
30/06/2025
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ጋር ተወያዩ፡፡
|| የኢፌዴሪ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት ከቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ጋር አድርገዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እንደገለፁት ዩኒቨርሲቲዎች እውነትና ዕውቅት ብቻ የሚፈልቅባቸው ተቋማት ናቸው::
ዩኒቨርሲቲዎች የመማር ማስተማርና የምርምር ማዕከል መሆናቸውን ያነሱት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ዩኒቨርሲቲዎች መንግስት በዘርፉ ያስቀመጣቸውን ዓላማና ግብ መሰረት በማድረግ መስራት አለባቸው ብለዋል::
የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕረዝደንት ዶክተር ደገላ ኤርገኖ በየደረጃው የሚገኙ የዩኒቨርሲቲው አካላት ጋር በተደረገው ዉይይት ተቋሙን ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ ግብ ተጥሎ ተግባር ተኮር ሥራ መጀመሩን ተናግረዋል::
ተቋሙ የጀመራቸው መልካም ስራዎችን ማስቀጠል እና የሚሻሻሉ ተግባራትንም ለይቶ የማሻሻል ሥራ እየተሰራ ነው ብለዋል::
የዩኒቨርሲቲው የ2017 በጀት ዓመት የድጋፍና ክትትል ግብር መልስ እየቀረበ ሲሆን በዉይይቱ ከመድረኩ ተሳታፊዎች ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል::
በውይይቱ ላይ የዩኒቨርሲቲው የስራ ሀላፊዎች፣ መምህራን እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል ሲል የዘገበው የካፋ ቴሌቪዥን ድርጅት ነው::