ኢትዮ ገጠር ቲዩብ Ethio geter tube

  • Home
  • ኢትዮ ገጠር ቲዩብ Ethio geter tube

ኢትዮ ገጠር ቲዩብ Ethio geter tube የገጠር ባህላችን እና ወጋችን ማስተዋወቅ
እንዲሁም የጠፉ ባ?

21/04/2021

1000 አሸናፊዎች የሚሸለሙበት የጥያቄና መልስ ውድድር ላይ ተሳታፊ ለመሆን ዛሬ ምሽት ይጠብቁን:: ጓደኞችዎ በውድድሩ ተሳታፊ እንዲሆኑ መልዕክቱን ያጋሩ

"በህይወት እስካለህ፦🚢ልትሳሳት🚢ልትወድቅ🚢ሰዎች ላይቀበሉህ🚢ሀሳብህን ላይረዱህ🚢ቦታ ላይሰጡህ🚢በእጅህ ላይ ያለው ሙሉ በሙሉ አመድ ሆኖ ልታገኘው🚢ሰዎች ሊጠሉህ🚢ሊያሙህ🚢ስም ሊያወጡልህ🚢ሊስቁብህ....
26/01/2021

"በህይወት እስካለህ፦
🚢ልትሳሳት
🚢ልትወድቅ
🚢ሰዎች ላይቀበሉህ
🚢ሀሳብህን ላይረዱህ
🚢ቦታ ላይሰጡህ
🚢በእጅህ ላይ ያለው ሙሉ በሙሉ አመድ ሆኖ ልታገኘው
🚢ሰዎች ሊጠሉህ
🚢ሊያሙህ
🚢ስም ሊያወጡልህ
🚢ሊስቁብህ... ይችላሉ።
-
"በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ለሁሉም ሰው ትክክለኛ ሆኖ ለመታየት
መሞከር ነው።
# መልካም ብትሆን ክፉዎች ይጠሉሀል።
# አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች ባዶነታቸውን ስለምትገልጥባቸው አብዝተው ይፀየፉሀል።
ብርሀናዊ # ራዕይ ቢኖርህ የጨለምተኞችን ጨለማ ስለምታሳይ መኖርህ ያንገበግባቸዋል።
# ነፃ_አውጭ ብትሆን ጨቋኞች ያሳድዱሀል።
-
ምናለፋህ በዓለም ስትኖር በሙሉ ድምፅ ልትወደድ _ አሊያም ልትጠላ
አትችልም። ስለዚህ በደረስክበት ሁሉ ልክ እንደ ውሀ ቅርፅህን አትቀያይር።
ከምንም በላይ በፈጣሪህ ፊት ትክክል ሁን"
ስብሓት ገብረእግዚአብሔር
ተዬ ቦጋለ እንደፃፈው✍🏾✍🏾✍🏾✍🏾

||የሕይወት መርሆዎች || ለደስተኛ ሕይወት ቁልፍ የሆኑ ነገሮች ።* * * *1. እራስህን ከሌላ ሰው ጋር አታፎካክር፦ ሁላችንም እንደ አሻራችን ሁሉ ባህሪያችን እና ፍላጎታችንም በጣም ይለያ...
26/01/2021

