Hule Addis Media

  • Home
  • Hule Addis Media

Hule Addis Media ትክክለኛዉ የሁሌ አዲስ ሚዲያ ገፆች

Telegram: bit.ly/3NBQbro
YouTube : bit.ly/3p7kj3N
Twitter : bit.ly/3NVMRrB

ሰሞንኛ አነጋጋሪው | የልጅን ስም በሚስቱ አስጠራ | አርቲስቱ ትችት ገጠመው | ለማመን የሚከብድ እዉነተኛ ታሪክ ...
10/03/2025

ሰሞንኛ አነጋጋሪው | የልጅን ስም በሚስቱ አስጠራ | አርቲስቱ ትችት ገጠመው | ለማመን የሚከብድ እዉነተኛ ታሪክ ...

10/03/2025

ሰሌክታ ግሩፕ በፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት ከኢትዮጵያ ወጣ l የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር የመልቲሞዳል ትራንስፖርት ፈቃድ አገኘ l የአዲስ አበባ ባለሀብቶች ያላመኑበትን ግብርና ታክስ...

Title : የዋጋ ንሩቱ ተግዳሮት የሆነበት ፕሮጀክት  | የቤቶች ጉዳይ በዘላቂነት ይፈታ ይሁን ?
27/01/2025

Title : የዋጋ ንሩቱ ተግዳሮት የሆነበት ፕሮጀክት | የቤቶች ጉዳይ በዘላቂነት ይፈታ ይሁን ?

የቤቶችን የገንዘብ ችግር ለመቅረፍ የቤቶች ፋይናንስ ሥርዓት እንደ ሀገር ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑ ተነገረ ይልን ስርአት ለማቋቋም ጥናት መደረጉ እና የህግ ማዕቀፍ መዘጋጀቱ ተገልጿል ።=...

15/12/2024

ሩሃማ መርዝ ጠጥታ ሆስፒታል ገባች !!

ኩላሊቱን የሰጣት ሀብታሙ በስተመጨረሻ

ሚስት ባሏን ደሀ ነህ ብላ በፈታች በማግስቱ ባል  የሚሊዮን ዶላሮች ሎተሪ አሸነፈሰውዬው ለተወሰነ ጊዜ ሥራ አጥ ነበር እና ሚስቱ በሂደቱ ላይ እምነት መጣል ትዕግስት ስለሌላት ወደ ፊት ለመቀ...
15/12/2024

ሚስት ባሏን ደሀ ነህ ብላ በፈታች በማግስቱ ባል የሚሊዮን ዶላሮች ሎተሪ አሸነፈ

ሰውዬው ለተወሰነ ጊዜ ሥራ አጥ ነበር እና ሚስቱ በሂደቱ ላይ እምነት መጣል ትዕግስት ስለሌላት ወደ ፊት ለመቀጠል ወሰነች። ሆኖም የፍቺ ሰነዶችን ከፈረመ ከአንድ ቀን በኋላ ህይወቱን ሙሉ በሙሉ የሚለዉጠውን ሎተሪ አሸንፏል።

የአንካራውን ስምምነት መግለጫ ካነበብኩ በኋላ፣ በጉዳዩ ላይ ቀጥተኛ ሚና ከነበራቸው አካላት ተጨማሪ መረጃ በማሰባሰብ የሚከተልውን መረዳት ችያለሁ። - በጋራ መግለጫው ላይ  ባይገለጽም ኢትዮጲ...
13/12/2024

የአንካራውን ስምምነት መግለጫ ካነበብኩ በኋላ፣ በጉዳዩ ላይ ቀጥተኛ ሚና ከነበራቸው አካላት ተጨማሪ መረጃ በማሰባሰብ የሚከተልውን መረዳት ችያለሁ።

- በጋራ መግለጫው ላይ ባይገለጽም ኢትዮጲያ ከሶማሊላንድ ጋር የተፈራረመችውን ስምምነት ሽራለች።ሶማሊያ ደግሞ የኢትዮጲያ ጦር ከሀገሯ እንዲወጣ ስታራምደው የነበረውን አቋም ቀይራለች።

