ሸጋ ሚዲያ Shega media

  • Home
  • ሸጋ ሚዲያ Shega media

ሸጋ ሚዲያ Shega media Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ሸጋ ሚዲያ Shega media, News & Media Website, .

አንድ መቶ ሰማኒያ ሺህ ብር ይዞ ሞተ....ምን ላድርግ አማክሩኝ ? Inbox ጉርሻየ እነዴት ናችሁ የሆነ ሀሳብ እንድታማክሩልኝ ፈልጌ ነበረ አረብ ሀገር በጣም የምወዳት እህት አለችኝ ለእኔ ...
24/04/2025

አንድ መቶ ሰማኒያ ሺህ ብር ይዞ ሞተ....

ምን ላድርግ አማክሩኝ ?

Inbox ጉርሻየ እነዴት ናችሁ የሆነ ሀሳብ እንድታማክሩልኝ ፈልጌ ነበረ አረብ ሀገር በጣም የምወዳት እህት አለችኝ

ለእኔ ብላ ብዙ ነገር የሆነች እኔ እና ቤተሰባችን በሷ እርዳታ ነው የምንኖረው

አረብ ሀገር ከሄደች 4 አመት ይሆናታል
በጣም ስለምትወደኝ እና ስለምታምነኝ ብሯን በእኔ አካዉንት ነበረ የምታስቀምጠዉ::

እኔም አላሳፍራትም ነበረ በዚህ አመት እኔም ከተመረኩ በሆላ ስራ ከሚሰሩ ሰወች ጋር ተፍ ተፍ ማለት ጀመርኩኝ

በአካባቢያችን ከለ ባለሀብት ጋር ተገናኝተን ስራ አብረን ጀመርኩኝ

3 ሳምንት በፊት አሪፍ ነበረ ማለት በቃ እኔ ትንሽ ብር እሱ ብዙ ብር አድርገን ስራ እያሰራን ነበረ

እኔም በሷ ብር ነበር እየሰራሁ የነበሩኩት

ለካ ሰዉየዉ የብዙ ሰዉ ብድር ነበረትና
በአል ሊደርስ 1 ሳምንት ሴቀረዉ እራሱን አጠፋ

አብረን እንስራ ብዬ የሰጠሁት የምወዳትን የእህቴን
ብር 180000 (አንድ መቶ ሰማኒያ ሺህ ብር) ይዞ ሞተ

ከሞተ በሆላ ግን በጣም ብዙ ሰዎች የኔም እዳ አለበት እያለ ቤተሰቡን እያስጨነቁት ይገኛል ::

እኔም ለቤተሰብ ስጠይቅ ምንም
የምናውቀው ነገር የለም አሉኝ

እንዲሁም እህቴ በቅርብ እመጣለሁ
ቤተሰቦቻችንን ሰርፕራይዝ አደርጋለሁ

አዲስ አበባ መተህ
ሆቴል ይዘህ ትጠብቀኛለህ አለችኝ

እኔ ከክፍለ ሀገር ነዉ የምመጣዉ እና በቃ ጨነቆኛል እንኳን የሷን ብር ለትራንስፖርት እና ሆቴል መያዣ የለኝም

ምን ላድርግ ?
እስኪ ጨነቀኝ እኮ

እስኪ የቤተሰቦችህን (የተከታታዬችን)
ምክር ልቀበል አመሰግናለሁ::

🙏🙏🙏

🌴🌴🌴

በጃፓን ጦርነት ወቅት የወንድሙን ሬሳ (አስክሬን) በጀርባው አዝሎ በጥልቅ ስሜት ሊቀብር ይሄድ የነበረውን ታዳጊ ሕጻን ያስተዋለ አንድ ወታደር!"ለምን እራስህን ታደክማለህ የሕጻኑን እሬሳ ጥለ...
22/04/2025

በጃፓን ጦርነት ወቅት የወንድሙን ሬሳ (አስክሬን) በጀርባው አዝሎ በጥልቅ ስሜት ሊቀብር ይሄድ የነበረውን ታዳጊ ሕጻን ያስተዋለ አንድ ወታደር!

