DAGU Communication PLC

DAGU Communication PLC DAGU :
Multimedia
Events management
Advertising
Entertainment
Tour & Travel
Commissioning The only agent for many travel agents in Bahir dar

የድርጅታችን ዳጉ ኮምንኬሽን ፒ ኤል ሲ ቤተሰቦች እንዲሁም የተወዳጁ ሀገራዊ የሬዲዮ ፕሮግራማችን የ "ሔሎ ኢትዮጵያ " አጋሮችና አድማጮች ፤ እንኳን ለ 2018 ዓ/ም አደረሳችሁ ። የምንወዳት...
11/09/2025

የድርጅታችን ዳጉ ኮምንኬሽን ፒ ኤል ሲ ቤተሰቦች እንዲሁም የተወዳጁ ሀገራዊ የሬዲዮ ፕሮግራማችን የ "ሔሎ ኢትዮጵያ " አጋሮችና አድማጮች ፤ እንኳን ለ 2018 ዓ/ም አደረሳችሁ ።
የምንወዳት ሀገራችንን ፈጣሪ ይጠብቅልን !
ማናዬ እውነቱ
ስራ አስኪያጅ

29/01/2025

"ሔሎ ኢትዮጵያ" በዚህ ሳምንት !

ከ4:00 እስከ 6:00 ለሁለት ሰዓታት!

ሰላምና ጤና ይስጣችሁ ውድ አድማጮቻችን!

የረቡዕ ጥር 21 ቀን 2017 ዓ.ም የ"ሔሎ ኢትዮጵያ" ተወዳጅ የሬድዮ ፕሮግራም ይዘቶች የሚከተሉት ናቸው!!

☑️የሔሎ ኢትዮጵያ ማስታወሻ

በሔሎ ኢትዮጵያ ማስታወሻ ለሀገር ፣ለወገን ታላቅ ስራ የሰሩ ኢትዮጵያዊያንን እናስታውሳለን።በዛሬው ማስታወሻችን አንጋፋውን የሚዲያ ሰው አማረ አረጋዊን እናስታውሳለን።

☑️የሔሎ ኢትዮጵያ ልዩ እንግዳ

በርካታ የዜማና የግጥም ሥራዎችን ለብዙ ድምጻውያን ሰጥቷል።ራሱም ድምጻዊ ነው።የተለያዩ አልበሞችንም ፕሮዲዩስ ያደርጋል።ከሰሞኑም ለሙዚቃ አፍቃሪያን የደረሰውን የድምጻዊ አህመድ ሁሴን(ማንጁስ) "አልጣሽ" አልበምንም ፕሮዲዩስ አደርጓል።አንጋፋው የሙዚቃ ሰው አበበ ብርሃኔ።በዛሬ የሔሎ ኢትዮጵያ ልዩ እንግዳች ሠዓታችን በቀጥታ ስልክ መስመራችን ላይ እንግዳ ነው።

☑️የሔሎ ኢትዮጵያ አቨንቶች

በሔሎ ኢትዮጵያ ኤቨንቶች የተመራረጡ ልዩ ልዩ የኤቨንት መረጃዎችን እንጠቋቁማችዋልን።

☑️የሔሎ ኢትዮጵያ ሰሞነኛ ጉዳይ

በሔሎ ኢትዮጵያ ሰሞነኛ ጉዳይ ከሰሞኑ የተሰሙ ሰሞነኛ ጉዳዮችን እንነግራችኋለን።

📌በዩኤስኤይድ የሚደረጉ የእርዳታ ስራዎች እንዲቋረጥ መደረጉ በልዩ በልዩ ተቋማት ላይ በርካታ ተጽዕኖ ማሳደሩ ተነግሯል።በዝርዝር እንነግራችኋለን።

📌የቢላልን አዛን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ እንቅስቃሴ እንደተጀመረ ተሰምቷል።

📌 በኢትዮጵያ ምን ያህል ሰዎች የሞባይል ስልክ ይጠቀማሉ?።ከሰሞኑ የወጣ መረጃ አለ።እንነግራችኋለን።

☑️የሔሎ ኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ ጉዳይ

በሔሎ ኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ ጉዳይ በዓለማችን የተሰሙ ለይት ያሉ መረጃዎችን እናጋራችዋለን።

