ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore Yoftahie book shop locate at the center of Bahir Dar city .kebele 04 ቋሪት(ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል

ዮፍታሔ ማለት እግዚአብሔር ይከፍታል ማለት ሲሆን እንድገናም የአገራችን ታላቁና ታዋቂው ባለቅኔ፣ ደራሲ፣ ጸሐፊ ተውኔት ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤን ለማስታወስ የተሰየመ ነው። እኛም የተለያዩ መጻሕፍትን፣ መጽሔትና ጋዜጣን በችርቻሮና በጅምላ ማቅረብና መሸጥ ነው። የተመሠረተውም በ2004 ዓመተ ምህረት ነው። ዓላማችን ንባብን ማስፋፋት እና መጽሐፍ በእያንዳንዱ ሰው እጅ ገብቶ እንዲነበብ ማድረግ ነው።

" ቆማ ፋሲለደስ ክበቡ ክበቡእንኳን ሳር ቅጠሉ ያስደምማል ካቡ "( በታዴ የማመይ ልጅ )የረቀቁ አብያተ ክርስቲያናት፣ የተዋቡ አብያተ መንግሥታት፣ እጹብ የሚያሰኙ ገዳማት ህብረት የፈጠሩበት ...
27/05/2025

" ቆማ ፋሲለደስ ክበቡ ክበቡ
እንኳን ሳር ቅጠሉ ያስደምማል ካቡ "

( በታዴ የማመይ ልጅ )

የረቀቁ አብያተ ክርስቲያናት፣ የተዋቡ አብያተ መንግሥታት፣ እጹብ የሚያሰኙ ገዳማት ህብረት የፈጠሩበት ይህ ስፍራ የአምላክ ድንቅ ጥበብ ይታይበታል ።
ፈጣሪ አሳምሮ የሠራቸው ተራራዎች፣ ሸለቆዎች፣ ኮረብታዎች ታሪክ ይናገራሉ በምድሩ የበዙ ገዳማትና አድባራት ይገኛሉና ዙሪያ ገባቸው ቅዱስ መንፈስ ሞልቷል ። ።
ቆላማ ደጋማ በርሃና ወይንአደጋ የአየር ፀባይ በአንድነት የከተሙበትን ተፈጥሮዉን የተመለከተ ስም አዉጭም በጎ ለም ገር ምድር ነዉና በጌምድር ብሎታል ።
ታዲያ በዛሬው የቱሪዝም ማዕዳችን በዚሁ ግንደ ሃገር ጎንደር ደቡባዊ አቅጣጫ ተጉዘን ዘመናትን የተሻገረ ድንቅ ስፍራ ልንጎበኝ እስቴ ወረዳ ዘልቀን ልናስተዋዉቃችሁ ወደናል ። ታተርፋላችሁና ሃሳብ አስተያየት እየሰጣችሁ ተከተሉን።

ከታላቁ ንጉሥ አፄ ፋሲል ጋር ተያይዞ ስሙ ተደጋግሞ የሚነሳው “ቆማ የፋሲለደስ” መገኛዉ በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ ዉስጥ ሲሆን “ቆማ” ስያሜዋን ያገኘችው በአጼ ፋሲል እናት በንግሥት ወልደ ሳህላ እንደሆነ የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ።
ስያሜው ቅዱስ ፋሲለደስ ቢሆንም ቆማ የሚለዉን መለያ ያገኘው እንዲህ ነበር ይባላል በአፈ ታሪክ ።

በ1657 ዓ.ም. በንጉሥ ሱስንዮስ ሚስት በአጼ ፋሲል እናት በንግሥት ወልደ ሳህላ የበላይ ተከታታይነት ቤተ መቅደሱ ተገንብቶ ከተጠናቀቀ በኋላ የክብረበዓሉ እለት
ለቤተመቅደሱ ምርቃት ሊታረድ የተሰናዳው ነጭ በሬ የእርድ ሂደቱን አቋርጦ አመለጠ። ህዝቡም በሬውን ለመያዝ ሲሮጥ ንግሥቲቱ “በሬውን አትያዙት” አሉ። “ዝምብላችሁ ተከተሉት” ህዝቡም የታዘዘውን ፈጸመ። ለንግሥቲቱ “በሬው የት ደረሰ?” ለሚለው ጥያቄ ሕዝቡ “ቆመ” ሲል የሰጠው ምላሽ እስካሁን የአካባቢው መጠሪያ በመሆን እያገለገለ ይገኛል።

