Capital Market In Ethiopia

Capital Market In Ethiopia Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Capital Market In Ethiopia, Digital creator, Bahir Dar.

ይህ ግላዊ ገፅ ሲሆን የካፒታል ገበያ፣ የኢንቨስትመንት እና የኢኮኖሚ ሀሳቦች እና ዕሳቤዎች ይቀርቡበታል።
Dedicated page to share insights, information, and documents about Capital Market and Investment in Ethiopia.

Now Available Online!We’re excited to announce that the Amharic version of our Rulebook and An Interpretative Guidance N...
13/06/2025

Now Available Online!

We’re excited to announce that the Amharic version of our Rulebook and An Interpretative Guidance Notes/Explanatory Commentaries to the Rulebook are now accessible on our website.

These resources are designed to help market participants, investors, and stakeholders better understand the regulatory framework guiding our markets.

Our sincere thanks to FSD Ethiopia for their valuable support in making this happen!

🔗 Explore and download here: https://esx.et/equity-market/regulatory-framework/ -df_6616/1/

ESXEthiopia

The ESX Academy is back!We're happy to announce that ESX Academy is back ! Your way to learn about capital markets, inve...
09/06/2025

The ESX Academy is back!
We're happy to announce that ESX Academy is back ! Your way to learn about capital markets, investment opportunities, and the future of finance in Ethiopia.
ESX Academy has expert-led sessions for students, entrepreneurs, and professionals that will give you the information you need to keep up with the market.
Do you have questions or want to sign up for upcoming sessions? You can get in touch with us at academy.esx.et or [email protected]

06/06/2025

እንኳን ለዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል አደረሰዎ!

መልካም በዓል እንዲሆንልዎ ከልብ እንመኛለን!

ዒድ ሙባረክ!

20/04/2025
መልካም የአድዋ ድል በዓል!Happy Adwa Victory Day!
02/03/2025

መልካም የአድዋ ድል በዓል!
Happy Adwa Victory Day!

ኢንቨስትመንት ባንኪንግ ምንድን ነው?ኢትዮጲያ የካፒታል ገበያን ስርዓት በስራ ላይ ለማዋል ወደ ትግበራ ገብታለች:: ይህ ለንግድ ማህበረሰቡና ለዜጎች ታላቅ ብስራት ነው:: የካፒታል ገበያ ዜጎ...
06/02/2025

ኢንቨስትመንት ባንኪንግ ምንድን ነው?

ኢትዮጲያ የካፒታል ገበያን ስርዓት በስራ ላይ ለማዋል ወደ ትግበራ ገብታለች:: ይህ ለንግድ ማህበረሰቡና ለዜጎች ታላቅ ብስራት ነው:: የካፒታል ገበያ ዜጎች በአገራቸው የኢኮኖሚ ግንባታ ላይ ባቅማቸው ለመሳተፍ የሚያችላቸው ስርዓት በመሆኑ የተጀመረውን መልካም አጋጣሚ በመደገፍ የሃገራችን ታላቅነት በኢኮኖሚው ዘርፍ ይደገም ዘንድ የሁሉንም ርብርብ ይጠይቃል::

የቢዲኦ ኢትዮጲያ ማኔጅንግ ፓርትነር አቶ ሚሊዮን ክብረት የካፒታል ገበያ አንዱና ዋናው አካል ስለሆነው ኢንቨስትመንት ባንኪንግ ምንነት እና ዋና ዋና ተግባሮቹ ከተግባራዊ ልምድ ያገኙትን ተሞክሮ ያካፍሉናል:: አቶ ሚሊዮን ክብረት በድርጅቶች ምርመራ (due diligence)፤ ድርጅቶችን ለኢንቨስተሮች ምቹ በማድረግ ሂደት (restructuring)፤ እንዲሁም በድርጅቶች ትመና (business valuation) የኢንቨስትመንት ባንኪንግ ስራዎች ሰፊ ልምድ ያካበቱ ሲሆን በቢዲኦ ኢትዮጲያ ሀገር በቀል ድርጅቶችን ከኢንቨስተሮች በማገናኘት ላለፉት አስር አመታት በሃላፊነት ሲያከናውኑ ቆይተዋል:: በተጨማሪም ቢዲኦ በምስራቅ ኣፍሪካ ባደረጋቸው የኢንቨስትመንት ባንኪንግ እና ኮርፖሬት ፋይናንስ ስራዎች በሰፊው ተሳትፈዋል::

በዚህ ፕሮግራም የሚከተሉት ዋና ዋና ጉዳዮች ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል

1) ኢንቨስትመንት ባንኪንግ ምንድን ነው?