- ከሶማሊላንድ ጋር ተደርጎ የነበረው ስምምነት ኢትዮጵያ ሶማሌላንድን እንደ ነጻ ሀገር እውቆና ለመስጠት፤ በምትኩም ለወደብ እና የባህር ኃይል የሚሆን የባህር በር ማግኘት እንደነበር የሚታወስ ነው። የአንካራው ስምምነት ደግሞ ኢትዮጲያ የሶማሊያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ለማክበር፣ ሶማሊያ ደግሞ ወደቦቿን ኢትዮጲያ እንድትጠቀም እንድትፈቅድ የሚል ነው።

- ይህ ማለት የአንካራው ስምምነት ኢትዮጲያን የባህር ወደብ ባለቤትነት ሳይሆን የመጠቀም መብትን የሚወስን ነው። ማለትም የኢትዮጲያ መንግስት በሶማሊላንዱ ስምምነት ተጎነጻፍኩት ሲለው የነበረው የወደብ ባለቤትነት ቀርቶ፣ የሶማሊያንም ሆነ የሌላ ሀገራትን ወደብ በሊዝ፣ በኮንትራት ወዘት የሁለትዮሽ ስምምነት መጠቀም ትችላለች በሚለዉ ተተክቷል። ይህ ደግሞ እንደ United Nations Convention on the Law of the Sea (UNCLOS) ያሉ የአለም አቀፍ ህጎች ላይ የተመሰረተ ይሆናል። ሶማሊያም ሆነች ሌሎች ጎረቤቶቻችን ድሮውንም የተቀበሉት ጉዳይ ነው።ለምሳሌ ጂቡቲ የታጁራን በሊዝ ለኢትዮጲያ ለመስጠት እንደምትፈልግ ደጋግማ ተናግራለች።

ሲጠቃለል የአንካራው ስምምነት የኢትዮጲያ እና ሶማሊያን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲሁም ኢትዮጲያ የወደብ ባለቤት ለመሆን የምታደርገውን ሙከራ ከአምና (የሶማሊልንዱ ስምምነት ከተፈረመበት ከጃኑዋሪ 1፣ 2024) በፊት ወደነበረበት የሚመልስ ነው። ለዚሁ ነበር ያን ሁሉ ዲፕሎማሲያዊ ዋጋ የተከፈለው?

ሀገር የምትመራው በእውቀት ላይ በተመሰረተ የሰከነ እቅድ ይልቅ በባብዶ ምኞት ሲሆን ውጤቱ ሀገራዊ ተዓማኒነት (credibility) በእጅጉ መጉዳት ነው። በዚህ ጉዳይ ከተፈጸሙ ስህተቶች እና የደርሰውን ሀገራዊ ኪሳራ ለማመን እና ለመማር ዝግጁ የሆነ ዓዕምሮ ካለን፣ ወደፊት እንዳንደግመው ይረዳን ይሆናል። Jawar Mohammed

ኤርትራዊያን ስደተኞች በኢትዮጵያ አላግባብ ክፍያ እየተጠየቁና ዲፖርት እየተደረጉ ነው በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሃሰተኛ ነው - አገልግሎቱኤርትራዊያን ስደተኞች በኢትዮጵያ ያለ አግባብ ክፍያና ዲ...
13/12/2024

ኤርትራዊያን ስደተኞች በኢትዮጵያ አላግባብ ክፍያ እየተጠየቁና ዲፖርት እየተደረጉ ነው በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሃሰተኛ ነው - አገልግሎቱ

ኤርትራዊያን ስደተኞች በኢትዮጵያ ያለ አግባብ ክፍያና ዲፖርቴሸን እንደሚፈጸምባቸው ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ መሆኑን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አስታውቋል፡፡

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በኢትዮጵያ የህግ ጥሰት የፈፀሙ የውጭ ዜጎችን በተመለከተ በዛሬው ዕለት ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

አገልግሎቱ በማብራሪያው ኤርትራዊያን ዜጎች በኢትዮጵያ የተለየ በደልና አድልዎ እየፈጸመባቸው ነው በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን ገልጿል፡፡