||የሕይወት መርሆዎች || ለደስተኛ ሕይወት ቁልፍ የሆኑ ነገሮች ።
* * * *
1. እራስህን ከሌላ ሰው ጋር አታፎካክር፦ ሁላችንም እንደ አሻራችን ሁሉ ባህሪያችን እና ፍላጎታችንም በጣም ይለያያል። ደስታን ከሚያጠፉ ምክንያቶች አንደኛው እራስን ከሰው ጋር ማፎካከር ነው። አሳ ደስታዋን እንደ ወፍ በሰማይ ልፈልግ ብትል፤ ወፍ ደግሞ እንደ አሳ በውሃ ውስጥ ልፈልግ ብትል፤ ሁለቱም ሳይደሰቱ ይቀራሉ።
ስለዚህ ደስታህን በራስህ መለኪያ ለካው። አንተ በሌሎች ስትቀና ሌሎችም ባንተ እንደሚቀኑ እወቅ።
2. አትኩሮትህን በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ አድርገው፦ የጎደለህ ምንድን ነው? ያለህስ ምንድን ነው ? ብታመዛዝነው የቱ ይበልጣል? ብዙዏቻችን ሃሳብ እና አትኩሮቶቻችን በሌለን ነገር ላይ ስለሆነ፤ ያለንን ነገር ሳንጠቀምበት እንቀራለን። ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም። በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው። ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና።
3. እራስህን ሁን፦ በዚህ ምድር ላይ ሌላውን ለመምሰል እንደመሞከር ከበድ ነገር ምን አለ? ሌላውን ለመምሰል
ስትሞክር፤ የምትጣላው ከሰው ጋር ሳይሆን ከገዛ እራስህ ጋር ነው። እናም እራስህን አታስቀይመው፤ እውነተኛ ወዳጆችህ አንተን ባንተነትህ ይቀበሉሃል…..ከምንም በላይ እራስህን በመሆን ከራስህ ጋር ሰላም ፍጠር፤
4. ሁሉን ለማስደሰት አትሞክር፦ አንድ ነገር ስታደርግ
ሰዎች ደስ እንዲላቸው ብለህ ሳይሆን ትክክለኛ እና አንተ ያመንክበት ነገር ስለሆነ ይሁን። በዚህ ምድር ላይ ምንም አይነት ጻዲቅ ሰው ብትሆን እንኳን ሁሉንም ሰዎች ማስደሰት አትችልም። ስለዚህ የምታደርጋቸው ነገሮች ከህሊናህ ጋር እስከተስማሙ ድረስ በቂ ነው። ለሰው ሳይሆን ለህሊናህ ኑር።
5. የውሸት ደስታን አትፈልግ፦ በውሸት ደስታና በእውነተኛ ደስታ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ።የውሸት ደስታ፤ ጊዜያዊ በሆኑና ከውጪ በምናገኛቸው ነገሮች የሚመጣ ነው። ሃዘናችንን ለጊዜው የሚጋርድ ጊዜያዊ ማስታገሻ፤ እውነተኛ ደስታ ግን ሃሳባችን፤ አላማችን፤ ምግባራችን ሲጣመር የሚፈጠር ስሜት ነው። ሃዝን እና መከራችንን ሳንደብቅ የምንጽናናበት ደስታ፤
6. ማንን እንደምታገኝ አታውቅምና ለሁሉም ሰው ቅን
ሁን፦ ከመንገደኛው አንስቶ እስከ ቅርብ ወዳቻችን ድረስ፤ ሰዎች በኛ ላይ ትልቅ አስተዋጽዎ አላቸው። በህይወትህ የምታሰፍራቸው ነጥቦች ሁሉ በኋላ ላይ ተያይዘው መስመር መስራታቸው አይቀርም። የተናቀው ድንጋይ የማዕዘን ራስ ይሆናል ተብሏልና ሰዎችን አትናቅ። በየትኛውም አጋጣሚ ለምታገኛቸው ሰዎች ትክክለኛውን ነገር አድርግ፤
7. መለወጥ የማትቻለውን ነገሮችን ተቀበላቸው፦ ብዙ
ሰዎች ጭንቀት ውስጥ የሚገቡት መለወጥ የማይችሏቸውን ነገሮች ለመለወጥ ስለሚጥሩ ነው። ምንም እንኳን በህይወታችን ውስጥ አብዛኛው ነገሮች ላይ ስልጣን ቢኖረንም፤ መለወጥ የማችላቸው ነገሮች አሉ። ከአቅምህ በላይ በሆኑ ነገሮች እራስህን አታስጨንቅ። ከአቅምህ በላይ የሆነውን ነገር ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ስጠው።
8. የራስህ እውነተኛ ወዳጅ ሁን፦ ምንም እንኳን ሰዎች በአንተ ቢያምኑብህም እና ቢመኩብህም ፤ አንተ በገዛ እራስህ ካላመንክ ህይወትህ ምንም ዋጋ የለውም። ከሰዎች ፍቅር በላይ የራስህ ፍቅር ወሳኝ ነው። የሚገርመው ሰዎች እራሱ ሊወዱህ የሚችሉት አንተ በመጀመሪያ እራስህን መውደድ ስትችል ነው።እራስህን በደንብ ተንከባከበው። ሲያጠፋ ይቅር በለው፤ ሲደክም አበርታው፤ ሲሳካለት አሞካሸው። ላንተ ካንተ የቀረበ ማን አለህና?
* * * *
ዶ/ር ምህረት ደበበ

23/12/2020

Photo picture camera geter love

long life for our dad!!!
23/12/2020

long life for our dad!!!

ማፍቀር ስትጀምር ከእምነትህ ጀምር ትዳር ስትጀምር በሙሉ ልብህ እመን ምክኒያቱም ትዳር የእግዚአብሔር ስጦታ ነውና ለስጋህ ምግብ እንደሚያስፈለገው ሁሉ ለነፍስህም ፀሎት ያስፈልጋታል ሌላው ሁሉ...
21/12/2020

ማፍቀር ስትጀምር ከእምነትህ ጀምር
ትዳር ስትጀምር በሙሉ ልብህ እመን ምክኒያቱም ትዳር
የእግዚአብሔር ስጦታ ነውና ለስጋህ ምግብ እንደሚያስፈለገው ሁሉ ለነፍስህም ፀሎት ያስፈልጋታል
ሌላው ሁሉ ለእግዚአብሔር ተው እርሱ ሁሉን አዋቂ ነውና።

እያንዳንዱ ቀን የፍቅር ቀን ይሁንልን ዋነው ፍቅር ነው

15/12/2020
ባህልባህሌ ያደኩበትንእኔ 'ወደዋለሁ የኔርኩበትን
13/12/2020

ባህል
ባህሌ ያደኩበትን
እኔ 'ወደዋለሁ የኔርኩበትን

13/12/2020

Address


Telephone

+251918530557

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኢትዮ ገጠር ቲዩብ Ethio geter tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ኢትዮ ገጠር ቲዩብ Ethio geter tube:

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share