2) የኢንቨስትመንት ባንኪንግ ዋና ዋና ስራዎች ምንድን ናቸው?

3) ኢንቨስትመንት ባንኪንግ ከንግድ ባንክ በምን ይለያል?

4) ኢንቨስትመንት ባንክ ለሃገራችን ያለው ፋይዳ ምንድን ነው?

5) ኢንቨስትመንት ባንኪንግ የንግድ ባንኮችን ስራ አይሻማም?

https://lnkd.in/eiWtrdXv
Million Kibret (MD - BDO Ethiopia)

01/02/2025

ጥንትም ሆነ አሁን አስፈላጊነቱ ባያጠያይቅም በተለይ ደግሞ በመጪው ጊዜ ያለ በቂ እውቀት ክምችት ልንኖር እንቸገራለን። እንደ መስመራችን (fields) ሊጠቅመን እና ልንጠቀምበት የምንችለውን የእውቀት አዝመራ በተቻለ መጠን ወደ ጎተራው (አዕምሮአችን) ማስገባት ይጠበቅብናል።

በዚህ እውቀት የመሰብሰብ ሒደት ውስጥ እንደ እምነታችን የክርስትና/እስልምና (ሌላም ሊሆን ይችላል) እውቀት ብሎ ነጣጥሎ አንዱን ጥሎ አንዱን ማንጠልጠል ልከኛ መንገድ አይደለም። እስከጠቀመን ድረስ ሁሉንም ለማወቅ የሚቻለንን ርቀት መጓዝ አለብን።

ለምሣሌ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ተከፍቷል፤ የሌሎች ሐገራት የካፒታል ገበያዎች ላይም መሣተፍ እንችላለን። ከሸሪዓ-ተስማሚ ካፒታል ማርኬት ላይ አዋጭ የኢንቨስትመንት ወይም ፋይናንሲንግ አማራጭ ብናገኝ 'ሙስሊም አይደለሁም' ብለን ልንተወው ነው?
የምንከተለው ሐይማኖት እንዳለ ሆኖ ከሸሪዓ ተስማሚው ካፒታል ገበያ በጣም አዋጪ ሆኖ ካገኘነው ውድ (expensive) ወደ ሆነው አማራጭ ለምን እንሔዳለን?

በፋይናንሱም ሆነ በሌላ ፊልድ አውቀን መገኘት ከቀረቡ አማራጮች ከሁሉም የተሻለው ላይ እንድናርፍ ያግዘናል። እናም ስለ ሸሪዓ-ተስማሚ ካፒታል ማርኬት መሠረታዊ ግንዛቤ የምታስጨብጠዋን ተመጥና የተዘጋጀችውን ሞጁል አንብቡ።

የቴሌ'ግራም ሊ'ንክ አስተያየት መስጫ ሳጥን ውስጥ ይገኛል።
መልካም ንባብ! 🙏

ካፒታል ገበያ በኢትዮጵያ: ታሪካዊ ዕይታ![Capital Market in Ethiopia; Historical Perspective]ገበያ (Market) ከመነሻው በሁለት ከፍለን ልናየው እንችላለን። ...
28/01/2025

ካፒታል ገበያ በኢትዮጵያ: ታሪካዊ ዕይታ!
[Capital Market in Ethiopia; Historical Perspective]