"ለምን እራስህን ታደክማለህ የሕጻኑን እሬሳ ጥለኸው ብትሄድ እኮ ድካምህ ይቀንስልህ አልነበር?" ሲል ጠየቀው::

ሕጻኑም :- "ወንድሜ ነው እኔን አይከብደኝም" አለው::

ያን ጊዜ ጥያቄውን ያቀረበው ወታደር ራሱን መቆጣጠር አልቻለም ... ስሜቱ በጣም ተነካ ... ዓይኖቹ በዕንባ ታጠቡ::

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በጃፓን ይህ ፎቶ የወንድማማችነት፣ የአንድነት ተምሳሌት ሆነ::

እናም ... የሕይወት መርሃችን እንዲህ ቢሆንስ:-
ወንድሜ ነው እኔን አይከብደኝም !
እህቴ ናት እኔን አትከብደኝም !
ወንድምህ ቢወድቅ አንሳው !
እህትህ ብትደክም ከጉኗ ቁም !
ወንድምህ ቢስት በየውሃት መንፈስ አቅናው !
እህትህ ስህተት ብትሰራ ይቅርታህን አትንፈጋት ።

"​​ሕማማተ መስቀል" ተብለው የሚዘከሩት አሥራ ሦስት ሲሆኑ እነዚህም፦             1. በብረት ሐብለ መጋፊያና መጋፊያው እስኪጋጠም ድረስ የኋሊት መታሰሩ2. ከአፍንጫው ደም እስኪውጣ ...
18/04/2025

"​​ሕማማተ መስቀል" ተብለው የሚዘከሩት አሥራ ሦስት ሲሆኑ እነዚህም፦

1. በብረት ሐብለ መጋፊያና መጋፊያው እስኪጋጠም ድረስ የኋሊት መታሰሩ
2. ከአፍንጫው ደም እስኪውጣ ድረስ 25 ጊዜ በጡጫ መመታቱ
3. 65 ጊዜ ከግንድ ማጋጨታቸው
4. 120 ጊዜ በድንጋይ ፊቱን መመታቱ
5. 365 ጊዜ በሽመል መደብደቡ
6. 80 ጊዜ ጽህሙን መነጨቱ
7. 6666 ጊዜ መገረፉ
8. አክሊለ ሦክ በራሱ ላይ መደፋቱ
9. 136 ጊዜ በምድር ላይ መውደቁ
10. ሳዶር፡ አላዶር፡ ኤዴራ፡ ዳናትና ሮዳስ በሚባሉ 5ቱ ቅንዋተ መስቀልበችንካር መቸንከሩ
11. መራራ ሐሞትን መጠጣቱ
12. መስቀሉን ተሸክሞ መንገላታቱ
13. በመስቀል መሰቀሉ ናቸው።

ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተሰጠ የሐዘን መግለጫ የአማራን ህዝብ ካልጨረስኩ እንቅልፍ አልተኛም ያለው ጨፍጫፊው የአብይ አህመድ ቡድን በምስራቅ ጎጃም ዞን እናርጅ እና እናውጋ ወረዳ ገደብ በተባለች...
17/04/2025

ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተሰጠ የሐዘን መግለጫ

የአማራን ህዝብ ካልጨረስኩ እንቅልፍ አልተኛም ያለው ጨፍጫፊው የአብይ አህመድ ቡድን በምስራቅ ጎጃም ዞን እናርጅ እና እናውጋ ወረዳ ገደብ በተባለች አነስተኛ ከተማ ዛሬ ሚያዚያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ከ120 በላይ ንፁሐን በድሮን ተጨፍጭፈዋል ።

በአካባቢው የፋሲካ በዓልን ለማክበር የበዓል ቅድመ ዝግጅት ላይ የነበሩ፣ ቤት ለመስራት በህብረት እንጨት ተሸክመው የነበሩ ንፁሐን የገደብ ከተማ እና አካባቢዋ ነዋሪዎች በግፍ በጅምላ ተጨፍጭፈዋል።