በሌላ በኩል በርካታ ኤርትራዊያን በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገር በመግባትና በህጋዊ መንገድ ገብተው ከተፈቀደላቸው የጊዜ ገደብ በላይ በመቆየት በህገ-ወጥ መንገድ እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ በማብራሪያው ተነስቷል፡፡

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በጉዳዩ ላይ የሰጠው ማብራሪያ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

በኢትዮጵያ የህግ ጥሰት የፈፀሙ የውጭ ዜጎችን በተመለከተ የተሰጠ ማብራሪያ

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ደህንነቱንና ጠራቱን የጠበቀ ዘመናዊ፣ ተደራሽ የውጭ ዜጎች አገልግሎት በመዘርጋት የሀገራችን የውጭ ኢንቨስትመንትና የቱሪዝም ፍስት በመጨመር የተጀመሩትን የልማትና የለውጥ ጉዞ በማፋጠን የሀገራችን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ እየተደረገ ባለው ሀገራዊ እንቅስቃሴ የበኩሉን ሚና ለመወጣት የሚያስችለውን የሪፎርምና ቀጣይነት ያለው ተቋማዊ ግንባታ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ ያሏት ተፈጥራዊና ታሪካዊ የቱሪዝም እምቅ ሀብቶች እና ኢንቨስትመንት ተጠቃሚ ለማድረግና የቱሪዝም መዳረሻ ማዕከል ለማድረግ በሀገር ደረጃ በሚደረግ ጥረት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የቱሪስት ቪዛ፣ ኮንፈረን ቪዛ ከዚህ በፊት ከነበረው የቪዛ ክፍያ ተመን ከ23 በመቶ በላይ እንዲቀንስ መደረጉን ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የክፍያ አገልግሎት ደንብ ቁጥር 550/2016 መገንዘብ ይቻላል።

መንግስት ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለው መልካም ጉርብትናና ህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ካለው ቁርጠኛ አቋም በድንበር አካባቢ ከሚደረጉ ነጻ የሰዎች እንቅስቃሴ መፍቀድ በተጨማሪ መግቢያ ቪዛ ሳይጠየቁ በቀን ማህተም (ያለ ቪዛ ከፍያ) ገብተው ለ90 ቀናት እንዲቆዩ መፍቀዱ ይታወቃል።

በተለይ ከኤርትራ (አስመራ ወደ አዲስ ኣበባ ኢትዮጵያ) የሚመጡ ኤርትራዊያን ለ9ዐ ቀናት ያለ ቪዛ ክፍያ በቀን ማህተም ገብተው እንዲቆዩ ማድረጉ በሁለቱም ህዝቦች ያለው ግንኙነትና ወንድማማችነት ለማጠናከር ምን ያህል ቁርጠኛ አቋም እንዳለው ለመገንዘብ ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኤርትራዊያን ስደተኞች በጥገኝነት እንደሚኖሩ ይታወቃል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አንዳንድ ሚዲያዎች በተሳሳተ፣ ሚዛኑን ባልጠበቀ እና ኃላፊነት በጎደለው አግባብ ተቋማችን ኤርትራዊ ዜግነት ያላቸውን ሰዎች የተለየ በደል እና አድልዎ እየፈጸመባቸው እንደሆነ፣ ለመውጪያ ቪዛ የተጋነነ ክፍያ እንደሚጠየቁ፣ በስደተኝነት የተመዘገቡ ኤርትራዊያን ዲፖርት እየተደረጉ እንደሆነ አድርገው ሲዘግቡ ተስተውሏል።