ንግስቲቱ በሬው የቆመበት ሥፍራ አጋጣሚ ሳይሆን ፈቃደ እግዚአብሄር እንደሆነ ተቀበሉ። በመጀመርያ እድሞ (አጥር) እና እቃቤት በድንጋይ እና በኖራ አሰሩ። በመቀጠልም ቤተ-መቅደሱን አሳነጹ። ስለ አሰራሩ የሚያስረዱት የገዳሙ አባት “ግማሹ በኖራና በድንጋይ የታነጸው ቤተ-መቅደስ የተጠናቀቀው በጭቃ ነው። የበቁ አባቶች እድሜሽ አጭር ነው ስላሏት ሞትን ለመቅደም በጭቃ ተጠናቀቀ” ይላሉ።

“ቤተ ክርስቲያኑን በ1624 ዓ.ም. አፄ ፋሲል የደብርና የገዳም ሥርዓት እንዲፈፀምበት ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ቆማ ቅዱስ ፋሲለደስ ብለው ሰይሙታል” የሚሉትን ደግሞ
የገዳሙን መዛግብት እንዳሻቸው መመርመር የሚችሉት ገዳማዉያን ናቸው፡፡

አክለዉም በገዳሙ ዙርያ ያሉ 44 አድባራት የሚገኙ ምእመናን ለገዳሙ ግብር እንዲያስገቡ በ318 አገልጋዮች እንዲገለገል፤ በደናግል መነኮሳት እና አስራ ስምንት ዓመት ባልሞላቸው ዲያቆናት አገልገሎት እንዲሰጥ እንዳደረጉ ያብራራሉ።

በንግሥቲቱ የተሰጠ ሰፊ የእርሻ መሬትም ነበረው። የድመት መሬት (ለእቃ ቤት ጠባቂዋ ድመት የእርሻ መሬት ተዘጋጅቶ ኑግ እየተዘራ ትመገብ ነበር)፣ ለአጽጂዎች፣ ለብረት ባለሙያዎች፣ ለሸማኔዎች መሬት ነበራቸው ይላል የገዳሙ ታሪክ ።
ለርዕስ አድባራት ወገዳማትነት መገደም አጼ ፋሲለደስ እናት ከፍ ያለ አስተዋጽኦም አበርክተዋል ።

የጥንቱ ሕንጻ ኪነ-ቅርጽ ከፋሲል ግቢ ጋር የሚመሳሰል ሲሆን በክብ ቅርፅ የተሰራ ነው። ሦስት ክፍል አለው። በእንክብካቤ እጥረት ቢጎዳም ውበቱን ጨርሶ አልጠፋም። ከመሬት ወደ ላይ 6 ሜትር ከፍታ የካብ ዕድሞ /አጥር/፣ የትምህርት መስጫ ባለ ሰገነት ጉባኤ ቤት አለው።

ቤተ ክርስቲያኑ በሰማዕቱ ቅዱስ ፋሲለደስ ስም የተደበረ ከመሆኑም በላይ ንጉሱ ርዕሰ ገዳማት እንዲሆን አድርገዋል በዘመናቸው መስከረም 11 እና ታህሳስ 11 ክብረ በዓሉ ደማቅ የነበረ ከመሆኑም በላይ ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ክብረ በዓሉን የእስልምና ተከታዮችም ያከብሩት እንደነበር የደብሩ አባቶች ያስረዳሉ።