ገበያ (Market) ከመነሻው በሁለት ከፍለን ልናየው እንችላለን። የመጀመሪያው የሸቀጣ ሸቀጥ ገበያ (Good and Services market) በዋናነት የሸቀጣ ሸቀጥ እና የአግልግሎት ግብይት የሚደረግበት ሲሆን ሁለተኛው ግን የፋይናንስ እና ፋይናንስ-ነክ ሰነዶች ግብይት የሚፈፀምበት የፋይናንስ ገበያ (Fimancial Market) ነው።

የፋይናንስ ገበያን (Financial Market) እንደገና በሁለት ይከፈላል። አንደኛው የገንዘብ ገበያ (Money Market) የሚባለው ሲሆን በዋናነት የአጭር ግዜ የበጀት ፍላጎትን (< 1 year) ለማሟላት የሚሸጡ የግምጃ ቤት ሰነዶችን (Treasure Bill)፣ በባንኮች መካከል የሚደረግ የብድር ውልን (Inter-Bank lending) ፤ Certification of Deposit, Commercial Paper፤ እና ሎሎችም የሚያካትት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የሠነድ መዋለንዋይ ገበያ (Capital Market) የሚባለው ነው። በካፒታል ገበያ የባለቤትነት ሰነድ (አክሲዮን/Share)፣ የባለእዳነት ሰነድ (ቦንድ/Bond) እና ገንዘብ-ነክ ሰነዶች (other financial assets) የሚገበያዩበት ሲሆን የረጅም ግዜ የፋይናንስ ፍላጎትን (>10 year) የምናሟላበት ገበያ ማለት ነው።

የኢትዮጵያን የካፒታል ገበያ ታሪካዊ ዳራውን ስንመለከት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ እ.ኤ.አ. በ1897 የኢትዮ ጂቡቲን ምድር ባቡር ሐዲድ ለመዘርጋት የ40 ሚሊዮን ፍራንክ አክሲዮን በፈረንሣይ አገር መሸጣቸውን ታሪክ መዝግቧል፡፡ በእሳቸው ዘመን የተቋቋመው የመጀመርያው ባንክ፣ አቢሲኒያ ባንክ ሲመሠረት አክሲዮኖቹ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ ኒውዮርክ፣ ፓሪስ፣ ለንደንና ቪየና እንደተሸጡ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡ በተጨማሪም በ1901 G.C የአሁኑ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በወቅቱ የእርሻ እና ንግድ ማስፋፊያ አ.ማ ተብሎ በአክሲዮን መልክ እንደተመሰረተ ሰነዶች ያሳያሉ። በኋላ በንጉሱ ዘመን የአሁኑ ልማት ባንክ የያኔው State Bank of Ethiopia (የኢትዮጵያ መንግስት ባንክ) የአክሲዮን ሽያጭ ክፍል (Share Exchange Department) አቋቁም በመንግስት ተቋም ደረጃ የአክሲዮን ግብይት እና የክፍያ ማሳለጥ ስራዎችን ይሰራ ነበር። ትንሽ ቆይት ለመጀመሪያ ግዜ የግል ኩባንያ የሆነው Addis Ababa Share Dealing Group የሚባል 1960ዎቹ መጀመሪያ ላይ ተቋቋመ። ይህም በዋናነት የአክሲዮን ግብይትን ይከውን ነበር። አዲስአበባ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮርፖሬሽን ደግሞ capacitated to act as intermediaries in the clearing & settlement of share trading issues. በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች (ለምሳሌ ጎረቤት ሀገር ኬኒያ) ጋር የካፒታል ገበያን የጀመረችበት ወርቃማ ግዜ እንደነበረ ይታወሳል። የአክሲዮን ሽያጭ ግብይቱም በባለሙያዎች ይመራ እንደነበረ፣ ሰፊ ህዝባዊ ተቀባይነት እንደነበረው ዶክመንቶች ያሳያሉ። ለምሳሌ ያኽል በ1959 GC የ 152,300 ብር አክሲዮን ግብይት ሲፈፅም፤ በ1963GC ከ1,159,090 ብር በላይ ዋጋ ያለው የአክሲዮን ግብይት ፈፅሟል። ይህ ማለት በ5 ዓመት ውስጥ ሰፊ እድገትና ተቀባይነት አግኝቶ እንደነበረ ማረጋገጫ ነው።