በርካታ የውጭ ሀገር ሰዎች በህገወጥ መንገድ ድንበር ጥሰው ወደ ኢትዮጵያ በመግባትና ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ ሀገር ውስጥ ሲቆዩ የሚስተዋሉ ሲሆን፣ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የውጭ ሀገር ሰዎች የስራ ፈቃድና መኖሪያ ፈቃድ ሳይኖራቸው ባልተፈቀደላቸው የሥራ መስክ ከመሰማራት ጀምሮ በህገወጥ የማዕድን ዝውውር፣ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ በአደገኛ እፅ ዝውውር፣ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ በኮንትሮባንድ፣ በሀሰተኛ ሰንዶች ዝግጅት ወዘተ የመሳሰሉ የሀገራችን ብሔራዊ ጥቅምና ደህንነት የሚጎዱ ተግባራት ላይ በመሰማራት ከባድ እና የተደራጁ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ሲፈፅሙ መገኘታቸውን ማርጋገጥ ችለናል።

በተለይ በርካታ ኤርትራዊያን በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገር በመግባትና በህጋዊ መንገድ ገብተው ከተፈቀደላቸው የጊዜ ገደብ በላይ በመቆየት በህገ-ወጥ መንገድ እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ይታወቃል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እነዚህን አካላት ወደ ህጋዊ መንገድ ለማስገባትና ለመመዝገብ በተደጋጋሚ ጥሪ ማድርጉ የሚታወቅ ቢሆንም ተመዝግበው ወደ ህጋዊ ስርዓቱ የገቡ ግን በጣም ጥቂት ናቸው።

ስለሆነም የሀገርን ብሄራዊ ደህንነትና ጥቅም በሚጎዳ መልኩ ህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙ የውጭ ሀገር ዜጎች በተመለከተ የሚከተሉትን ነጥቦች ማጉላት አስፈላጊ ነው።

ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድና የስራ ፈቃድ ሳይኖራቸው ሐሰተኛ ወይም የተጭበረበረ ማንነት በመያዝ ለውጭ ሀገር ዜጎች ባልተፈቀዱ የስራ መስኮች በመሰማራት በህገወጥ መንገድ ከትንሸ ሱቅ ችርቻሮ እስከ ያልተፈቀዱ ትላልቅ ስራዎች ተሰማርተው ተገኝተዋል።

በርካታ የኤርትራዊ ዜግነት ያላቸው ዘመድ ለመጠየቅ በማስመስል ከዱባይ፣ ከኤርትራ፣ ከኡጋንዳ በመመላለስ የተለያዩ ሸቀጣ ሸቀጦች በሻንጣ በማስገባትና በማስወጣት የኮንትሮባንድ እና ሌሎች ህገወጥ ተግባራት ሲያከናውኑ ተገኝቷል።

በተለያዩ ሀገራት ከሚገኙ ሌሎች ህገ-ወጥ ደላሎች ጋር በመተሳሰር በርካታ ፍልሰተኞችን በህገ-ወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩና በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሲያከናውኑ ተገኝቷል።

ለተለያዩ ሕገወጥ ተግባራት የሚያገለገሉ ሐሰተኛና የተጭበረበሩ የጉዞና የይለፍ ሰነዶች፣ ማህተሞች፣ የባንክ ቡኮች በማዘጋጀትና በመጠቀም ህገ-ወጥ ተግባራት ሲፈጽሙ ተገኝተዋል።

የተለያዩ ሐሰተኛ ሰነድና ማንነት በመጠቀም ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ሲያከናውኑ እና ከህግ ውጭ ሰነዶችን ሲጠቀሙ መገኘታቸው።

ስለዚህ ማንኛውም የውጭ ሀገር ዜጋ የሀገራችንን ህግ ተላልፎ ከተገኘ በህግ ተጠያቂ እንደሚሆን ይታወቃል።

በመሆኑም ህጉ ተፈጻሚ የሚሆነው በሁሉም የሚመለከታቸው የውጭ ሀገር ሰዎች እንጂ በአንድ ሀገር ዜጋ ብቻ ተፈጻሚ የሚደርግ አሰራር ተደርጎ በአንድ አንድ ሚድያዎች መዘገቡ ስህተት ነው። ስለሆነም ለኤርትራዊያን ዜጎች እንደማንኛውም የጎረቤት ሀገር ዜጎች በቀን ማህተም ገብቶ በተፈቀደለት የጊዜ ገደብ (90) ቀናት ቆይቶ ለሚሔድ ሰው ምንም ዓይነት የቪዛ ክፍያ እንደማይጠየቅ ለመግለጽ እንወዳለን።

