
29/05/2025
አምሀራ
አም=ነፃ
ሀራ=ህዝብ
አምሀራ =ነፃ ህዝብ
ቅኔ የሆነ ታላቅ ህዝብ !!!
አማራ እኔም(individualistic)
እኛም(collectivist) ስነልቦና ያለው ማኅበረሰብ ነው፡፡ ይህ ሲባል የእኛ ስነልቦና በአብዛኛው የተላበስ ቢሆንም ሁል ጊዜ መጨፍለቅና በደቦ መወሰን አይስማማውም፡፡
እኔነትና እኛነት አይጣሉበትም፡፡ ይህም የሆነው ራስን ከማወቅና (self-awareness) ራሰን ከመግዛት (self-regulation) የመጣ ነው፡፡ ፈረንጆቹ self-actualization የሚሉት አይነት ትዎሪ አይደለም፡፡ ምናልባት ራስን ማወቅና (self-awareness) ራሰን ከመግዛት (self-regulation) ከዚያም በላይ ነው፡፡ በስልቦና ራስን ከማወቅ የበለጠ ምንም ትልቅ ነገር የለም፡፡ አማራ የእኔ (individualistic) ስነልቦና የተላበሰ መሆኑ ብዙ ጀግኖች ጎልተው እንዲወጡ ረድቶታል፡፡ አደንና ጦርናት ላይ በግለሰብ ደረጃ ጀብድ መስራት የተለመደ ነው፡፡ አጤ ቴዎድሮስ ውስጥ እኔ (individualistic) ስነልቦና መኖሩ አሸናፊ እንዲሆኑ ረድቶአቸዋል፡፡ ከሽፍትነት እስከ ታላቅ መሪነት 💪፡፡ አማራ የጠነከረ የእኛ (collectivist) ስነልቦና የተላበሰ በመሆኑ ደግሞ survive ከማድረግም አልፎ ሰፊ አገር ገንብቶ እንዲኖር ረድቶታል፡፡ አማራ collectivist ስለሆነ the Amhara concept of family is very broad, encompassing parents, children, grandparents, aunts, uncles, and cousins. እንዲያውም በአማርኛ cousins የሚባል ቃል የለም፤የእህት ልጅ፣ የወንድም ልጅ፤ ነው የሚባለው፡፡ እየሰፋ ሲሄድ አንድ የወሎ አማራ ሌላውን የወሎ አማራ የወንዜ ልጅ ወንድሜ ነው የሚለው፡፡ ጎንደር፤ ጎጃም፤ ሸዋም እንዲሁ ነው፡፡ ለምሳሌ የጎንደር አማራ ሌላውን የጎንደር አማራ ለሌላ ሰው ሲያስተዋውቀው የእኛ አገር ሰው ከማለት ይልቅ ወንድሜ ነው ይላል፡፡
…..
አማራ የኅልውና ጥያቄዎቹን (existential questions) የመለሰ ማኅበረሰብ በመሆኑ ጤነኛ ስነልቦና የተላበሰ ነው፡፡ ይህ ማለት ከየት መጣሁ፤ ዘሬ፣ ርስቴ (አገሬ) ወዴት ነው? ማን ፈጠረኝ? ምንድን ነኝ? የሚሉት ሁሉ በልቡ የተፃፉለት በመሆኑ አንድም ቀን አወዛግበውት አያውቁም፡፡ አማራ ፈጣሪውን ያወቀው በትምህርት አይደለም፤ በልቦናው እንጂ፡፡ የልቦና ጸንሰ ሐሳብ ፈረንጅ ውስጥ የለም፡፡ mind ልቦናን አይወክልም፡፡ ልቦና ረቂቅ ነው፡፡ አስተሳሰብን ደመነፍስን ኅሊናን ፍርድን ሁሉ ይመለከታል፡፡ አማራ ለኅሊናዊ የማይበጅ ወይንም ኅሊናው ያልፈቀደውን ነገር አድርግ ሲባል ‹‹ብሞት ይሻለኛል›› ይላል፡፡ ይህ በexistential ስነልቦና የጤንነት ምልክት ነው፡፡ ለኑሮውም ለሞቱም ምክንያት ያለው ሰው እጅግ ጤነኛ ነው፡፡
…..
