Ethio news daily

Ethio news daily Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethio news daily, Digital creator, gondar, Abay.

26/04/2023
ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን የኢትዮጵያ መንግስት በቱርክ ላደረገው የሰብዓዊ እርዳታ ምስጋና አቀረቡ የቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን በቱርክ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የኢትዮጵያ መ...
26/04/2023

ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን የኢትዮጵያ መንግስት በቱርክ ላደረገው የሰብዓዊ እርዳታ ምስጋና አቀረቡ
የቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን በቱርክ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የኢትዮጵያ መንግስት ላደረገው ሰብዓዊ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ለተደረገው ሰብዓዊ ድጋፍ በቱርክ ለኢትዮጵያ አምባሳደር አደም መሃመድ እና የኢትዮጵያ የነፍስ አድን ልዑክን ለመሩት ሌተናል ጀኔራል ደስታ አብቼ የፕሬዚዳንታዊ ሜዳሊያ ሽልማት እና የምስክር ወረቀት አበርክተዋል፡፡

ባለፈው የካቲት ወር በቱርክ ከ59 ሺህ በላይ ዜጎችን ለህልፈት የዳረገ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ተከስቶ የነበረ ሲሆን÷ የኢትዮጵያ የነፍስ አድን ልዑክም በቱርክ የሰብዓዊ እርዳታ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔዎችን አሳለፈየሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 20ኛ መደበኛ ስብሰባው ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ ምክር ቤቱ በመካከለኛ ዘመን /2016-2020/ የማክሮ...
26/04/2023

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔዎችን አሳለፈ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 20ኛ መደበኛ ስብሰባው ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

ምክር ቤቱ በመካከለኛ ዘመን /2016-2020/ የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊሲካል ማዕቀፍ ላይ ነው ተወያይቶ ውሳኔ ያሳለፈው፡፡ማዕቀፉ በዋናነት የመንግስት በጀት ከማክሮ ኢኮኖሚ ዓላማዎችና ታሳቢዎች ጋር ተጣጥሞ እንደተዘጋጀ የሚያመላክት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም የመካከለኛ ዘመን የመንግስት ገቢና ወጪ እንዲሁም የፊሲካል ሚዛን የፖሊሲ አቅጣጫዎችን ለመለየትና ለማመላከት የሚያገለግል የበጀት ዕቅድ መሳሪያ ሆኖ የ2016 የፌዴራል መንግስት ዝርዝር በጀት የሚዘጋጅበትን ጥቅል የገቢ ትንበያ፣ የወጪ ጣሪያ፣ የክልላዊ መንግስታት የበጀት ድጋፍ ጣሪያና የፊሲካል ጉድለት መጠንን የሚያመላክት ሆኖ መዘጋጀቱን ምክር ቤቱ አረጋግጧል፡፡

ማዕቀፉ ባለፉት ዓመታት በሀገሪቱ በተከሰቱ ችግሮች ምክንያት የተጋረጠውን የፊሲካል ስጋት ለመቅረፍና የፊሲካል ጤናማነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል የፋይናንስ አጠቃቀም ስልት ተግባራዊ እንዲደረግ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ስለሆነም ማዕቀፉ የመንግስት ገቢና ወጪ እንዲመጣጠን ማድረግን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት ምክር ቤቱ በማዕቀፉ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ መወሰኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡

በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሱዳን በተፈጠረው ውጊያ ቢያንስ ስምንት ኢትዮጵያዊያን እንደተገደሉና ሌሎች አራት ኢትዮጵያዊያን የመቁሰል ጉዳት እንደደረሰባቸው መናገሩን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።ኢት...
26/04/2023

በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሱዳን በተፈጠረው ውጊያ ቢያንስ ስምንት ኢትዮጵያዊያን እንደተገደሉና ሌሎች አራት ኢትዮጵያዊያን የመቁሰል ጉዳት እንደደረሰባቸው መናገሩን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።

ኢትዮጵያዊያኑ ለሞት እና ለመቁሰል አደጋ የተዳረጉት፣ በተባራሪ ጥይት እና ከባድ መሳሪያ አረሮች ፍንጣሪ ሳቢያ መኾኑን ኢምባሲው መግለፁን ዘገባው አመልክቷል።

