Ethio News

Ethio News ለተሻለ መረጃ ስለመረጡን እናመሰግናለን

15/11/2024

ይሄ ነገር እውነት ይሆን ወገን?

ምሽቱን በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው የመሬት ንዝረት ለ18 ሰከንድ ያህል የቆየ ነው - ዶ/ር ኤልያስ ሌዊ***********************ዛሬ ምሽት በአዲስ አበባ የተለያ...
06/10/2024

ምሽቱን በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው የመሬት ንዝረት ለ18 ሰከንድ ያህል የቆየ ነው - ዶ/ር ኤልያስ ሌዊ
***********************

ዛሬ ምሽት በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው የመሬት ንዝረት ለ18 ሰከንድ ያህል መቆየቱን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጂኦ ፊዚክስ ስፔስ ሳይንስ እና አስትሮኖሚ ተቋም አስታውቋል፡፡

የተቋሙ ዳይሬክተር ዶ/ር ኤልያስ ሌዊ በመዲናዋ የተከሰተው የመሬት ንዝረት በአዋሽ ፈንታሌ ተራራ አካባቢ በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ሞገድ አማካይነት የተፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።

ህብረተሰቡ በአዲስ አበባ የተከሰተው የመሬት ንዝረት መሆኑን አውቆ፤ የእለተ እለት እንቅስቃሴውን በተረጋጋ መንገድ መቀጠል እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

በፈንታሌ ተራራ አካባቢ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.9 ሆኖ የተመዘገበ መሆኑን ዶ/ር ኤልያስ ሌዊ በተለይ ለኢቢሲ ተናግረዋል።

በፈንታሌ ተራራ አካባቢ ከምሽቱ 2 ሰአት ከአስር ደቂቃ ከሶስት ሰከንድ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ሞገዱ በመሬት ውስጥ ተጉዞ አዲስ አበባ በልዩ ልዩ አካባቢዎች ንዝረት መፍጠሩንም ነው ዶ/ር ኤልያስ ያስረዱት።

አሁን የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተበት የፈንታሌ አካባቢ ለመሬት መንቀጥቀጥ የተጋለጠ አካባቢ መሆኑን የገለፁት ዶ/ር ኤልያስ፤ አካባቢው ብዙ ነዋሪ የሌለበት መሆኑንም ተናግረዋል።

ተቋሙ ተጨማሪ መረጃዎችን የማሰባሰብ ስራ እየሰራ መሆኑንም ነው የተናገሩት ዶ/ር ኤልያስ በቀጣይ ዝርዝር መረጃዎችን ተቋሙ እንደሚያቀርብ እና እንዲህ ያለ አደጋ ሲያጋጥም የቤት ቋሚዎች በተለይ ኮንዶሚኒየም ህንጻ ላይ ያሉ ሰዎች ኮለኖች አካባቢ መጠጋት፣ ጠረጴዛ ስር መግባት፣ ሊፍት አለመጠቀም፣ ውጪ ላይ የመብራትና መሰል ምሶሶዎችን አለመጠጋት እንደሚያስፈልግ ዳይሬክተሩ መክረዋል።

በጌታቸው ባልቻ

እስራኤል ተጨማሪ የደቡባዊ ሊባኖስ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ አሳሰበች እስራኤል በሊባኖስ በተመረጡ የሂዝቦላህ ይዞታዎች ላይ የምትፈጽመው የአየር ላይ ጥቃት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አ...
03/10/2024

እስራኤል ተጨማሪ የደቡባዊ ሊባኖስ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ አሳሰበች

እስራኤል በሊባኖስ በተመረጡ የሂዝቦላህ ይዞታዎች ላይ የምትፈጽመው የአየር ላይ ጥቃት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቃለች፡፡

በዛሬው ዕለትም በሊባኖስ መዲና ማዕከላዊና ደቡባዊ ቤሩት በተመረጡ ቦታዎች ላይ የተሳካ የአየር ጥቃት መፈጸሙን የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት አስታውቋል፡፡

ጥቃቱን ተከትሎም እስካሁን የ9 ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን÷ 14 ሰዎች ላይ ደግሞ ጉዳት መድረሱን የሊባኖስ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል በደቡባዊ ሊባኖስ የእስራኤል ጦር ከሂዝቦላህ ታጣቂዎች ጋር የፊት ለፊት ውጊያ እያደረገ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

በውጊያው 8 የሚደርሱ ወታደሮቹ መገደላቸውን የገለጸው የእስራኤል ጦር÷ በቀጣናው በሂዝቦላህ ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል፡፡

ስለሆነም በደቡባዊ ሊባኖስ ተጨማሪ 25 አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች አካባቢውን በፍጥነት ለቀው እንዲወጡ ጦሩ አሳስቧል፡፡