☑️የሔሎ ኢትዮጵያ ጉብኝት

በሔሎ ኢትዮጵያ ጉብኝት እናንተ ውድ አድማጮቻችን በቀጥታ ስልክ መስመራችን ላይ በመገኘት አካባቢያችውን የምታስጉብኙበት ሰዓታችን እንደተጠበቀ ነው።

☑️የሔሎ ኢትዮጵያ ምርጥ ሙዚቃዎች

በሔሎ ኢትዮጵያ ምርጥ ሙዚቃዎች አንጋፋው የሙዚቃ ሰው አበበ ብርሃኔ የተሳተፈባቸው ምርጥ ሙዚቃዎችን እንጋብዛችኋለን።

በመስተንግዶው ማናዬ እውነቱ፣ ናትናኤል ደበና (ናቲ ማናዬ)፣ ብርቱካን አንለይ አብረናችሁ ቆይታ እናደርጋለን።

አጋሮችን አርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ነው።

"ሔሎ ኢትዮጵያ" ዘወትር ረቡዕ ከረፋዱ 4:00 እስከ 6:00 ለሁለት ሰዓታት በአንጋፋው ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ላይ ይደመጣል።

ውብ ህዝብ ፤ ውብ ሀገር ፤ ኢትዮጵያ!

አቶ ገበያው ታከለ የአለም አቀፉ ጅምናስቲክ ፌዴሬሽን ካውንስል አባል ሆነው ተመረጡ። …. አቶ ገበያው ታከለ የኢትዮጵያ ጅምናስቲክ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ፣ በኳታር ዶሀ በተካሄደው በ85ተኛው ...
01/11/2024

አቶ ገበያው ታከለ የአለም አቀፉ ጅምናስቲክ ፌዴሬሽን ካውንስል አባል ሆነው ተመረጡ።
….
አቶ ገበያው ታከለ የኢትዮጵያ ጅምናስቲክ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ፣ በኳታር ዶሀ በተካሄደው በ85ተኛው የአለም አቀፉ ጅምናስቲክ ፌዴሬሽን ካውንስል (FIG Council) አባል ሆነው በከፍተኛ ድምፅ ተመርጠዋል።

በአለም አቀፉ ጅምናስቲክ ፌዴሬሽን ኮንግረንስ ላት ፣ የአለም አቀፉ ጅምናስቲክ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት፣ ሦስት ምክትል ፕሬዚዳንቶች እና ሰባት የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት፣ እንዲሁም 21 የምክር ቤት አባላት የተመረጡ ሲሆን ከአፍሪካ የካውንስሉን አባላት የድምጽ ብልጫ በመያዝ አቶ ገበያው ታከለ 1ኛ በመሆን መመረጥ ችለዋል።

በኢትዮጵያ የጅምናስቲክ ስፖርት ከሃያ ዓመታት በላይ ሀገራቸውን በማገልገል ላይ የሚገኙት እንዲሁም በአህጉር አቀፍና ዓለማቀፍ የጅምናስቲክ ስፖርት ውድድሮች ላይ በመገኘት አሸናፊዎችን በመሸለም ፣ ከአትላንታ ኦሎምፒክ ጀምሮ ንዑስ የቡድን መሪ እንዲሁም ከአቴንስ ኦሎምፒክ ጀምሮ ደግሞ በተከታታይ ዋና ቡድን መሪና ቲሬጀረር ከመሆን በተጨማሪ ሌሎች ኃላፊነቶችን በስኬት በመወጣት የሚታወቁት ፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሜቴ የክብር አባል አቶ ገበያው ታከለ ፣ የአለም አቀፉ ጅምናስቲክ ፌዴሬሽን ካውንስል (FIG Council) አባል ሆነው መመረጣቸው ለሀገራችን ኢትዮጵያ ብሎም ለአህጉሪቱ የጅምናስቲክ ስፖርት የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ ነው።

85ኛው የአለም አቀፍ ጂምናስቲክስ ፌዴሬሽን ኮንግረስ ከ157 ሀገራት የተውጣጡ ከ500 በላይ የብሄራዊ ጂምናስቲክስ ፌዴሬሽኖች ተወካዮች በተገኙበት ከጥቅምት 14 እስከ 16 ቀን 2017 ዓ/ም ለተከታታይ ሦስት ቀናት በኳታር ዶሃ ተካሂዷል።
HelloEthiopia On FM Addis 97.1

Address

Addis Ababa/
Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when DAGU Communication PLC posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to DAGU Communication PLC:

Share