ከአገሪቱ መውጣት የሚፈልጉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ኢትዮጵያዊያን ዜጎች በአውቶብስ ወደ መተማ ለመሸኘት እየመዘገበ መሆኑን ኤምባሲው መግለፁን የጠቀሰው ዘገባው፣ የኤምባሲው ሠራተኞች ካርቱምን ለቀው ለኢትዮጵያ ቅርብ በሆነችው የሰሜን ሱዳኗ ገዳሪፍ ከተማ ሥራቸውን እያከናወኑ መሆኑን ጠቅሷል።

በቦረና ዞን በሐጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን የተሰራው የውኃ ፕሮጀክት ተመረቀ። ፕሮጀክቱ በቦረና ዞን ሚዮ ወረዳ ቡኮ ሉቦማ ቀበሌ እና ዱቡሉቅ ወረዳ ተሰርቶ እንደተመረቀ  ከፋውንዴሽኑ ያገኘው መረ...
31/03/2023

በቦረና ዞን በሐጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን የተሰራው የውኃ ፕሮጀክት ተመረቀ። ፕሮጀክቱ በቦረና ዞን ሚዮ ወረዳ ቡኮ ሉቦማ ቀበሌ እና ዱቡሉቅ ወረዳ ተሰርቶ እንደተመረቀ ከፋውንዴሽኑ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
Ethio news daily

በአለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ የሰፈረችው ውሻ እድሜ 30 አመት 266 ቀን ነው።  በሊሪያ ፣ ፖርቹጋል ውስጥ በኮንኬይሮስ ገጠራማ መንደር ውስጥ ህይወቱን በሙሉ ከኮስታ ቤተሰብ ጋር ኖሯል |...
03/02/2023

በአለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ የሰፈረችው ውሻ እድሜ 30 አመት 266 ቀን ነው። በሊሪያ ፣ ፖርቹጋል ውስጥ በኮንኬይሮስ ገጠራማ መንደር ውስጥ ህይወቱን በሙሉ ከኮስታ ቤተሰብ ጋር ኖሯል | ስፓይክ የዓለማችን አንጋፋ ውሻ መሆኑን ከገለጸ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ጊነስ ወርልድ ሪከርድስ ስለ አንድ ትልቅ ውሻ ማስረጃ አግኝቷል። በጣም የቆየ ውሻ። እንደ እውነቱ ከሆነ ቦቢ (በ. ግንቦት 11 ቀን 1992) የሚኖረው በጣም ጥንታዊ ውሻ ብቻ አይደለም; እሱ ከመቼውም ጊዜ ትልቁ ውሻ ነው!

Follow Ethio news daily
03/02/2023

Follow Ethio news daily

''በዘፈንና በወረቀት ጋጋት የሚፈርስ መንግስት የለም!....pm abiy Ahmed
07/07/2022

''በዘፈንና በወረቀት ጋጋት የሚፈርስ መንግስት የለም!....pm abiy Ahmed

የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ስልጣን ለመልቀቅ ወሰኑ የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ስልጣን ለመልቀቅ መወሰናቸውን መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ...
07/07/2022

የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ስልጣን ለመልቀቅ ወሰኑ

የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ስልጣን ለመልቀቅ መወሰናቸውን መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ሰልጣን ለመልቀቅ የወሰኑት ባለፉት ሁለት ቀናት ከ50 በላይ የመንግሥታቸው ሚኒስትሮች እና የስራ ሀላፊዎች ስልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከወግ አጥባቂው ፓርቲ መሪነታቸው ለመልቀቅ የተስማሙ ሲሆን፥ ቀጣዩ የፓርቲው መሪ እስከሚታወቅ ድረስ በጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው…

በ"ዝንጀሮ ፈንጣጣ" በሽታ የተያዘም ሆነ የተለየ ሰው አለመኖሩን እናሳውቃለን" - ጤና ሚንስቴር"የዝንጀሮ ፈንጣጣ" በሚባል የሚታወቀውና በተለያዩ ሃገራት የተከሰተው ተላላፊ በሽታ በሃገራች ተ...
03/07/2022

