28/09/2026
የትምህርት ምዝገባ አፈፃፀምና የመማር ማስተማር ስራን በተመለከተ ከወረዳ አመራሮችና ከዘርፉ ባለሙያዎች ጋር የውይይትና የስምርት መድረክ ተካሄደ።
በካፋ ዞን ጨታ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት በ2019 ዓ/ም የትምህርት ምዝገባ አፈፃፀምና የመማር ማስተማር ስራ እንዲሁም በተረጂነት እና በወቅታዊ አጀንዳዎች ዙሪያ ከወረዳ አመራሮችና ከዘርፉ ባለሙያዎች ጋር የውይይትና የስምርት መድረክ ተካሂዷል።
መድረኩን የመሩት የወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሰለሞን ኃይሌ በትምህርቱ ዘርፍ የሚታዩ ስብራቶችን በመጠገን ውጤታማነትን ለማስመዝገብ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል።
ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ተቀምጠው እንዲማሩ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር ያስፈልጋል ያሉት አስተዳዳሪው ወላጆችም መሟላት ያለባቸውን የትምህርት ቁሳቁሶችን በማሟላት ተማሪዎች ሰክኖ እንዲማሩ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።
ሰባዊ ድጋፎችን የሚሹ አካላቶችን በመለየትና በማጥራት በግዜያዊነት እና በቋሚነት አስቸኮይ ድጋፎችን ለማድረግ በወረዳ ደረጃ የተጠናከሩ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ በመጠቆም ውጤታማ የልየታ ስራ እንዲሰራ አሳስበዋል።
የወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ ዘውዴ የእስካሁን የተግባር አፈፃፀምና ወቅታዊ የስምርት አጀንዳዎችን ለባለድርሻ አካላቶች አቅርበዋል።
ስኬታማ የተግባር አፈፃፀም እንዲመዘገብ እና ውጤታማ ስራ እንዲኖር የአመራር ቁርጠኝነትና ቅንጅታዊ አሰራር መጠናከር አለበት ብለዋል።
መደበኛውን የመማር ማስተማር ስራን ውጤታማ ለማድረግ የአመራሮችና የመርሱ አባላቶች ሚና የጎላ ነው በማለት ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ሁሉም ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ላይ እንዲሆኑ መስራት ትልቅ ኃላፊነት የሚጠይቅና መጠናከር ያለበት እንደሆነ ጠቁመዋል።
ከትኩረት አጀንዳዎች በተጨማሪ ወቅታዊ የመንግስትና የፓርቲ ተግባራትን ማሳለጥ ከአመራሩ የሚጠበቅ ነው ያሉት ዋና ተጠሪው በሞዴሊንግ፣ በግብርና፣ በፀጥታ፣ በጤናና መሰል ስራዎች ላይ ውጤታማነት እንዲያስመዘግቡ ጠይቀዋል።
በሁሉም መዋቅሮች ላይ ቀሩ የተባሉ ተግባራቶች ቆጥሮ በመስራት የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገብ ከሁሉም የሚጠበቅ ነው በማለት ለአመራሮችና ደጋፊ ባለሙያዎች የሳይት ስምርት ተሰጥቷል።
የጨታ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት።
ወቅታዊ፣ ተዓማኒ፣ ትኩስና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ፌስቡክና ቴሌግራም ገፆቻችን ይከታተላሉ ፣ይወዳጁ👇👇👇👇👇????
በፌስቡክ፦https://www.facebook.com/profile.php?id=100091368031356
በቴሌግራም፦https://t.me/C12g6/1057?single
በቲክቶክ፦https://vm.tiktok.com/ZMHtnCGMKnVKa-Th2vR/