
29/07/2025
በሀዋሳ ሐምሌ 24 የሚካሄደው የአንድ ጀንበር አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃግብር በቂ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቋል።
በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሐምሌ 24 የአንድ ጀንበር አረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን የከተማ ደጋፊ አመራርና የከተማ አስተባባሪዎች ምልከታ አድርገዋል።
7ተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ሐምሌ 24 እንደ ሀገር 700 ሚሊየን እንደ ክልል ስምንት ሚሊየን ችግኝ ተከላ ይካሄዳል።
በሀዋሳ ከተማ በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ በአንድ ጀንበር ችግኝ ለመትከል መዘጋጀቱ ተገልጿል።
በመርሀግብሩ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች የከተማችን ወጣቶች በችግኝ ተከላ የሚሳተፉበት እንደሆነና ተከላዉ ልክ ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ ቀኑን ሙሉ የሚደረግ እንደሆነ ተገልጿል።
ለተከላዉ የሚሆን ጉድጓድና የችግኝ ማጓጓዝ ዝግጅት የተጠናቀቀ ሲሆን ህብረተሰቡም በችግኝ ተከላ በነቂስ እንዲሳተፍ ጥሪም ቀርቧል።