
25/07/2025
ዮርዳኖስ ለፍልስጤማውያን እርዳታን መላኳ ተሰማ።
➯➯➯➯➯አልጀዢራ
ዮርዳኖስ በጋዛ የረሃብ አደጋ እየጨመረ ወደመጣበት የጋዛ ሰርጥ አካባቢ የነብስ አድን እርዳታ በመላክና ለፍልስጤማዉያን ፈጥኖ በመድረስ ቀዳሚዋ ሀገር መሆኗ ተሰማ ።
በጆርዳን ሃሽሚት በጎ አድራጎት ድርጅት (JHCO) ከአለም ሴንትራል ኩሽና እና ከአለም የምግብ ፕሮግራም ጋር በመተባበር የተላከው የእርዳታ ኮንቮይ ሃሙስ እለት ከአማን ተነስቶ ወደስፍራው መላኩን የመንግስት ቃል አቀባይ መሀመድ ሞማኒ ተናግረዋል።
ሞማኒ ለዮርዳኖስ ሮያ የዜና ጣቢያ በሰጠው መግለጫ ምንም እንኳን መሰናክሎች እና ተግዳሮቶች ቢኖሩም ዮርዳኖስ "እርዳታን በማስጀመር እና በመላክ ከመጀመሪያዎቹ መካከል በመሆኗ ኩራት ይሰማታል" ብሏል።
ባለፉት 10 ቀናት ውስጥ 147 የጭነት መኪናዎች የተውጣጡ አምስት ኮንቮይዎች ወደ ጋዛ መላካቸውን የገለፁት ሚኒስተሩ በዚህ ዙር 50 የጭነት መኪና ኮንቮይ ዱቄት፣ እህል፣ ዘይት እና የህጻናት ፎርሙላዎችን ጨምሮ አስፈላጊ የምግብ ምርቶችን መያዙን ገልፀዋል ።
የዮርዳኖስ የዜና ወኪል እንደገለጸው እርዳታን ለማድረስ የሚደረገው ጥረት በእስራኤል ድንበር ላይ ረጅም መጓተት እንደገጠመው እና እርዳታውን ለመቀበል ወደ መሻገሪያ በሚመጡት ተስፋ የቆረጡ ሲቪሎች ላይ የእስራኤል ወታደሮች በቀጥታ ጥይቶች ይተኩሳሉ ብሏል።
የዮርዳኖስ መንግሥቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ የእርዳታ መኪናዎችን ወደ ጋዛ ለመላክ ዝግጁ ብትሆንም ነገር ግን እስራኤል ፍቃደኛ አለመሆኗን የገለፁ ሲሆን “የእስራኤል መሰናክሎች ጋዛ ላይ ለመድረስ ቀዳሚ እንቅፋት ሆነው ቀጥለዋል” በማለት የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ለተጨማሪ እርዳታ ግፊት ለማድረግ “ሁሉንም እድሎች ” እንደሚጠቀም ተናግሯል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በጋዛ ያለው ሰብአዊ ቀዉስ መቀጠሉን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገልጿል ደ
እንደ ተቋሙ ገለፃ ከሆነ በግንቦት ወር በዩናይትድ ስቴትስ እና በእስራኤል የሚደገፈው የጋዛ ሰብአዊ ፋውንዴሽን ኦፕሬሽንን ከተቆጣጠረ በኋላ የእስራኤል ወታደሮች ምግብ ለማግኘት ሲሉ ከ1,000 በላይ ፍልስጤማውያንን መግደላቸውን በዚህ ሳምንት ተናግሯል።
➯አልጀዚራ