1/ ለአማራ ፋኖ በጎጃም አባላት እና አመራሮች :- በወገኖቻችን ላይ የተፈፀመውን ጅምላ የድሮን ጭፍጨፋ ድርጅታችን የአማራ ፋኖ በጎጃም ለመላው ወገናችን መፅናናትን እየተመኘ በወገናችን ላይ በደረሰው ጅምላ ጭፍጨፋ ከህዝባችን ጎን በመቆም እስከመጨረሻ መስዕዋትነት ለመክፈል ከመቸውም ጊዜ በላይ በተጠንቀቅ ላይ እንድትቆሙ እናሳስባለን ።

2/ ለመላው የአማራ ህዝብ :- በዛሬው ዕለት ሚያዝያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በእናርጅ እና እናውጋ ወረዳ ገደብ ከተማ የተፈፀመው የጅምላ ድሮን ጭፍጨፋ የእያንዳንዱ አማራ ዕጣ ፋንታ መሆኑ ግልፅ ነው።

በመሆኑም በቀጣይ ለምናደርገው ህዝባዊ ጥሪ እና የክተት አዋጅ ከዛሬ ጀምሮ እንድታዘጋጅ እና ይህንን ጨፍጫፊ ስርዓት ለማጥፋት የመጨረሻ መስዕዋትነት በመክፈል ነፃነትህን በክንድህ እና በትግልህ እንድታረጋግጥ ስንል ጥሪ እናቀርባለን ።

በጅምላ የተጨፈጨፉ ወገኖቻችንን ነፍስ በአፀደ ገነት ያኑርልን እያልን ለተጎጂ ቤተሰቦች መፅናናትን እንመኛለን።

ክብር ለሰማዕታት
ድል ለጀግናው አማራ ህዝባዊ ሰራዊት

የአማራ ፋኖ በጎጃም !!

17/04/2025
ፎቶ ፦ የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ይጠቀሙበት የነበረው ዝነኛው ዳሽ ፋይፍ (5) ወይም ቡፋሎ አውሮፕላን ከ37 ዓመታት በኋላ ተጠግኖ የበረራ አገልግሎት እንዲ...
17/04/2025

ፎቶ ፦ የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ይጠቀሙበት የነበረው ዝነኛው ዳሽ ፋይፍ (5) ወይም ቡፋሎ አውሮፕላን ከ37 ዓመታት በኋላ ተጠግኖ የበረራ አገልግሎት እንዲሰጥ ተደረገ።

ሀገር መከላከያ ሰራዊት ፤ አውሮፕኑን ከተጣለበት ጥሻ አንስቶ ማደሱን ገልጿል።

ይህን አውሮፕላን ለመጠገን ከ1 ዓመት በላይ ጊዜ መውሰዱን የገለጸው ሀገር መከላከያ ሰራዊት ለትራንስፖርት ፣ ለፓራሹት ዝላይ እና የካርጎ አገልግሎት መሥጠት ይችላል ብሏል።

የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ኮሎኔል መንግሥቱን ኃይለማርያምን ከሀገር ይዘው የወጡት በወቅቱ ኮፐይለት የነበሩት ካፒቴን ያሬድ ተፈራ በአንድ ወቅት ለአንጋፋው ጋዜጠኛ ደረጄ ኃይሌ በሰጡት ቃለ ምልልስ ስለዚህ ዳሽ ፋይፍ (5) ስለተሰኘው አውሮፕላን ተናግረው ነበር።

ዳሽ ፋይፍ (5) ወይም ቦፋሎ አንድ ስያሜ ሲሆን ዲሃቪላንድ ካናዳ ከሚሰራቸው አውሮፕላኖች አንዱ እንደሆነ ጠቁመው ነበር። በወቅቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዳሽ 6 እና ዳሽ 5 የተባሉ አውሮፕላኖች ነበሩት።

ሁሉም ዳሽ 6 አውሮፕላኖች የሀገር ውስጥ በረራ የሚካሄድባቸው የነበረ ሲሆን ዳሽ 5 የካርጎ፣ የመንገደኛ ፣ የቻርተር ኦፕሬሽን ይሰራበት ነበር። ዳሽ 5 ቁጥሩ 5 ስለሚል አነስተኛ ቢመስልም ከዳሽ 6 ይበልጣል በግዝፈት። ይህ አውሮፕላን በመንገደኛ ደረጃ 42 መንገደኛ የሚይዝ ነው።