በኋላ የደርግ መንግስት መምጣት ተጀምሮ የነበረውን የካፒታል ገበያ በእንጭጩ እንዲቀጭ አድርጓል። Addis Ababa Share Dealing Group was legally abolished in 1974GC. የደርግ መንግስት የዕዝ ኢኮኖሚ (Command Economy) ተከታይ ስለነበረ ሁሉም ነገር በመንግሥት ቁጥጥር ውስጥ እንዲሆን 1975 Nationalization ሲታወጅ አክሲዮን ማቋቋምም ሆነ ኃ/የተ/የግ/ማህበር መመስረት በህግ ተከለከለ። የተፈቀደውም ጄኔራል ፓርትነርሽፕ (General partnership) ሲሆን ይህም የካፒታል ጣራ የተቀመጠለት ነበር። የተጀመሩ የግል-ዘርፍ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች በመንግሥት ተወረሱ። ጉዞ ወደ ኋላ ሆነ።

ክፍል ፪ ...ይቀጥላል!

Ethiopian Capital Market Authority
Ethiopian Securities Exchange (ESX)

ሌሎች አዳዲስ ነገሮችን ለማግኘት ቤተሰብ ይሁኑ!🙏

LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/capital-market-in-ethiopia/
Telegram: https://t.me/capitalmarketinethiopia21
TikTok: https://vm.tiktok.com/ZMhW2Q6AD/
Facebook: https://www.facebook.com/profile.php?id=100052394646625

ቻይና ለኮፒ አትታማም😍ለ AI ውድድር Deepseek የሚለውን AI App  አምጥታለች። Download በመደረግ ቀዳሚውን ቦታ ይዟል። ... እንግዲህ አውርዳችሁ ተጠቀሙ።🙏
27/01/2025

ቻይና ለኮፒ አትታማም😍
ለ AI ውድድር Deepseek የሚለውን AI App አምጥታለች። Download በመደረግ ቀዳሚውን ቦታ ይዟል። ... እንግዲህ አውርዳችሁ ተጠቀሙ።🙏

Financial Markets & Institutions.If you need the pdf of this book, you can find it on our Telegram channel. Here is the ...
25/01/2025

Financial Markets & Institutions.

If you need the pdf of this book, you can find it on our Telegram channel. Here is the link https://t.me/capitalmarketinethiopia21.

Sharing is caring. So, share this post!🙏

 Hello everyone,Continuous learning and staying up-to-date with new knowledge are essential for success in life. As Ethi...
25/01/2025



Hello everyone,

Continuous learning and staying up-to-date with new knowledge are essential for success in life. As Ethiopia’s finance sector undergoes various changes and begins aligning with international standards, it’s important for us to equip ourselves with the necessary knowledge to navigate these developments effectively.

With that in mind, We’d like to share a free financial literacy course that covers core concepts and principles of finance. The course is developed by Khan Academy. The course includes 16 units addressing topics such as:

1, Introduction to Financial Literacy
2, Budgeting and Saving
3, Consumer Credit
4, Financial Goals
5, Loans and Debts
6, Insurance
7, Investment and Retirement
8, Scams and Fraud Prevention
9, Careers and Education
10, Taxes and Tax Forms
11, Employment
12, Banking
13, Car Buying
14, Housing
15, Teacher Resources
16, Additional Resources
Although the course is not specifically tailored to Ethiopia’s context, it provides a general understanding of finance that can be applied broadly. This course is not specifically designed for finance individuals, anyone interested in improving their financial knowledge and managing their financial situation, regardless of their background or profession can take them and develop their understanding.

Beyond that, the course is completely FREE! We encourage all of you to take advantage of this opportunity and make the most of it. You can find the link to the course below.

HAPPY LEARNING!

COURSE LINK - https://www.khanacademy.org/college-careers-more/financial-literacy

Address

Bahir Dar

Telephone

+251913279476

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Capital Market In Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share