30/08/2025
ኃይሌ ሆቴል ሻሸመኔ ዳግም አገልግሎት መስጠት ጀመረ !
| ኃይሌ ሆቴል ሻሸመኔ ታድሶና ሚሰጣቸውን አገልግሎቶች አሳድጎ ፤አስፍቶና ፤አዘምኖ በድጋሚ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ፡፡
የ ኃይሌ እና ዓለም ኢንተርናሽናል ኃ/የተ/የግ/ማህበር አካል የሆነው ኃይሌ ሆቴሎች እና ሪዞርቶች ግሩፕ ባለ ሶስት ኮኮብ ሆቴል በሻሸመኔ ከተማ ዳግም ግንባታውንና የማስፋፊያ ስራውን አጠናቆ ነሀሴ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
ኃይሌ ሆቴል ሻሽመኔ ማስፋፊያውን ሁለት አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቀ ሲሆን
✓ ከ 40 ወደ 84 የእንግዳ ማረፊያ ክፍሎች
✓ የተለያዩ ባሮችና ዘመናዊ ሬስቶራንቶች
✓ የመዋኛ ገንዳ
✓ የስፖ (የሳውና እና ስቲም)
✓ ጂምናዚየም
✓ ለተለያዩ ዝግጅቶችና ስብሰባ የሚሆኑ 3 አዳራሾች
✓ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የበይነ መረብ(ኢንተርኔት) አገልግሎቶች ላይ ማሻሻያ ጨምሮ ስራ ጀመረ።
ሆቴሉ ለ 210 የአካባቢው ነዋሪዎች የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን በቀጣይ አገልግሎቱን እያሰፋ 300 ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ
የስራ እድልን ይፈጥራል።
የኃይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ግሩኘ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ጋዲሳ ግርማ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው ለግንባታውም ከ600 ሚሊዬን ብር በላይ እንደወጣና የኃይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች መገለጫ የሆነውን በይቻላል መንፈስ የተገነባ የስራ ባህልንና የአገልግሎት ልህቀትን ደንበኞቻቸው በሻሸመኔም እንደሚያገኙ ተናግረዋል።
በይቻላል መርህ የተገነባ አገልግሎት በሁሉም ቦታ!
ኃይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ግሩኘ
#ሻሸመኔ