ETHIO PRIME

ETHIO PRIME Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ETHIO PRIME, Digital creator, .

በአዋሽ ፣ መተሀራ ፈንታሌ ተራራ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ መድረሱን የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።" በሬክተር ስኬል 4.9 ነው። 150 ኪሎሜትር አካባቢ ርቀት ላይ የተፈፀመ ነው። ንዝረቱ...
06/10/2024

በአዋሽ ፣ መተሀራ ፈንታሌ ተራራ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ መድረሱን የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።

" በሬክተር ስኬል 4.9 ነው። 150 ኪሎሜትር አካባቢ ርቀት ላይ የተፈፀመ ነው። ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ ተሰምቷል " ብሏል።

" በስምጥ ሸለቆች ውስጥ ንዝራቱ ከማሰማት በሻገር የመሬት መንቀጥቀጥ ከፈንታሌ ተራሮች ውጭ የደረሰ ስለመኖሩ አልተረጋገጠም " ሲል አክሏል።

" በደሴ መስመር እስከ ኮምቦልቻ የታየውም ንዝራቱ ነው። ክስተቱ ከሰሞኑ ጀምሮ በፈንታሌ ተራራ እና አዋሽ አካባቢዎች የነበረ ስሜት ነው " ብሏል።

https://t.me/ethio_prime
https://t.me/ethio_prime

ከመጪው ዓመት ጀምሮ የግል ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ዲግሪ በማሳተም ለተማሪዎቻቸው መስጠት አይችሉም ተባለ።በግል ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች የተማሩ ተማሪዎች ዲግሪ የሚታተምላቸው በትምህርት ሚኒስቴ...
31/07/2024

ከመጪው ዓመት ጀምሮ የግል ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ዲግሪ በማሳተም ለተማሪዎቻቸው መስጠት አይችሉም ተባለ።

በግል ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች የተማሩ ተማሪዎች ዲግሪ የሚታተምላቸው በትምህርት ሚኒስቴር በኩል እንደሆነም ተነግሯል፡፡

ይህንን ያሉት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ(ፕ/ር) ናቸው፡፡

ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ የግል ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ለሚያስተምሯቸው ተማሪዎች ዲግሪ በራሳቸው ማተም እንዲያቆሙ የተናገሩት ሚኒስትሩ፤ ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎቹን ዲግሪ የማተም ስራ እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡

ፕ/ር ብርሀኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ ‘’ሰኪውሪቲይ ፕሪንቲንግ’’ ብለው የጠሩት አዲስ የዲግሪ ህትመት አሰራር ይጀመራል ብለዋል፡፡

ይህም በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሩ ተማሪዎች ዲግሪን የማተም ስልጣን ለት/ት ሚኒስቴር ብቻ የሚሰጥ ነው ተብሏል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎቹን ዲግሪ የሚያትመው ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ውጤት እና ተቋማቱ ለትምህርት ሚኒስቴር በላኩት የመረጃ ቋት(HEMIS) ተምርኩዞ እንደሆነም ሚኒስትሩ ሲናገሩ ሰምተናቸዋል፡፡

የትምህርት ተቋማቱ ላስተማሯቸው ተማሪዎች ለሚታተምላቸው ዲግሪ ህትመት ለትምህርት ሚኒስቴር ክፍያ ይፈፀማሉም ተብሏል፡፡

ይህ አሰራርም ተግባራዊ የሚደረገውም፤ በሀገሪቱ የሚታየው የሀሰት ዲግሪ(ፎርጅድ) ህትመት ለማስቆም ተብሎ እንደሆነ የትምህርት ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡

JOIN ON TELEGRAM

https://t.me/ethio_prime
https://t.me/ethio_prime
https://t.me/ethio_prime

Address


Telephone

+251920479422

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ETHIO PRIME posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ETHIO PRIME:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share