አማራ ኃይሉ መንፈሳዊነቱ ላይ ነው (external agency) ፡፡ አጤ ቴዎድሮስ እኔ የክርስቶስ ባሪያ ይል ነበር፡፡ አማራ ለስኬቱ ክሬዲቱን በአብዛኛው ለፈጣሪው ነው የሚሰጠው፡፡ ለአማራ መንፈሳዊነቱንና ዓለማዊነቱን መለየት ከባድ ነው፡፡ ዓለማዊና መንፈሳዊ የሚባል ስብዕና የለም፡፡ አማራ መንፈሳዊም ዓለማዊም ነው፤አይጣሉበትም፡፡ መንፈሳዊነቱ ለኑሮው ለአመራር ጠቅሞታል እንጂ፡፡
…….
አማራ ወንድነት የባህሪው ነው፡፡ ወንድነት ፆታ የለውም፡፡ በእርግጥ በአብዛኛው ለወንዶች ጋር ያለ ስነልቦና ነው፡፡ ወንድነት brave, courage, warrior ማለት ነው፡፡ የአማራ ልጅ ከተወለደ ጀምሮ ወንድነትን እንዲላበስ socialize ይደረጋል፡፡ እናም እግዚአብሔር ሰውን ነፃ ይሆን ዘንድ ፈርዶበታል፤አማራ ደግሞ ልጁን ወንድ (brave, courage, warrior) ይሆን ዘንድ ይፈርድበታል፡፡
….
አማራ ሥልጡንነትና ዘመናይነት ስነልቦና የተላበሰ ነው፡፡ በትንሹ አንድም ቤቱ ውስጥ ያሉት እቃዎች አሰራር አጊያጊያጥ የልብሱ ጥልፍ(ዲዛይን) ማየት ይቻላል በትልቁ ደግሞ ይሉኝታውና በአንተና በእኔ መካከል ያለውን ድንበር የመለየት ችሎታው ትልቅ ያደርገዋል፡፡ አማራ ሥልጡንነት ስነልቦና የተላበሰ ነው ማለት ሥርዓት ያለውና በኑሮው ሁሉ ሥርዓትን የሰራ ማኅበረሰብ ነው ፡፡ አመጋገብ አለባበስ አረማመድ አነጋገር ልጅ አስተዳደግ ሕዝብ አስተዳደር ሁሉም ሥርዓት አለው፡፡ አንድን ማኅበረሰብ ሥልጡን ነው ዘመናዊ ነው ለማለት ትልቁና ዋናው መስፈርት ሥርዓት ነው፡፡ አደለም እንዴ? ነው፡፡ ሕንፃ መንገድ ቴክኖሎጂ ሕክምና እዚያ በኋላ ነው፡፡ ደግሞም አማራ እነዚህም አሉት፤አንዳንድ ደብተራዎቹና መሻሂዎች ዘመናዊ ሐኪምን ያስንቃሉ፡፡ ብዙ ማኅበረሰቦች እንደቀላል የሚያዩት የአማራን ይሉኝታ ነው፡፡ ይሉኝታ በስነልቦና- ይሉኝታ is the development of community –mindedness. አስምሩበት፡፡ ይሉኝታ የሰውነት የውኃ ልክ ነው ፡፡ (yilougnta is the absolute essential to the concept of personhood. It is the internalization of social rules and values that determine personhood.)
….
አማራ ማኅበረሰብ ውስጥ መማርና አለመማር በብሰለት ደረጃ ልዩነቱ አጨቃጫቂ ነው፡፤ ገበሬውም ሊቅነት አለው፡፡ ዋናው ሊቅነት የቃል ነው፡፡ አማራ ንግግሩ በጣም ሰምና ወርቅ ነው፡፡ ኃዘኑንም ደስታውንም በአሽሙር በቅኔ ይናገራል፡፡ አማራ ሌላው ኃይሉ የንግግር ችሎታው ላይ ነው፡፡ የአውሮፓ የintelligence theory ለአማራ አይሰራም፡፡ ለምሳሌ የሼህ ሁሴን ጅብሪልና አለቃ ገብረሃናን ሊቅነት ትዎራው አቃፊ አይደለም :: ሼህ ሁሴን ጅብሪል መፍረድ የጀመሩት ገና በሰባት ዓመታቸው እንደነበርና የሚናገሩትም መሬት ጠብ የማይል እንደነበር ይነገርላቸዋል። ወደር የማይገኝላቸው ትንቢት ተናጋሪ ነበሩ፡፡ በአውሮፓ አስተምሮ ግን ትንቢት መናገር የሊቅነት የአዋቂነት ማሳያ አይደለም፤እንዳውም የአዕምሮ መታወክ ነው፡፡
…..
