04/02/2026
ነብይ፤ ሐዋርያ ነኝ የምትሉ ይበቃል መርካቶ ግቡ!!
ዘማሪ በረከት ተስፋዬ
"ነብይ ነኝ፤ ሐዋርያ ነኝ የምትሉ ይበቃል መርካቶ ግቡ። ወንጌል ለንግድ አይሆንም ለንግድ የሚሆን ጌታ የለም! ንግድ ሌላ ነገር ነዉ።
እንደዚህ ዓይነት ሰዎች ነብይ ነኝ፤ ሐዋርያ ነኝ የምትሉ በስነ ሥርዓት በቃ እስካሁን ጥሩ ሳንቲም ሰርታችኋል እርግፍ አድርጋችሁ ተዉትና መርካቶ ግቡ።
ስሩ ስራ መስራት ጥሩ ነዉ። ነገር ግን የዛሬ 2 ሺህ ዓመት የሞተ፤ ስለፍቅር የሞተ፤ ደሙን ያፈሰሠ ይኼ ንጉሥ ኢየሱስ በሚባል ንጉስ አይነገድም!! ኢየሱስ አይሸጥም!! ለንግድ የሚሆን ጌታ አይደለም። የለም።