የሂዝቦላህ ታጣቂዎች በበኩላቸው በዛሬው ዕለት በደቡባዊ ሊባኖስ ማሮን አል ራስ በተሰኘ አከባቢ በእስራኤል ወታደሮች ላይ የቦምብ ጥቃት መፈጸማቸውን አስታውቀዋል፡፡

ከሊባኖስ ወደ ሰሜን እስራኤል የሚተኮሱ ሮኬቶች ተጠናክረው ቀጥለው ከትናንት ጀምሮ ከ240 በላይ ሮኬቶች መተኮሳቸው ተመላክቷል፡፡

በዛሬው ዕለት ብቻ 75 ሮኬቶች መተኮሳቸውንና አብዛኛዎቹ ኢላማቸውን ሳያሳኩ መምከናቸውን የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት መግለጹን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የአውሮፓ ህብረት በሊባኖስ ለሰብዓዊ ቀውስ መከላከል ተጨማሪ 30 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ማድረጉን የህብረቱ ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን አስታውቀዋል፡፡

ለ5 ባንክ ላልሆኑ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች የሥራ ፈቃድ ተሰጠየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለአምስት ባንክ ላልሆኑ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች የሥራ ፈቃድ መስጠቱን አስታወቀ፡፡ባንኩ የውጭ ምንዛሪ አገልግ...
02/10/2024

ለ5 ባንክ ላልሆኑ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች የሥራ ፈቃድ ተሰጠ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለአምስት ባንክ ላልሆኑ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች የሥራ ፈቃድ መስጠቱን አስታወቀ፡፡

ባንኩ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎትና ተደራሽነትን ለማስፋፋትና የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ለማዳበር አሁን በሥራ ላይ ካሉት ከባንክ ጋር ከተያያዙ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች በተጨማሪ ከባንክ ጋር ዝምድና የሌላቸው የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎችን ለመክፈት የሚያስችል የውጭ ምንዛሪ መመሪያ ማውጣቱን አስታውሷል፡፡

በዚሁ መሠረት ተፈላጊውን መስፈርት ማሟላታቸው ተረጋግጦ በመመሪያው ንኡስ አንቀጽ 4.2 መሠረት እንዲንቀሳቀሱ ለዱግዳ ፊደሊቲ ኢንቨስትመንት ፒኤልሲ፣ ኢትዮ ኢንዲፔንደንት ፎሬይን ኤክስቼንጅ ቢሮ፣ ግሎባል ኢንዲፔንደንት ፎሬይን ኤክስቼንጅ ቢሮ፣ ሮበስት ኢንዲፔንደንት ፎሬይን ኤክስቼንጅ ቢሮ እና ዮጋ ፎሬክስ ቢሮ ፈቃድ መሰጠቱን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች በሙሉ ተቀባይነት ያላቸው የውጭ ሀገር ጥሬ ገንዘቦችን በመግዛትና በመሸጥ እንዲሁም ከባንኮች ጋር በመቀናጀት ለወጪና ገቢ ንግድ የሚውል የውጭ ምንዛሪ በማመቻቸት የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ገበያ ለማስፋፋትና ለማዳበር የሚረዳ ሚና ይኖራቸዋል ብሏል ባንኩ፡፡

የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች በዋናነት የሚያካሂዱት የውጭ ምንዛሪ ሽያጭም ሆነ ግዥ ወዲያውኑ የሚፈጸም ብቻ እንደሚሆንም ነው ብሔራዊ ባንክ ያስታወቀው፡፡

የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ያለ ጉምሩክ ዴክላራሲዮን ከደንበኞች እስከ 10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር፣ የጉምሩክ ፈቃድ ከሚያቀርቡት ደግሞ ከዚያ በላይ የውጭ ምንዛሪ በጥሬ ገንዘብ መግዛት እንደሚችሉም ተገልጿል፡፡

እንዲሁም ተፈላጊ የጉዞ መረጃ ላላቸው የግል ተጓዦች እስከ 5 ሺህ የአሜሪካ ዶላር፣ ለንግድ ሥራ ተጓዦች ደግሞ እስከ 10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በጥሬ ገንዘብ መሸጥ ይችላሉ ነው የተባለው፡፡

የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የወጡ የአሠራር፣ የደህንነት፣ የሪፖርት አደራረግና የመዝገብ አያያዝ መስፈርቶችን በአግባቡ ተግባራዊ ስለማድረጋቸው ባንኩ ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እንደሚያደርግም በአጽንኦት ገልጿል፡፡

አንዲት እናት በአንድ ጊዜ 4 ሕፃናት ተገላገሉ  በፓዊ አጠቃላይ ሆስፒታል የ42 ዓመት ዕድሜ ያላቸው እናት በአንድ ጊዜ አራት ሕፃናትን ተገላገሉ።ወይዘሮ አደባባይ የሺነህ ነዋሪነታቸው በአዊ ...
19/09/2024