ከተፈቀደለት የጊዜ ገደብ ቆይተው የሚጣልባቸው ቅጣት ቢሆንም የኤርትራ ዜግነት ያላቸው ሰዎችን ጨምሮ ለጎረቤት ሀገራት እንዲከፍሉት የሚጠየቀው ክፍያ በእጅጉ (በ200 በመቶ) የቀነሰ ሆኖ እያለ ለኤርትራዊያን የተለየና የተጋነነ ክፍያ እንደሚጠየቁ ተደርጎ መዘገቡ ከእውነታ የራቀ ነው።

በተመሳሳይ መልኩ ኤርትራውያን ስደተኞችን በተመለከተም ኢትዮጵያ ስደተኞችን ተቀብላ ጥላ ከለላ መሆን የቆየ ታሪኳና ባህሏ እንደሆነና የኤርትራ ዜግነት ያላቸው ስደተኞችን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት ዜጎች በጥገኝነት እንድሚገኙ ይታወቃል።

በመሆኑም በስደተኝነት የተመዘገበ ማንኛውም የኤርትራዊ ዜግነት ያለው ሰው ያለ ፈቃዱ ከሀገር እንዲወጣ እና ተገቢነት የሌለው ክፍያ እንዲከፍል የተረገ ሰው የሌለ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

እውነታው ይህን ሆኖ እያለ በኤርትራዊያን ስደተኞች ላይ ያለ አግባብ ክፍያና ዲፖርቴሸን እንደሚፈጸምባቸው ተደርጎ መዘገቡ ከእውነት የራቀ ነው።

የሀገራችንን ብሔራዊ ደህንነትና ጥቅም በመጠበቅ ህጋዊ የውጭ ሀገር ሰዎች እንቅስቃሴን ለማረጋገጥ ለሚሰራው ስራ ላይ ሁሉም የሚመለከታቸው ባለድርሻና ተባባሪ አካላት ከጎናችን እንዲቆሙ ጥሪያችን እያቀረብን በተለይ ሚደያዎች ሚዛናዊ በመሆን የሀገራችንን ብሔራዊ ደህንነትና ጥቅም በጠበቀ መልኩ አወንታዊ ሚና እንዲወጡ እናሳስባለን።

(ኤፍ ኤም ሲ)

የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የመሠረቱት ፋውንዴሽን ይፋ ሊደረግ ነው   | የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የመሠረቱት "የአዳም ፋውንዴሽን" የተ...
12/12/2024

የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የመሠረቱት ፋውንዴሽን ይፋ ሊደረግ ነው

| የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የመሠረቱት "የአዳም ፋውንዴሽን" የተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት በሚቀጥለው ሳምንት ሰኞ ምሥረታውን ይፋ የሚያደርግበት ሥነ ሥርዓት ሊያከናውን ነው።

አቶ ደመቀ መኮንን በቦርድ ሊቀመንበርነት የሚመሩት "የአዳም ፋውንዴሽን"፤ "በአፍሪካ መቀንጨርን ለመዋጋት" እንደሚሠራ ተገልጿል።

ለ11 ዓመታት ከቆዩበት የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሥልጣን ባለፈው ዓመት ጥር 2016 ዓ.ም. በፈቃዳቸው የተሰናበቱ አቶ ደመቀ ያቋቋሙት ፋውንዴሽኑ ይፋዊ የማብሰሪያ ሥነ ሥርዓቱ የሚከናወነው ሰኞ ታኅሣሥ 7/2017 ዓ.ም. ነው።

"በአፍሪካ መቀንጨርን መግታት" የሚል መሪ ቃል ያለው ፋውንዴሽኑ፤ ከኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያገኘው ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ እንደሆነ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ውሂብእግዜር ፈረደ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የፋውንዴሽኑ መሥራች አቶ ደመቀ መኮንን የድርጅቱ የቦርድ ሊቀመንበር እንደሆኑ ዶ/ር ውሂብእግዜር ገልጸዋል።