በ"ዝንጀሮ ፈንጣጣ" በሽታ የተያዘም ሆነ የተለየ ሰው አለመኖሩን እናሳውቃለን" - ጤና ሚንስቴር

"የዝንጀሮ ፈንጣጣ" በሚባል የሚታወቀውና በተለያዩ ሃገራት የተከሰተው ተላላፊ በሽታ በሃገራች ተከስቶ ሁለት ሰዎች ተለይተዋል(ኳረንቲን ገብተዋል) የሚል መረጃ በሪፖርተር ጋዜጣ ወጥቶ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ይገኛል።

በሽታው በሌሎች ሃገራቶች ቢከሰትም በሃገራችን እስከ አሁን በበሽታው የተያዘም ሆነ የተለየ ሰው አለመኖሩን እናሳውቃለን፣ ሃላፊነት የሚሰማቸው የሚዲያ ተቋማት ይህን መሰል ያልተረጋገጠና በሚመለከተው አካል ያልቀረበ መረጃን ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ እናሳስባለን። ወቅታዊ የጤና መረጃዎችን እንዲሁም የማህበረሰቡ የጤና ስጋት የሚሆኑ ወረርሽኞችን በተመለከተ ትክክለኛ መረጃ ከጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ማግኘት የሚቻል መሆኑን እናሳዉቃለን።
ምንጭ ፣ ጤና ሚንስቴር

03/07/2022

በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ የሚመራው የትግራይ መስተዳድር ከኢትዮጵያ ፌድራል መንግስት ጋር ለሚደረገው ድርድር ከሕዝብ ጋር በመመካከር ተወካዮቹን እንደሚመርጥ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ።

ከክልሉ መስተዳድር ከፍተኛ ባለሥልጣናት አንዱ የሆኑት አቶ ጌታቸው የተደራዳሪዎቹ ማንነት በህውሓት ብቻ እንደማይወሰን ለክልሉ መገናኛ ብዙኃን በሰጡት እና በዛሬው ዕለት በተላለፈ መግለጫቸው ተናግረዋል። ትግራይን የሚመራው የህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል ባለፈው ሰኔ 6 ቀን 2014 በጻፉት ግልጽ ደብዳቤ በናይሮቢ በኬንያው ፕሬዝደንት ኡኹሩ ኬንያታ አመቻቺነት ለሚደረግ ድርድር የክልሉ መንግሥት ተወካዮቹን ለመላክ ፈቃደኛ መሆኑን አስታውቀው ነበር።

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ለማብቃት የሚደረገው ድርድር በአፍሪካ ኅብረት በኩል ሊደረግ ይገባል የሚል አቋም ያለው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ብልጽግና ፓርቲ በበኩሉ ሰባት አባላት ያሉት የፌድራል መንግስት ተወካዮች ባለፈው ሣምንት መርጧል። የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥትን ወክሎ በድርድሩ የሚሳተፈው የልዑካን ቡድን በምክትል ጠቅላይ ምኒስትር ደመቀ መኮንን የሚመራ ነው።አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ቅዳሜ በተላለፈ መግለጫቸው "ድርድር በተፈጥሮው በሰጥቶ መቀበል መርኅ ላይ የተመሠረተ ስለሆነ ምንድነው የምንሰጠው? ምንድነው የምንቀበለው? ከምንሰጣቸው መሰረታዊ የማይዘለሉ የሚባሉ መሠረታዊ ነገሮች ውጪ ባሉ ጉዳዮች ላይ መወያየት ይቻላል። እሱን ለማድረግ በእኛ እምነት ህወሓት የሚባል ፓርቲ ብቻ የሚያደርገው አይደለም" ሲሉ ተናግረዋል። "ሕዝብን አሳትፈን፤ እነ ማንናቸው ወክለውኝ ሊደራደሩ የሚችሉ ብሎ ወስኖ የምናደርገው ነው የሚሆነው" ያሉት አቶ ጌታቸው "ጊዜ አንገብጋቢ ነው ብለን እናምናለን። ወደዚህ ጉዳይ በአስቸኳይ መግባት አለብን ብለን እናምናለን። ለእኛ ግን በዚህ ጉዳይ ላይ የተሟላ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ግልጽ ስዕል ተፈጥሮልናል ብለን አናምንም" ሲሉ የክልሉን መንግሥት አቋም አብራርተዋል።

