13/08/2024
አውቀን እንታረም!
ወልቃይት ጠገዴ ላይ 1972ዓ.ም ላይ የተሰራ ስህተት 2016ዓ.ም ላይ አይደገምም!
የ1966ቱን አብዮት ተከትሎ የዘር ጥላቻን መሰረቱ ያደረገ የትግል ትርክት ሲተከል፤ አማራን በመዋቅር የሚያጠቃ ኃይል ወደፊት ተስፈንጥሮ ለመውጣት እርሾ እየያዘ ነበር፡፡ የወቅቱ ሴረኛ ኃይሎች ትግል ሁለት መልክ ነበረው፡፡ በአንድ በኩል ቀጥተኛ ፍረጃ ውስጥ የገቡ እንደወያኔ ያሉ አማራ-ጠል ኃይሎች፤ በሌላ በኩል ደግሞ በአማራ ሕዝብ በተለይም ልሂቃኑ ላይ ውስጣዊ ድብቅ ዓላማ ኑሯቸው ነገር ግን ውስጣቸውን ሳይገልጡ ‹ለጋራ የትግል ዓላማ እንታገላለን› የሚሉ ‹መደባዊ መሳይ› ኃይሎች ነበሩ፡፡
በሁለተኛው ጎራ ከሚመደቡ ኃይሎች አንዱ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኀብረት (EDU) ነው፡፡ ይህ ኃይል ዋና መሪዎቹ መሠረታቸው ትግራይ፤ የጀርባ መደባቸው መሳፍንቶች ሆነው ወታደራዊ አቅሙን ደግሞ በቀድሞው አጠራር የጎንደር ክፍለ-ሃገር ላይ ያደረገ ነበር፡፡
የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኀብረት (EDU) የትግል መነሻው ወታደራዊውን የደርግ ሥርዓት ለመታገል ነው ቢባልም፣ ይህ ኃይል በሂደቱና በፍጻሜው የዋናው ጠላት በር ከፋች ነበር፡፡
‹ኢዲዩ›ን በውጤት ብቻ ሳይሆን በውስጣዊ የድርጅት ታሪኩ ሲታይ፣ በትግል ስም ያቀፋቸውን የአማራ ተወላጅ አርበኞች ያስፈጀና ቀጥተኛ ፍረጃ ውስጥ ለገባው አማራን በ‹‹ጨቋኝነት›› ፈርጆ ለተነሳው ወያኔ መንገድ ጠራጊ ሆኖ ያገለገለ ኃይል ነው፡፡
በተለይም በትግራይ ከመጀመሪያው የወያኔ ኃይል ጋር ተጋጭቶ ከወጣ በኋላ በትግል አካሄድ የተለያየ ቢመስልም፤ በተግባር ግን ለወያኔ መንገድ መጥረግን ያለመ ትግል ያደርግ እንደነበር ታሪኩ ይመሰክራል፡፡ ዘግይቶም ቢሆን ዛሬን እንድንማርበት ያን ታሪክ መመርመር አስፈላጊ ሆኖ ተገንቷል፡፡
የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኀብረት (EDU) ከትግራይ ወጥቶ ወልቃይት-ጠገዴን የትኩረት ማዕከሉ በማድረግ ሲንቀሳቀስ ትግሉ እውነት መስሏቸው ይህን ኃይል የተቀላቀሉ የጎንደር አማራዎች በርካታ ነበሩ፡፡
ጣሊያንን ያንቀጠቀጡ ታላላቅ አርበኞች፣ ባላባቶች፣ ባለፀጋዎች፣… የጎንደር መልክ፤ የአማራ ኩራት፤ የኢትዮጵያ ዳር ድንበር አስከባሪ የሆኑ ትልልቅ ሰዎቻችን ይህን ኃይል ተቀላቅለው ያደረጉት ትግል ከውስጣቸው ባሉ ሴረኛ የትግራይ መሳፍንቶች ተጠልፎ፤ አንድ በአንድ ከትግል ሜዳው ተለቀሙ፡፡ ሞት ለአማራ ብቻ የሆነ እስኪመስል ድረስ ኢዲዩ ውስጥ ያሉ የጎንደር ክፍለ ሃገር ተወላጅ ታጋዮች በየአውደ ውጊያው ወደቁ፡፡
ይህ የ1972 የወያኔ ወረራ መግቢያ ምዕራፍ መንገድ ጠረጋ እንደሆነ ለማወቅ የወቅቱ አባቶቻችን አልታደሉም ነበር፡፡ በርግጥም ሁኔታው ነቢይነትን ይጠይቅ ነበር፡፡
የትግራይ መሳፍንቶች ልብ ግን ቢቆፍሩት አይገኝምና በኢዲዩ ትግል ሥም እንቁ የአማራ ታጋዩችን አስፈጅተው፤ ወያኔ ቀድሞ በተጠረገለት መንገድ (የወልቃይት-ጠገዴ አርበኞች ሞትና መበታተን) ነገር ቀሎለት ተከዜን ተሻግሮ እግሩን ተከለ፡፡
በኢዲዩ፣ ኢሕአፓ፣ ኢሰፓ፣… ትግል የተበታተነው የአማራ ልሂቅ፣ ወልቃይት ጠገዴ ላይ የፀረ ቅኝ-ግዛት ትግሉን በተደራጀ መንገድ ለመጀመር አልታደለም ነበር፡፡ የብሔር ንቃትም አልነበረውም፡፡
ጥቂቶች ‹እጅ አንሰጥም› ያሉ የከፋኝ አርበኞች የፀረ ቅኝ-ግዛት ትግሉን ቢጀምሩትም በኢዲዩ ትግል ሥም በርካታ ጀግኖች ወድቀው ነበርና ወያኔ ወልቃይት ጠገዴን በሽፍትነት ወረራ ይዞ፤ በእጁ በገባው ኮሪደር ራሱን በማጠናከር፣ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ድጋፎችን አግንቶ ወደዋናው ሥልጣን ለመንጠላጠያ ተጠቅሞበታል፡፡
ከ40 ዓመታት በኋላ ታሪክ ራሱን ሊደግም…?
ያለፈው ሃምሳ ዓመት የትግል ታሪካችን