
30/08/2025
በአመራሩና በአባላቱ ዘንድ እምርታዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ እና የአስተሳሰብ አንድነትን ለመፈጠር ስልጠናው የጎላ ድርሻ አለው፦አቶ ነፃነት ብርሃኑ
ሻማ:-ነሐሴ 24/2017 ዓ.ም (የጨታ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት)
በተከታታይ ለሶስት ቀናት በካፋ ዞን ጨታ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" በሚል መሪ ቃል ለወረዳና ቀበሌ መካከለኛና የበታች አመራርና ለቀበሌ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አመራሮች ስሰጡ የቆየው የስልጠና መድረክ ተጠናቋል።
"ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር" በተሻገረ ህልም፣ በላቀ ትጋት፣ በአስተማማኝ ነገን መስራት"
በመድረኩ የተገኙት የካፋ ዛን ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት መምሪያ ኃላፊ አቶ ነፃነት ብርሃኑ በአመራሩና በአባላቱ ዘንድ እምርታዊ ብልፅግና ለማረጋገጥና የአስተሳሰብ አንድነትን ለመፈጠር ስልጠናው የጎላ ድርሻ አለው ብለዋል።
አቶ ነፃነት ብልፅግና በ2023 ዓ/ም ኢትዮጵያ የአፍርካ ተምሳሌት፣ በ2040 ዓ/ም የዓለም ብልፅግና ተረጋግጦ ኢትዮጵያ የዓለም ተምሳሌት ለመሆን ጠንካራ ትሰራለች በማለት አሁን ላይ በዕቅዷ መሰረት የኢትዮጵያ ተምሳሌት ሆናለች ነው ያለት።
የወረዳው መንግስት ዋና ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ ዘዉዴ እንደገለፁት በተከታታይ ለሦስት ቀናት በሀገር ደረጃ የአመራሩን አቅም ይገነባል ተብሎ የተሰናዳውን የስልጠና ስነድ በወረዳ ደረጃ ሁሉም የመካከለኛና የበታች አመራር በድስፕሊን ተከታትሎ ማጠናቀቃቸውን አንስተዋል።
አቶ አለሙ ፓርቲያችን ብልፅግና ወደ ስልጣን ከመጣበት ግዜ ጀምሮ በረካታ የውስጥ ባንዳና የውጭ ባዳ ሀገሪቱን ለማድከም የተለያዩ ችግሮች መፍጠራቸውን ገልፀው ለፈተናዎች ሳይበገር በርካታ ሀገራዊ ድሎችን ያስመዘገበ መሆኑን አንስተው ለዚህም የአባይ ህዳሴ ግድብ በስኬት መጠናቀቁን ብቻውን ታላቅ መስክር ነው ብለዋል።
የወረዳ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰለሞን ኃይሌ ስልጠናው በሀገር ደረጃ ከፌዴራል ጀምሮ ለሁሉም ስሰጥ መምጣቱንና እስከ ታችናው ደጋፊ አባላት ድረስ እንደሚሰጥ አንስተው ድሎችን የሚያጎላ፣ ስኬቶችን የሚያስቀጥል እና ችግሮችን የሚጋፈጥ ብርቱ አመራርና አባል ለመፈጠር ያተኮረ ነው ብለዋል።
አቶ ሰለሞን በቀጣይ የህዝቡን የመሰረተ ልማት ጥያቄዎችን ለመፈታት ደረጃ በደረጃ ተይዞ እንደሚሰራ ገልፀው መንግስት የመንግስት ሰራተኛ ኑሮ ለማረጋጋት ያደረገውን የኑሮ ማሻሻያ ማድረጉን ተከትሎ አላስፈላጊ ዋጋ የሚጨምሩ አካላት ላይ እርምጃ ለመወሰድ ይሰራል ነው ያሉት።
በኢኮኖሚ የበለፀገች ሀገር ለመገንባት የበለፀገ እና በኢኮኖሚ እራሱን የቻለ ዜጋ መፍጠር እንደሚያስፈልግ የገለፁት አቶ ነፃነት ብርሃኑ ህብረተሰቡን የኢኮኖሚ ባለቤት ለማድረግ ሁሉም አካል ጠንክሮ እንዲሰራ ጠይቀዋል።
በመጨረሻም ከሁሉም የቀበሌ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር የወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የጋራ የግብ ስምምነት ተፈራርመዋል።
በኤልያስ ጋሎ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ፌስቡክ ገፃችንን ይከታተላሉ ፣ይወዳጁ👇👇 https://www.facebook.com/profile.php?id=100091368031356
telegram https://t.me/+qw3dNLrRkgAyNjQ0