ሁለቱ ወገኖች በአደራዳሪዎች ማንነት ላይ ያላቸው ልዩነት እንዴት መፍትሔ እንደሚያገኝ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም። የአፍሪካ ኅብረት፣ አሜሪካ እና የአውሮፓ ኅብረት ለአፍሪካ ቀንድ በሾሟቸው ልዩ መልዕክተኞች በኩል የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በድርድር እንዲቋጭ ግፊት ሲያደርጉ ቆይተዋል። በድርድሩ አሜሪካ፣ የአውሮፓ ኅብረት፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የአፍሪካ ኅብረት ሊሳተፉ እንደሚገባ ዶክተር ደብረጺዮን ገብረ ሚካኤል በጻፉት ግልጽ ደብዳቤ ጠቅሰዋል።

❗️በሱዳን ተቃውሞ ጠንክሯልየፀጥታ ኃይሎችም በተቃዋሚዎች ላይ አስለቃሽ ጭስ እና ወሃ በመርጨት ለመበተን የሞከሩ ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰልፈኞች ካርቱም ውስጥ ወደ ሚ...
03/07/2022

❗️በሱዳን ተቃውሞ ጠንክሯል

የፀጥታ ኃይሎችም በተቃዋሚዎች ላይ አስለቃሽ ጭስ እና ወሃ በመርጨት ለመበተን የሞከሩ ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰልፈኞች ካርቱም ውስጥ ወደ ሚገኘው የፕሬዝዳንቱ ቤተመንግሥት እንዳያመሩ ለማገድ ጥይት መተኮሳቸው ተዘግቧል። በዚህም ሳቢያ ቢያንስ ዘጠኝ ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች ደግሞ እዚያው ካርቱም ውስጥና በአቅራቢያ በምተገኘው ኦምዱርማን ከተማ ውስጥ በጥይት ቆስለው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።

በኢትዮጵያ ከሚገኙት 36 የነዳጅ ኩባንያዎች 26ቱ ወደ ኢትዮጵያ ሁሉም አከባቢዎች ስለመድረሳቸው ሪፖርት አለማድረጋቸውን የነዳጅና ኢነርጂ ማኒስቴር አስታወቀ።በቀጣይ ካላሳወቁ በኩባንያዎቹ ላይ...
03/07/2022

በኢትዮጵያ ከሚገኙት 36 የነዳጅ ኩባንያዎች 26ቱ ወደ ኢትዮጵያ ሁሉም አከባቢዎች ስለመድረሳቸው ሪፖርት አለማድረጋቸውን የነዳጅና ኢነርጂ ማኒስቴር አስታወቀ።

በቀጣይ ካላሳወቁ በኩባንያዎቹ ላይ እርምጃ ይወሰዳል ሲል ሚኒስትሩ አስታውቋል።

አዲስ አበባ ያለው የኦነግ ቢሮ በኦነግ ሸኔ ላይ እየተወሰደ ነው ያለው ወታደራዊ እርምጃ እንዲቆም ጠየቀየአማራ እና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንቶች በቅርቡ የኦሮሞ ነጻነት ጦር የተባለውን ታጣቂ ...
03/07/2022

አዲስ አበባ ያለው የኦነግ ቢሮ በኦነግ ሸኔ ላይ እየተወሰደ ነው ያለው ወታደራዊ እርምጃ እንዲቆም ጠየቀ

የአማራ እና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንቶች በቅርቡ የኦሮሞ ነጻነት ጦር የተባለውን ታጣቂ ቡድን “ለማጥፋት” ይወሰዳል ያሉት እርምጃ እንዲቆም የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጠየቀ። ኦነግ ባወጣው መግለጫ ግጭቱ በሰላም እንዲፈታ ጥሪ አቅርቧል።

የአማራ እና የኦሮሚያ ክልል መሪዎች የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ ሹማምንት በተገኙበት በባሕር ዳር ከተማ ባለፈው ሰኔ 21 ቀን 2014 በሰጡት መግለጫ በታጣቂ ቡድኑ ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀው ነበር። ባለሥልጣናቱ መግለጫውን የሰጡት ሰኔ 11 ቀን 2014 በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ አሰቃቂ ጥቃት ተፈጽሞ በርካታ ሰዎች ከተገደሉ በኋላ ነው።