በሥነ ምግብ ላይ በመሥራት የሚታወቁት የቀድሞዋ የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ ወ/ሮ ፍሬዓለም ሺባባው ደግሞ ምክትል የቦርድ ሊቀመንበር እንደሆኑ አስረድተዋል። የቀድሞ የትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ጥላዬ ጌጤም የፋውንዴሽኑ የቦርድ አባል ናቸው።

የአዳም ፋውንዴሽን በሥነ ምግብ ላይ እንደሚሠራ የገለጹት ዋና ሥራ አስኪያጁ፤ መቀንጨርን ለመግታት የሚያስችሉ "ባለብዙ ዘርፍ" ፕሮግራሞችን በመቅረፅ ተቋሙ እንደሚሠራ አመልክትዋል።

“…ምርጫውን እንወዳደራለን- ቢቀርም ቁጭት የለም!”  “መንግስታችን የቀረው ግዜ አንድ አመት ተኩል እድሜ ነው”**********ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ይህን ያሉት - በአዋሳ ከተማ የኮሪደር ...
10/12/2024

“…ምርጫውን እንወዳደራለን- ቢቀርም ቁጭት የለም!”

“መንግስታችን የቀረው ግዜ አንድ አመት ተኩል እድሜ ነው”
**********
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ይህን ያሉት - በአዋሳ ከተማ የኮሪደር ልማት ምረቃ ስነ ስርአት ላይ በተገኙበት ወቅት ነው፡፡

በዚህ ንግግራቸው የሚመሩት መንግስት የቀረው ኮንትራንት ጊዜ አንድ አመት ተኩል ነው ብለዋል፡፡

ከአመት ከመንፈቅ በኋላ በኢትዮጵያ ሌላ ሀገራዊ ምርጫ እንደሚደረግ ያወሱት አብይ - በዚያ ምርጫ አዲስ ኮንትራን ይፈፀማል በማለት - “በዚህ ምርጫ የሚወሰነውን ውጤት ከኢትዮጵያ ህዝብ ውጭ ማንም አያውቅም” ብለዋል፡፡

“እኛ ያለን ጊዜ የአንድ አመት ተኩል ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ - “የመንግስት ባለስልጣናት እንዳያንቀላፉ እና በቀራቸው ጊዜ ተቀለጣጥፈው የከተማ እና ገጠር ልማቶችን እንዲያፋጥኑ” ጠይቀዋል፡፡ “በዚህ በቀረው ጊዜ ውስጥ ነዋሪዎች በከተሞቻቸው ለመኖር የሚኖቸውን ፍላጎት የሚጨምሩ እና ምቾትን የሚያመጡ ጉዳዮች መስፋት አለባቸው” ብለዋል፡፡

አብይ ማሳሰቢያቸው ሲቀጥል “በገጠር ኮሪደር ደግሞ አልፎ አልፎ እንደታየው አትክልት እና ፍራፍሬ፣ እርሻ እና የሌማት ትሩፋትን ማስፋት ያስፈልጋል” - ያን አድርገን በሚቀጥለው ምርጫ ስንወዳደር - በሰራ መንፈስ እንወዳደራለን - ቢቀርም (በምርጫው መወዳደሩ) ቁጭትም የለም ብለዋል፡፡

አክለውም በጊዜያችን እስከሰራን ድረስ ቁጭት የለም በማለት - “በየደረጃው ያሉ የስራ ሀላፊዎች - ያልተገደበ የስልጣን ጊዜ እንደሌላችሁ አስቡ” ሲሉ ያስጠነቀቁ ሲሆን - “ያላችሁ ጊዜ ውስን ነው - ያንን ዘመን በሚገባ ተጠቀሙበት” ብለዋል፡፡

“ደሞዝ ከጠበቃችሁ ህይወታችሁ አይለወጥም..!” ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድጠቅላይ ሚንስትር አብይ በአርባ ምንጭ ከተማ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር ብዙ ሰው አይረዳም ያሉትን ቁልፍ ጉዳይ በማ...
10/12/2024

