
11/10/2025
"በክልሉ በተወሰደ ህግን የማስከበር ተግባር ድል ተመዝግቧል" የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ
በክልሉ በተወሰደ ህግን የማስከበር ተግባር ድል ተመዝግቧል ሲል የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ገለጸ።
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ እንደገለጸው፦ ከመስከረም 25/2018 ዓ.ም ጀምሮ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአድማ መከላከል ፖሊስ እንዲሁም ሌሎች የክልሉ የጸጥታ ኃይሎች ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ጋር በጋራ በወሰዱት ህግ የማስከበር ዘመቻ ድልን ተቀናጅተዋል።
በዚህም በሰሜን ወሎ ዞን፦ ጋሸና፣ መርሳ ከተማ ዋድላና ሀብሩ ወረዳ እንዲሁም በደቡብ ወሎ ዞን፦ ወረኢሉ፣ ከላላ፣ ወረባቦ፣ ቦረና፣ ተንታ፣ ኩታበር ወረዳዎች እና በመካነ ሰላም ከተማ።
በጎጃም ቀጠና፦ በአዊ ባንጃ ወረዳ፣ በደምበጫ፣ በገርጨጭ እና በእንጅባራ የገጠር ቀበሌዎች እንዲሁም በማዕከላዊ፣ በሰሜን እና በደቡብ ጎንደር ዞኖች።
በሰሜን ሸዋ ዞን ታጥቀው የህዝብን ሰላምና ደኅንነት በሚነሱና በሚዘርፉ ህገ-ወጥ ቡድኖች ላይ ህጋዊ እርምጃ ከተወሰደባቸው አካባቢዎች ተጠቃሾች ሲሆኑ በዚህም በበርካታ ህገ-ወጥ ታጣቂዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ የተወሰደባቸው ሲሆን በርካቶችም ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነዋል ብሏል።
በርካታ የጦር መሳሪያዎች፣ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎች ህገ-ወጥ ቡድኖች የሚጠቀሙባቸው ቁሳቁሶች መማረካቸውንም አክሏል።
የአማራን ህዝብ ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ ጥምር ጦሩ የሚያካሂደውን ህግ የማስከበር ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ያስታወቀው።
Amhara Communications