አሰራሩም ዲዛይኑም የተለየ ሲሆን በጣም ትልቅ ሁለት ሞተር ነው ያለው። በጣም ለማረፍ አስቸጋሪ የሆኑ ሜዳዎች ላይ ያልተጠረጉ ሜዳዎች ላይ ማረፍ ይችላል። እንደ ወታደራዊ ኦፕሬሽንም የሚያገለግል ነው።

በአጭር የሆነ ራንዌይ ፣ ኮሮኮንች ላይ ፣ ሳር ባለው ሜዳ ላይ ማረፍና መነሳት የሚችል በጣም ጉልበት ያለው አውሮፕላን ነው።

ሲሮጥ እና ሲንደረደርም ' ቡፋሎ ' የተባለውን እንስሳ ይመስል ስለነበር ይኸው ዳሽ ፋይፍ (5)አውሮፕላን ቡፋሎ እየተባለ እንደሚጠራ ካፒቴን ያሬድ ተፈራ አስረድተው ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

" ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የቤተክርስትያኒቱ ንዋያተ ቅዱሳት ባልተገባ ቦታዎች ላይ በመታየታቸው ነው ማስመዝግቡ አስፈላጊ የሆነው " - ቤተክርስቲያኗየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ከ...
17/04/2025

" ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የቤተክርስትያኒቱ ንዋያተ ቅዱሳት ባልተገባ ቦታዎች ላይ በመታየታቸው ነው ማስመዝግቡ አስፈላጊ የሆነው " - ቤተክርስቲያኗ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ከበሮ ፣ ጸናጽል ፣ መቋሚያ እንዲሁም ከ10 በላይ ቅዱሳት መጻሕፍት ይገኙበታል በአዕምሯዊ ንብረትነት አስመዝግባለች።

ቤተክርስቲያኗ " ቅርሶቹን በአዕምሯዊ ንብረትነት ማስመዝገብ አስፈላጊ የሆነው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የቤተክርስትያኒቱ ንዋያተ ቅዱሳት ባልተገባ ቦታዎች ላይ በመታየታቸው ነው " ብላለች።

መላከ ሰላም ቀሲስ ዳዊት ያሬድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን የቅርሳቅርስ ጥበቃ፣ ቤተ መጻሕፍትና ወመዘክር እንዲሁም ሙዚየም መምሪያ ዋና ኃላፊ ናቸው።

ኃላፊው ቤተ ክርስትያኗ ቀደምት የእምነት ተቋም በመሆኗ " በርካታ የአምልኮ መፈፀሚያ ንዋየ ቅዱሳት ባለቤት ናት " ብለዋል።

ቤተ ክርስትያኗ የእነዚህን ቅርሶች የባለቤትነት ማረጋገጫ ለማውጣት ንዋያቱ ከየት መጡ፣ ማንነታቸው ምንድን ነው የሚለውን ስታስጠና ቆይታለች ብለዋል።

የባለቤትነት መብት ሕጋዊ ማረጋገጫ የመያዙ ዋነኛ አስፈላጊነትን በተመለከተም ፥ " ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ - ባለመረዳትም ሊሆን ይችል ይሆናል፤ የቤተክርስትያኒቱ ንዋየ ቅዱሳት ባልተገባ ቦታዎች ላይ የመታየት ሁኔታዎች እየተፈጠሩ በመምጣታቸው ነው። " ብለዋል።

የአእምሯዊ ንብረት መብት ከተረጋገጠላቸው ከቤተክርስቲያኒቱ የዜማ ንዋያተ ቅዱሳት መካከል ፦
- ከበሮ፣
- ጸናጽል፣
- መቋሚያ
- መስቀሎች ጨምሮ 10 ልዩ ልዩ ማለትም የድጓ፣ የዝማሬ፣ የመዋሲት፣ የቅዳሴ መጻሕፍት የሚገኙበት ሲሆን ቤተክርስትያኒቱ " በአግባቡ ተመዝግበው የማረጋገጫ የምስክር ወረቀቱ እጄ ላይ ደርሷል " ብላለች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን በቀጣይ ለሌሎች መጻሕፍት ፣ ለኪነ ሕንፃዎች ፣ ለአልባሳት እና ለቅዱሳት ሥእላት ጭምር የአዕምሯዊ ባለቤትነት መብት ለማውጣት ጥረት ላይ መሆኗን ይፋ አድርጋለች።

