ

28/07/2023

ንስር አሞራ መሬት ላይ ቆሞ ከእባብ ጋር አይጣላም እንደሚሸነፍ ያውቃል… ቦታው የእባብ መጫወቻ ሜዳ ነውና።

ንስር አሞራው እባቡን አንጠልጥሎ ወደ ሜዳው ወደ ሰማይ (ህዋ) ይወስደዋል፤ እባብ ያኔ አቅሙን ያጣል፣ ሚዛኑን መጠበቅ ያቅተዋል፣ በቅጡም አይቆምም። ለንስር አሞራው ደግሞ ህዋው comfort zonu (የራሱ መጫወቻ ሜዳው) ነውና እባቡን እንደፈለገ ያደርገዋል።

#… … እራስህን መሆን በማትችልበት ቦታ ከተቀመጥክ በየቀኑ ትሸነፋለህ።

መጀመሪያ የተደላደለ የምትወደው የሚመችህ ቦታ ላይ ቁም ከዚያ በኋላ በምትችለው አቅምህ ታገል ታሸንፋለህ።

ስኬት ከፍላጎት ይመነጫል ፍላጎት ደሞ ከምቾት የተወዳጀ ነው፣ አንዱ ከአንዱ ከተነጠለ ስኬት ወደኋላ ያዘግማል።

ያለህበትን ቦታ ለመቀየር አትፍራ ዓለም ለአንተ የሚሆን የተትረፈረፈ ቦታ አላትና።

Address

Siltie Zone, Worabe
Awassa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Zeynu aba xubale/ አባ ዡባሌ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Zeynu aba xubale/ አባ ዡባሌ:

Share