የኦሮሞ ነጻነት ጦር በኦሮሚያ ክልል ደምቢዶሎ እና ጊምቢ ከተሞች እንዲሁም በጋምቤላ ጥቃቶች ፈጽሟል።በጥቃቶቹ በበርካታ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች፣ የጸጥታ አስከባሪዎች እና የአማጺ ቡድኑ አባላት ተገድለዋል። ባለሥልጣናቱ ከሰጡት መግለጫ በኋላ ኦነግ እንደሚለው በኃይል የታጠቁ ወታደሮች የጫነ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቅፍለት ከአማራ ክልል በኩል በተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ኦሮሚያ ክልል ገብቷል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ባወጣው መግለጫ ግን ቀውሱ በኃይል ይፈታል ብሎ እንደማያምን አስጠንቅቋል። “ለሚፈጠረው ተጨማሪ የደም መፋሰስ ተጠያቂ በመሪዎቹ ትከሻ ላይ እንደሚወድቅ” የገለጸው ኦነግ ሌሎች ክልሎች እጃቸውን እንዳያስገቡ ጠይቋል።

ከትግራይ ልዩ ኃይል የመጡ የሽብር ቡድኑ  አባላት በቁጥጥር ሥር ዋሉ!!ከትግራይ ልዩ ኃይል የመጡ የሽብር ቡድኑ ሁለት አባላት አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቱሉ ድምቱ አካባቢ 11:00 ሰዓት ላይ በ...
03/07/2022

ከትግራይ ልዩ ኃይል የመጡ የሽብር ቡድኑ አባላት በቁጥጥር ሥር ዋሉ!!

ከትግራይ ልዩ ኃይል የመጡ የሽብር ቡድኑ ሁለት አባላት አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቱሉ ድምቱ አካባቢ 11:00 ሰዓት ላይ በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ተደርጓል።

በቁጥጥር ሥር የዋሉት
1ኛ. ዘመን ገ/እግዚአብሔር (የጥበቃ መምሪያ አባል የነበረ የፈንጂ ባለሞያ)
2 ኛ. ገ/ኪዳን ገ/ጻድቅ የልዩ ኃይሉ አባል ናቸው።የሽብር ቡድኑ አባላት ላይ ከፌደራል ፓሊስ ጋር በመሆን ምርመራ ተጀምሯል። ውጤቱን በቀጠይ እናሳዉቃለንም ብሏል።

ኢትዮጵያና ሱዳን የድንበር ውዝግባቸውን ከውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት ነፃ በሆነ መልኩ ሊፈቱ ይገባል – ደቡብ ሱዳናዊ ምሁርኢትዮጵያና ሱዳን የድንበር ውዝግባቸውን ከውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት ...
02/07/2022

ኢትዮጵያና ሱዳን የድንበር ውዝግባቸውን ከውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት ነፃ በሆነ መልኩ ሊፈቱ ይገባል – ደቡብ ሱዳናዊ ምሁር
ኢትዮጵያና ሱዳን የድንበር ውዝግባቸውን ከውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት ነፃ በሆነ መልኩ በውይይት ሊፈቱ እንደሚገባ የጁባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ረዳት ፕሮፌሰር ቴር ቶኚክ ማጆክ ገለጹ። ኢትዮጵያ የድንበር ውዝግቡን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ተደጋጋሚ ጥረት ብታደርግም÷ የሱዳን ወታደራዊ ኃይል ችግሩን ለማባባስና ዓለም አቀፋዊ ለማድረግ መሞከሩ ተገቢ አመሆኑን ነው ረዳት ፕሮፌሰር…

ለፖለቲካ ነጋዴዎች መጠቀሚያ ሳንሆን ራሳችንን ከጽንፈኝነት አርቀን የእህትማማችነትና ወንድማማችነት መርሐችንን ይበልጥ ወደ እያንዳንዱ ሰው እንዲደርስ በቁርጠኝነት እንሰራለን- የብልጽግና ፓርቲ...
02/07/2022

ለፖለቲካ ነጋዴዎች መጠቀሚያ ሳንሆን ራሳችንን ከጽንፈኝነት አርቀን የእህትማማችነትና ወንድማማችነት መርሐችንን ይበልጥ ወደ እያንዳንዱ ሰው እንዲደርስ በቁርጠኝነት እንሰራለን- የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ

Address

Gondar
Abay

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio news daily posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share