አዕምሯዊ ንብረት ምንድን ነው ? ያንብቡ https://telegra.ph/DW-04-16

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

" በቀጣይ 10 ቀናት እስከ 200 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ከማይናማር ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ እየተሰራ ነው " - ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር➡️ " ወደ 242 ልጆች ነገ አርብ ከማይናማር ...
17/04/2025

" በቀጣይ 10 ቀናት እስከ 200 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ከማይናማር ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ እየተሰራ ነው " - ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

➡️ " ወደ 242 ልጆች ነገ አርብ ከማይናማር ወደ ታይላንድ እንደሚገቡ ነግሮናል " - ኮሚቴው

የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በማይናማር በአስከፊ ሁኔታ የሚገኙ ወደ 700 የሚጠጉ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገለጸ።

የሚኒስቴሩ ቤቱ ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው፣ እስካሁን ወደ 130 ዜጎች ከማይናማር መመለሳቸውን አስታውሰው፣ ቀሪዎቹን ኢትዮጵያውያንም ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።

ቃል አቀባዩ በዚህም፣ " በቀጣይ 10 ቀናትም እስከ 200 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ከማይናማር ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ እየተሰራ ነው " ብለዋል።

የወላጆች ኮሚቴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አለ ?

ኮሚቴው ሰሞኑን ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ " ያለውን የቁጥር መፋለሱን ኒው ዴልሂ ያለውንና የቶኪዮ ኢምባሲ ስለአለመገጣጠሙ አንስተን " ነበር ብሏል።

" ‘ ምንም ችግር አያመጣም ዲኬቢኤ ያለው ስክሪንአውት ተደርጎ ወደ ታይላንድ መንግስት ስላልተላለፈ ነው። መጓጓዝ ይጀመር እንጂ የሚያስቸግር የለም ’ " እንዳለው ገልጿል።

የመመለስ ሂደቱን በተመለከተም፣ " ወደ 242 ልጆች ነገ አርብ ከማይናማር ወደ ታይላንድ እንደሚገቡ ነግሮናል። የነገን ቀን እየጠበቅን ነው " ሲል ኮሚቴው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

ኮሚቴው፣ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ሀገራቸው በመመለስ የበኩሉን እንዲያደርግላቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድን ሲጠይቁ እንደነበር አመልክቷል።

" 'ይሄ አየር መንገድ የኢትዮጵያ ህዝብ ንብረት ነው። ከእነዚህ ልጆች መካከል ይህን አየር መንገድ የሚመራ ልጅ ሊፈጠር ይችላል' " የሚል ምላሽ እንደሰጣቸው ነግሮናል።

አየር መንገዱ፣ " 'የተቃጠለባቸውን ቲኬት፣ የሚቀጡትን ቅጣት በማኔጅመንት ወስነን እናነሳለን። ሚስተናገዱበትንም ሁኔታ እናመቻቻለን፣ ጨራሽ ትኬት የሌላቸውን ከኢንጂኦ ጋ ሆነን የተወሰነ ፐርሰንት አድርገን እናስተናግዳቸዋለን፤ ያ ካልሆነም ከመንግስት ጋር ተነጋግረን መፍትሄ እንፈጥራለን። ማንም እዛ አይቀርም ' " እንዳላቸውም ኮሚቴው ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ


እሄን ማየት በራሱ
17/02/2023

እሄን ማየት በራሱ

እኔን ሊገሉኝ ይችላሉ ሲልጌታቸው ረዳ ተናገረ
07/09/2022

እኔን ሊገሉኝ ይችላሉ ሲል
ጌታቸው ረዳ ተናገረ

አዲግራት ይበቃል እያለች ነው!የህወሐት ጉዳይ ይበቃል ሰለቸን አንገበገበን እያለች ነው
23/08/2022

አዲግራት ይበቃል እያለች ነው!
የህወሐት ጉዳይ ይበቃል ሰለቸን አንገበገበን እያለች ነው

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሸጋ ሚዲያ Shega media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share