የንቀት ይሁን ከእዉቀት እጥረት በ 2005 በተደረገለት እድሳት የቤተ ክርስቲያኑ የውጭ ገፅታ በሲሚንቶ የተሰራ በመሆኑ ታሪካዊነቱን አጥፍቶታል። የቤተመቅደሱ እና የቅድስቱ ግድግዳ ግን ጥንት እንደነበረ ስለመሆኑ ሸበቶ ገፅታው ያሳብቃል ።
ለታሪክ ግድ የለሾች በቀመርና በእርጋታ ኖራን ከእንቁላል ተቀይጦ የተሰራዉን በቻይና ስሚንቶ መርገዉ ሞገሱን ቢያደበዝዙትም ታሪክ ዘካሪዎቹ በቅድስቱ ውስጥ 12 የእንጨት ምሰሶዎች አሉ። ምሶሶዎቹ ወይራ እና ጥድ ከእንቧጮ ዛፍ ጋር በማጣበቅ ይዘጋጃል። እንጨቶቹ የተያያዙትም ካለምንም ማጣበቂያ እርስ በርስ በማያያዝ ነው። ምሰሶዎች ሲተከሉ ቤተክርስቲያኑን የሚገነቡት ሰዎች ምሶሶዎቹን መትከል ከብዷቸው ትተውት ሲሄዱ አንድ ባህታዊ ብቻቸውን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንደተከሉት ይነገራል።
የተቆርቋሪ ማጣት የባለሙያዎች ግዴለሽነት ምክንያት የሌለ ያህል የተረሳውና ለአካባቢው የቱሪዝም መስህብ መዳረሻ መሆን የሚችለው ገዳም በአባቶች ተጋድሎና ጠባቂነት ዛሬም ድረስ አራት መቶ አመታትን የተሻገሩ እንድንመለከተው የተፈቀዱና ያለውን ተፈቀዱ ብዙ ጥንታዊ ቅርሶችን ይዞል ከአፄ ፋሲል፣ ከንግሥት ወልደሳህላ እና ከሌሎች ነገሥታት የተበረከቱ የብራና መጻሕፍት፣ የብረት ደውል፣ የብር ከበሮ፣ ነጋሪት፣ የወርቅ መስቀል እና ልዩልዩ ጥንታዊ ቅርሶች ጎብኝ ሊመለከታቸዉ የሚችሉ መካከል ይጠቀሳሉ ።

በተጨማሪም በዚህ ቤተክርስቲያን ከሚገኙ ጥንታዊና የማይቀሳቀሱ ቅርሶች መካከል የግድግዳ ላይ ሥዕሎች፣ በጎንደር ዘመነ መንግሥት የግንባታ ጥበብ የተሰሩት የቤተክርስቲያኑ አጥር፣ እቃ ቤት እና ሕንፃ ቤተክርስቲያኑ ናቸው።
ከዚህም ባሻገር ይህን ቤተክርስቲያን ልዩ ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ እቃ ቤቱ እና የቤተክርስቲያኑ ጉልላት ላይ ያሉ መስቀሎች ሙሉ በሙሉ በወርቅ የተሰሩ መሆናቸው ነው። ሌሎችም ለበርካታ ዓመታት የኖሩ ቅርሶች ከብር፣ ከወርቅ፣ ከእምነ በረድ ከሌሎች ማዕድናት የተሰሩ ንዋየ ቅድሳት ይገኛሉ።
ቆማ ፋሲለደስ በጣልያን ወረራ ወቅትም ለመዳፈር በሞከሩት ወራሪዎች ላይ ተዓምር ተፈፅሞበታል ።
ሌላው የዚህ ገዳም መገለጫ ደግሞ ዜማው ነዉ ።

የቆማ ዜና ርክርኩ(ጉሮሮ) ረዥም በመሆኑ አንድ አንድ ቦታ ላይ ዘሩ (ቁጥሩ) የሚለይ መሆኑ እና ዜማውን ለመማር ክብደት ያለው በመሆኑ ከሌሎች ዜማዎች ይለያል። የቆማ ዜማ ድጓ መጻሕፍት በታላላቅ ገዳማትና አድባራት የሚገኝ ሲሆን በአክሱም፣ ላሊበላ እና በመካነ ኢየሱስ እንደሚገኝ ይገመታል። የቆሜ ዜማ ምስክርነት የሚሰጠው በቆማ ፋሲለደስ ቤተክርስቲያን ነው።

እንደ አንድ የታሪኬ ጉዳይ ያገባኛል የአባቶቼ ልጅ ነኝ ለሚል ሰዉ ይህ ቅርስ የተያዘበት ሁኔታን ተመልክቶ ማዘኑና አይቀርም ለነገሩ እንዲህና መሰል የማንነት ምልክቶች አተኩሮ የሚሰራው የራዲዮ ዝግጂታችን በስፖንሰር ማጣት በአጋዥ አለመኖር ለመቆም ጫፍ ላይ ባለበት ሁኔታ ከእዝነት ዉጭ ሌላ የማድረግ አቅሙ የለኝምና ዝም ብዬ አንድ እንኳን ሃገር ወዳድ ቢገኝ ያየሁትን አስጊ የህልውና አደጋ ጠቁሟ ላብቃ ።
በአሁኑ ወቅት በቤተ ክርስቲያኑ በርካታ ረዥም እድሜ ያስቆጠሩ ቅርሶች ቢገኙም የሌላ የጠላት ንብረት ይመስል በአያያዝ ችግርና ባለመጠገናቸው እየተበላሹ መሆኑን ታዝቢያለሁ ። እነዚህም ችግሮች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገኙ የግድግዳ ሥዕሎች መበላሸት እና በእቃ ቤቱ የሚገኙ ቅርሶች በቦታ ጥበት ምክንያት ተደራርበው በመቀመጣቸው እየተጎዱ ይገኛሉ ትኩረት ይሻሉ። እናም ሲያሻን በዘፈን ወይም በግጥም የ ነገስታትን የጀብደኝነት ታሪክና የእነሱ ልጅነት ደጋግሞ መናገር ሳይሆን አሻራቸውን መጠበቅ ነዉ የእዉነተኛዉ ልጅነት መገለጫ እያልኩ ላብቃ ።

