
18/12/2024
ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የህንጻ ማሰሪያ ቦታ
ከቦንጋ ከተማ አስተዳደር ተረከበ
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለሚገነባው የህንጻ ማሰሪያ ቦታ ከቦንጋ ከተማ አስተዳደር ሦስት ሄክታር መሬት ተረክቧል።
ፓርቲው ለሚገነብው የህንጻ ማሰሪያ ቦታ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሀብት ልማት አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ መኩሪያ ከቦንጋ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ከአቶ ስዪም ወ/ሚካኤል ካርታና ፕላን ተረክበዋል።
በርክክቡ ወቅት የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሀብት ልማት አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ መኩሪያ እንደገለጹት በቀጣይ የፖለቲካና የአደረጃጀት ስራዎችን ይበልጥ ለማሳለጥ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ገልጸዋል።
የቦንጋ ከተማ አስተዳደርን ላደረገው የቦታ ርክክብ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከልብ ያመሰግናል ተብሏል ።