“ደሞዝ ከጠበቃችሁ ህይወታችሁ አይለወጥም..!” ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ በአርባ ምንጭ ከተማ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር ብዙ ሰው አይረዳም ያሉትን ቁልፍ ጉዳይ በማንሳት ሞግተዋል፡፡ እርሱም መንግስታቸው ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ በሕዝቡ ኑሮ ላይ ምን ለወጠ የሚለውን ነው፡፡

እንደ ጠቅላይ ሚንስትሩ ገለፃ መንግስት ለያንዳንዱ ዜጋ ደሞዝ በመክፈል የዚህችን አገር ችግር አይፈታም፡፡ “በተለያየ ሀገራት መሪዎች በሁለት መልኩ የህዝቡን ኑሮ ለውጠዋል” ሲሉ ያጣቀሱት አብይ “በአንድ በኩል ህዝባቸው ከምቾት ቀጠና እንዲወጣ - ያለበት ህይወት እንዳይመቸው እና ተጨማሪ ስራዎችን አንዲሰራ አቅማቸውን አሟጠው በመጠቀም ተለውጠዋል” ሲሉ ጠቅሰዋል፡፡

ከዚህ ባለፈ ደግሞ - “ሌሎች ሀገራት መጠነ ሰፊ የተፈጥሮ ሀብት አግኝተው - በነዳጅ እና ሌሎች ማእድናት ሀገር እና ህዝብን ያበለፀጉ አሉ ሲሉ” ጠቅሰዋል፡፡ “እናም ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለቱን መንገዶችን መጠቀም አለብን” ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ - “በአንድ በኩል ከፍተኛ የተፈጥሮ ሀብት አለን እርሱን አውጥተን መጠቀም አለብን - በሌላ በኩል ደግሞ ሰፊ ህዝብ አለን - ብዙ የወጣት ክምችት አለን - ይሄንን ሰው በመነቅነቅ - ከተመቸው ከባቢ አስወጥቶ በማነቃነቅ ሀገር መገንባት አለብን” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

“በዚህ መንገድ ለትውልድ የተሻለ ሀገር እናስረክባለን” ያሉት አብይ - “ካልሆነ ግን ሰዎች ከመንግስት ደሞዝ የሚጠብቁ ከሆነ መቼም አይለወጡም” ባይ ናቸው፡፡ “ከመንግስት አስቻይ የሚሆን ፖሊሲ እና ስትራቴጂ በመቅረፅ በየትኛው ሴክተር ብንሰማራ ልንለወጥ እንችላለን የሚለውን በማሳየት ነው ሚናውን የሚጫወተው” ብለዋል፡፡

አንዳንዶች “ብልፅግና መቼ ነው እኛጋ የሚደርሰው ብለው ይጠይቃሉ” ሲሉ የሚናገሩት ጠቅላይ ሚነስትሩ - “የብልፅግና ትሩፋት የሚደርሳችሁ ስራ እንፈጥራለን - ስራውን ስትሰሩት ነው፡፡ ሰዎች ናችሁ ጭንቅላት አላችሁ፣ ካላችሁበት (comfort zone) ነቅንቀን ለማስወጣት እንሞክራለን፡፡ ሀሳብ በመፍጠር ህይወታችሁን ስትቀይሩ ነው” በማለት መልሰዋል።

ፕሬዝዳንተ ሀሰን ሸክ በአንካራ ለሚካሄደው የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ሶስተኛ ዙር ንግግር ለመገኘት ቱርክ መግባታቸው ተገለጸበኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ ለመፍታት በሚል  ...
10/12/2024

ፕሬዝዳንተ ሀሰን ሸክ በአንካራ ለሚካሄደው የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ሶስተኛ ዙር ንግግር ለመገኘት ቱርክ መግባታቸው ተገለጸ

በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ ለመፍታት በሚል #በቱርክ ለሚካሄደው ሶስተኛ ዙር ንግግር ለመገኘት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሸክ ማህሙድ ወደ አንካራ ማቅናታቸውን የሶማሊያ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ፕሬዝዳንት ሀሰን ሸክ ወደ ቱርክ ያቀኑት ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ለምታካሂደው ሶስተኛ ዙር ድርድር ለመታደም በቱርኩ ፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶጋን በተደረገላቸው ግብዣ ነው ሲል የሀገሪቱ የዜና አገልግሎት በኤክስ ገጹ ባጋራው መረጃ ጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ጠ/ሚንስትር አብይ አህመድ በስብሰባው ላይ የሚገኙ ከሆነ ባሳለፍነው አመት ኢትዮጵያ ከሶማሊላንደ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ከተፈራረመች ወዲህ እና በሁለቱ ሀገራት መካከል ከፍተኛ እሰጥ አገባ ከተስተናገደ በኋላ ሁለቱ መሪዎች ለመጀመሪያ ግዜ የሚገናኙ ይሆናል።

“በቱርክ አደራዳሪነት በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል የሚካሄደው ሶስተኛው ዙር ውይይት ይቀጥላል" ሲል የሶማሊያ ብሄራዊ የዜና አገልግሎት (SONNA) በኤክስ ገጹ ባጋራው መረጃ አመላክቷል።

ባሳለፍነው አመት 2016 ዓ.ም መጨረሻ ነሃሴ ወር ላይ በሁለቱ ሃገራት መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ ለመፍታት ያለመ ሁለተኛ ዙር ንግግር በቱርክዬ አንካራ የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ማካሄዳቸው ይታወሳል።

የሁለቱም ሀገራት ተወካዮች ፊት ለፊት ሳይገናኙ በቱርክዬ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን አስተባባሪነት ውይይታቸውን ማካሄዳቸው በወቅቱ ተዘግቧል።

ሁለተኛው ዙር ጉልህ የሆነ ለውጥ ሳያመጣ ከተጠናቀቀ በኋላ ሦስተኛ ዙር ንግግር ለማድረግ ለመስከረም 7/2017 ዓ.ም. ቀጠሮ መያዙ ተገልጾ እንደነበር ይታወሳል።

የሁለተኛው ዙር ውይይት አለመሳካቱን ተከትሎ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በቱርክ አንካራ ያደረጓቸው ንግግሮች ሳይሳኩ የቀሩት ኢትዮጵያ የሶማሊያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ባለማክበሯ ነው ማለታቸውም በወቅቱ ተዘፍቧል።

ፕሬዝዳንቱ ቅዳሜ ነሐሴ 11/2016 ዓ.ም. በብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ በተላለፈው ንግግራቸው፤ ኢትዮጵያ የሶማሊያን ሉዓላዊነት እስክትቀበል ድረስ በምንም ጉዳይ ላይ አንነጋገርም” ማለታቸውም በዘገባው ተካቷል።

በመላው ሀገሪቱ ኃይል መቋረጡ ተገለፀበኢትዮጵያ በሚገኙ በሁሉም አከባቢዎች ኃይል መቋረጡን ካፒታል የደረሰው መረጃ ያመለክታል ። ይህን ተከትሎ ጉዳዩ የሚመለከተው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግ...
07/12/2024

በመላው ሀገሪቱ ኃይል መቋረጡ ተገለፀ

በኢትዮጵያ በሚገኙ በሁሉም አከባቢዎች ኃይል መቋረጡን ካፒታል የደረሰው መረጃ ያመለክታል ።

ይህን ተከትሎ ጉዳዩ የሚመለከተው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በመላዉ ሀገሪቱ ኃይል መቋረጡን በመግለፅ በድጋሚ ለመመለስ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁሟል።

ተቋሙ እንዳለው በሲስተም አለመረጋጋት በተፈጠረ ችግር የተነሳ በመላው ሀገሪቱ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል ብሏል።

ችግሩን በመፍታት የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ በኃይል ማመንጫዎች እና በማከፋፈያ ጣቢያዎች ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አስታውቋል ።

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hule Addis Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Hule Addis Media:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share