አንዲት እናት በአንድ ጊዜ 4 ሕፃናት ተገላገሉ

በፓዊ አጠቃላይ ሆስፒታል የ42 ዓመት ዕድሜ ያላቸው እናት በአንድ ጊዜ አራት ሕፃናትን ተገላገሉ።

ወይዘሮ አደባባይ የሺነህ ነዋሪነታቸው በአዊ ብሔረሰብ ዞን ጃዊ ወረዳ አሊኩራንድ ቀበሌ ሲሆን÷ በዛሬው እለት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ውስጥ በሚገኘው ፓዊ አጠቃላይ ሆስፒታል ነው ሶስት ወንድና አንድ ሴት የተገላገሉት።

ጨቅላ ህጻናቱ ጊዜያቸው ሳይደርስ በሰባት ወር የተወለዱ በመሆኑ በህፃናት ፅኑ ህሙማን ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

በሆስፒታሉ መንታ መውለድና አልፎ አልፎም አንዲት እናት እስከ ሶስት ሕፃናትን በአንድ ጊዜ መገላገል የተለመደ ቢሆንም በአንድ ጊዜ አራት ሕፃናትን ሲወለዱ ግን የአሁኑ የመጀመሪያ መሆኑን ሚድዋይፈሪ ሞገስ ጌታቸው ተናግረዋል።

ወላጅ እናት የአሁኑን ጨምሮ ለስድስተኛ ጊዜ የወለዱ ሲሆን÷ በአሁኑ ሰዓት በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ የህክምና ባለሙያው ገልጸዋል፡፡

ወ/ሮ አደባባይ በሰላም እንዲገላገሉ ለረዷቸው የሕክምና ባለሙያዎችና የፓዊ ወረዳ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ምስጋና ማቅረባቸውን የፓዊ ወረዳ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያ የዲጂታል መንግሥት ገጽታ ደረጃዋን አሻሻለች*****************************ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የ193 አባል ሀገራት የዲጂታል መንግሥት ገጽታ መለኪ...
18/09/2024

ኢትዮጵያ የዲጂታል መንግሥት ገጽታ ደረጃዋን አሻሻለች
*****************************

ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የ193 አባል ሀገራት የዲጂታል መንግሥት ገጽታ መለኪያ መሰረት ደረጃዋን ማሻሻል ችላለች።

በየሁለት አመቱ የሚወጣው የተባበሩት መንግሥታት አለማቀፋዊ የዲጂታል መንግሥት ገጽታ መለኪያ ትናንት በኒዮርክ ከመንግሥታቱ ስብሰባ ጎን ለጎን ይፋ ሆኗል።

ይህ አለማቀፋዊ የዲጂታል መንግሥት ገጽታ መለኪያ የአለም ሀገራት በየሁለት አመቱ ከሌሎች ሀገራት አንጻር እና በራሳቸው ካሳዩት እድገት ጋር በማነጻጸር ሀገራቱ በዘርፉ ያደረጉትን መሻሻሎች ያስመዘገቧቸውን ለውጦች የሚያሳይ ነው።

በአለም አቀፍ የዲጂታል መንግሥት ገጽታ ሪፖርት መሰረት ኢትዮጵያ ከነበረችበት ደረጃ አስር ደረጃዎችን በማሻሻል 169ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡

በዚህ የዲጂታል መንግሥት ገጽታ የ193 አባል ሀገራት ደረጃ ይፋ የተደረገ ሲሆን ዴንማርክ፣ ኢስቶኒያ እና ሲንጋፑር ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ከ193 አባል ሀገራት የዲጂታል መንግሥት ገጽታ ደረጃ የመጨረሻዎቹን ሦስት ደረጃዎች በመያዝ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ያሉ ሀገራት ሆነዋል፡፡

ቡሩንዲ፣ ሃይቲ፣ የመን፣ ኒጀር፣ አፍጋኒስታን፣ ቻድ እና ኤርትራም ቢሆኑ ዝቅተኛ የዲጂታል መንግስት ገጽታ ያላቸው ሀገራት ሆነዋል።

18/09/2024
22/12/2022

ታሪኩ ባባ አልሞተም|ይኸው አይኖቹን ማየት ችለናል|ወንድማችን ነብስ ለዘላለም ትረፍ|

21/12/2022

ተው ኦርቶዶክስ ተዋህዶን አትንኳት|ተዋህዶን ነክቶ የኖረ የለም|

20/12/2022

Dr. Wodajeneh Meharene ስለ ታሪኩ ባባ ተናገሩ!

20/12/2022

የቅርብ ጊዜ ትዝታዎች|ማዲንጎ አፈወርቅ |ታሪኩ ብርሀን ባባ| ድንቅ ስራዎች|

Address

Bole
Bole

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00

Telephone

+251916817972

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethio News:

Share