አማራ ውስጥ ኃቀኝነት ትኅትናም አለ፡፡ እውነቱን ተናግሮ ከመሸበት ማደር ወይንም የተናገርኩት ከሚጠፋ የወለድሁት ይጥፍ እንዲል፡፡ አማራ ጥጋብን ይፈራል፡፡ ጥጋብ ሲባል በድንቁርና በማን አለብኝነት የሚመጣውን ነው፡፡
….
በአማራ ድኃና ኃብታም አንድም የተለያዩም ናቸው፡፡ አንድነታቸው ሁለቱም ኩሩነታቸው ነው፡፡ ኃብታምና ባለሥልጣን እንዲሁም ቄስና ሼህ በማኅበረሰቡ ውስጥ ትልቅ ቦታ አላቸው፡፡ በአብዛኛው አዎንታዊ የሄኑ የስነልቦና መገለጫዎች ይነገርላቸዋል፡፡ ድኃም ግን በማንነቱ ከኃብታም አያንስም፤በድኅነቱ የሚመጣበት አይወድም፤ከደረስህበት ‹‹እኔ ድኅነቴን ይዤ ለተቀመጥሁት ምን ሆነኝ ብለህ ነው አንተው›› ይልሃል፡፡ ኃብታም የድኃን ጉለበት ይበዘብዛል እንጂ ስነልቦናውን እንዲበዘብዘው ግን ብዙም አይፈቅድም፡፡
…………
አማራን ማጥናት እጅግ ከባድ ነው፡፡ አንደኛ ብዙ ነገሮቹ ሲምቦሊክ (symbolic) ናቸው፡፡ ለምሳሌ፡- በማተቤ የመጣ ሲል በኃይማኖቱ ይመስልህና ግን እርሱን ብቻ አደለም ፡፡ ላመነበት ሁሉ ሟች መሆኑን ለማሳዬት ነው፡፡ ለምሳሌ፡- እናት የብዙ ነገሮች symbol ነች፡፡ በተለይ የአገርና የኃይማኖት፡፡ እናት መሬት ናት፡፡ መሬት እህል አብቃይ ናት፡፡ በአማራ ስነልቦና እናትንና የልጅን የስነልቦና ትስስር በቋንቋ መግለፅ ከባድ ነው፡፡ አማራ ‹‹እናትማ እናት ናት›› ነው የሚልህ ወይንም ‹‹የእናት ሞትና የድንጋይ መቀመጫ እያደር ይቆረቁራል›› ይልሃል፤ እናትን ማጣት ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ለመግለጽ፡፡
…………
አማራ ባለ ብዙ ታሪክ ሕዝብ ነው፡፡ ታሪክ ደግሞ ትናንት ብቻ አይደለም ተስፋም ነው፡፡ በስነልቦና ሁላችንም የትውስታ (የታሪክ) ውጤቶች ነን፡፡ ስንሞትም አንዳች የሚረባ ነገር ጥለን የምናልፈው ትውስታን ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ አንድ ማኅበረሰብ ታሪካም ከሆነ እውቀትን ከትናንት ከታሪኩ ይቀዳል፤ነገን ተስፋ ያደርጋል፡፡ ይህ አፍሪካውነትም ነው፤ሳንኮፋ( Sankofa) ይባላል፡፡ Sankofa is a Ghanaian symbol for remembering, to learn from the past. ስለሳንኮፋ ሌላ ጊዜ እመለስበታለው፡፡ ግን ብቸኛ መዳኛችንም ይመሰላኛል፡፡ Sankofa ነፃነትንም ያላብሳል፡፡ Sankofa = return to the past and fetch-ለሁሉም ለስነልቦናም ለፖለቲካም ይበጃል፡፡
………
በአማራ ስነልቦና ሰው አንዴ ተሰርቶ የሚያልቅ አይደለም፤እንዲያው ሙሉ ሰው የማይባልም ሰው አለ፡፡ ሰው ሙሉ ይሆን ዘንድ ስም ያስፈልገዋል፡፡ ይገረዛል፤ኃይማኖት ይኖረዋል፤ከዚያ ያገባል.፤…እያለ ሂደቱ ይቀጥላል፡፡ self-actualization በአማራ ስነልቦና እንደአብርሀም ማስሎው ትርክት አይደለም፡፡ አማራ ክብሩን ከኅልውናው፤ከአገሩ ሊያስቀድም ይችላል፡፡
መች ጀመርኩና እቀጥላለሁ።