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore

t.me/yoftahiebooks

የአፍ አዝመራ       በተዋቸው ወርቁ አካሉ          t.me/yoftahiebooks
27/05/2025

የአፍ አዝመራ

በተዋቸው ወርቁ አካሉ

t.me/yoftahiebooks

ሙሓዘ ስብሐት መጽሐፈ ሰዓታት ዘአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ      #አዘጋጅ  መምህር ኤፍሬም ዓሥራት          t.me/yoftahiebooks
26/05/2025

ሙሓዘ ስብሐት መጽሐፈ ሰዓታት ዘአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
#አዘጋጅ መምህር ኤፍሬም ዓሥራት

t.me/yoftahiebooks

26/05/2025





✅ ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
26/05/2025

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore

ጠባሳዬን ሳየው ጠባሼ ትዝ አለኝወይኔ ወይኔ ወይኔከዚያኔው የባሰ አሁን ነው ያመመኝ።ያ'ገሬ አዎቂዎችጠባሳ 'ሚያጠፋ ቅጠል ቢበጥሱም"ወይኔ"ን ለማሻር ግን በፍጹም አይደርሱም።   Solomon ...
24/05/2025

ጠባሳዬን ሳየው ጠባሼ ትዝ አለኝ
ወይኔ ወይኔ ወይኔ
ከዚያኔው የባሰ አሁን ነው ያመመኝ።

ያ'ገሬ አዎቂዎች
ጠባሳ 'ሚያጠፋ ቅጠል ቢበጥሱም
"ወይኔ"ን ለማሻር ግን በፍጹም አይደርሱም።
Solomon Sahele Tizazu





✅ ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
አድራሻችን
👇
+251918004191 +251902093535
Contact -
t.me/yoftahiebooks
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል
ሜላት ካፌ ፊት ለፊት ወደ ተክሌ ሆቴል ( አባይ ኢንተርናሽናል ሆቴል) በሚወስደው ኮበል በስተቀኝ #መጻሕፍትን በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ።
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore

24/05/2025





✅ ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
አድራሻችን
👇
+251918004191 +251902093535
Contact -
t.me/yoftahiebooks
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል
ሜላት ካፌ ፊት ለፊት ወደ ተክሌ ሆቴል ( አባይ ኢንተርናሽናል ሆቴል) በሚወስደው ኮበል በስተቀኝ #መጻሕፍትን በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ።
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore

              ✅ ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore           t.me/yoftahiebooks
23/05/2025





✅ ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore

t.me/yoftahiebooks

23/05/2025
              ✅ ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore        አድራሻችን               👇+251918004191   +251902093535    Contact...
22/05/2025





✅ ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
አድራሻችን
👇
+251918004191 +251902093535
Contact -
t.me/yoftahiebooks
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል
ሜላት ካፌ ፊት ለፊት ወደ ተክሌ ሆቴል ( አባይ ኢንተርናሽናል ሆቴል) በሚወስደው ኮበል በስተቀኝ #መጻሕፍትን በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ።
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore

              ✅ ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore        አድራሻችን               👇+251918004191   +251902093535    Contact...
22/05/2025





✅ ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
አድራሻችን
👇
+251918004191 +251902093535
Contact -
t.me/yoftahiebooks
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል
ሜላት ካፌ ፊት ለፊት ወደ ተክሌ ሆቴል ( አባይ ኢንተርናሽናል ሆቴል) በሚወስደው ኮበል በስተቀኝ #መጻሕፍትን በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ።

Address

St. Giorgis Road
Bahir Dar
6000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore:

Share