AberaHoeto ዘኢትዮጵያ

AberaHoeto ዘኢትዮጵያ studied plant science , biodiversity conservation and management . 0917825603

15/06/2025

የአባቶች ቀን
--------------
ዛሬ የአባቶች ቀን ነው አሉ። ብዙዎች ለአባቶቻቸው መልካም ምኞት አስተላልፏሉ። እኔ የሁሉንም ስያነብ ነው የዋልኩት። አሁን ግን ለሶስት አባቶቼ እንኳን አደረሳችሁ ለማለት ፈለኩ ።
1ኛ #ለኢየሱስ ክርስቶስ፦እንደ ፍጡራን እንኳን አደረሰህ ለማለት ባልችልም ለኔ ለልጅህ ለሀጢአተኛ ስትል ሳይገባህ ከሰማየ ሰማያት ወርደህ በእለተ አርብ መስቀል ላይ ውለህ ስለእኔ ክብር ደምህንአፈሰህ ክብር ሥጋህን ቆርሰሃልና አመልኮ ውዳሴ ምስጋና ይድረስህ
2ኛ ፦ ለኔ ስትል ያላደረከው ነገር አለ ብዬ አላምንም ። የኔ መነሻም መድረሻም አንተ ነህና እንኳን አደረሰህ።
3ኛ ከእግዚአብሔር ቀጠሎ ሠላም አስጠባቂ መንግስት ነው። ለሠላማችን ዋስትና መንግስት ነውና ይህን መንግስት እየመሩ ያሉ ክቡር ጠ/ሚ አብይ አህመድ(ዶ/ር) ሦስተኛ አባት ብያለሁ። ስለዚህ እንኳን አደረስዎት።

መልካም የአባቶች ቀን!

Father’s Day
==========
They say today is Father’s Day. Many have already sent their best wishes to their fathers. I was just reading what everyone wrote.
Now, however, I want to say **Happy Father's Day** to my **three fathers**:

1. To Jesus Christ:**
Even though I can't fully express it, I say Happy Father's Day to You who came down from the heavens for me—a sinner—without needing to.
You shed Your glorious blood and gave Your holy body on the cross on Good Friday, not for Yourself, but for me.
So, to You I offer my worship, praise, and thanksgiving.

2. To my biological father:**
There’s nothing I can say that you have not done for me.
You are my beginning and my end.
So, Happy Father’s Day to you.

3. To the Government, which is appointed by God to ensure peace:**
The government is the guardian of our peace.
Therefore, to the honorable Prime Minister Abiy Ahmed(Dr), who is currently leading this government, I refer to as my third father.
To him as well, I say Happy Father’s Day.

Happy Father’s Day!

ምነው የሚያስረዳ አጣሁምን እንደምናገር ከበደኝይህ የልጅ መላአክ ምን በላው?ይህን ሳቅና ሠላምታ ምን እንበል?
10/06/2025

ምነው የሚያስረዳ አጣሁ
ምን እንደምናገር ከበደኝ
ይህ የልጅ መላአክ ምን በላው?
ይህን ሳቅና ሠላምታ ምን እንበል?

07/06/2025

የዋጋ ንረት አሁን ላይ ወደ 13 በመቶ ዝቅ ብሏል፦ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ
*******************

የምርታማነት ማደግና መንግስት የተገበራቸው የገንዘብ ፖሊሲ እርምጃዎች የዋጋ ንረት የሚጨምርበት መጠን እንዲቀንስ ማድረጉን ነው ሚኒስትሩ የገለፁት።

የዋጋ ንረት አሁን ላይ ወደ 13 በመቶ መውረዱን የተናገሩት ሚኒስትሩ የተለያዩ አመላካቾችም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ጤናማ መሆኑን የሚያረጋግጡ ናቸው ብለዋል።

ኮንትሮባንድ እና ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴን ለመከላከልም መንግስት በትኩረት እየሰራ መሆኑንም ነው በማብራሪያቸው የገለፁት።

የግብርና የኢንዱስትሪ እና ማዕድን ዘርፎች ምርታማነት ማደጉንም የገንዘብ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

ከፕሮጀክቶች አፈፃፀም ጋር በተገናኘም ባለፉት ሰባት አመታት የተገኘው ልምድ ተጠናክሮ መቀጠሉን የገለፁት አቶ አሕመድ ሺዴ የተወሰኑ የፀጥታ ችግር ካለባቸው ቦታዎች በስተቀር የመንገድ፣የመስኖ፣የትምህርት፣የጤና እና ሌሎችም የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች በጥሩ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ብለዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አነሳሽነት የተጀመሩት የቱሪስት መስህብ መዳረሻ ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታም በታቀደው ጊዜ እየተከናወነ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

በተሟላ ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በሁሉም የኢኮኖሚ ዘርፎች የተገኙ ውጤቶች ታሪካዊ ናቸው ያሉት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሺዴ የተገኙ ስኬቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል።

Source

04/06/2025
ዛሬ አንድ ድብቅ ፔጅ (fake account) ይመስለኛል ከታች ያሉ ሕጻናትን ፎቶ በመለጠፍ እንዲህ ስል ጻፈ። "ሕጻናትን ወደ ትምህርት ቤት እንጂ ወደ ቤተክርስቲያን አትላኩ" የገጹ ባለቤት ...
04/06/2025

ዛሬ አንድ ድብቅ ፔጅ (fake account) ይመስለኛል ከታች ያሉ ሕጻናትን ፎቶ በመለጠፍ እንዲህ ስል ጻፈ። "ሕጻናትን ወደ ትምህርት ቤት እንጂ ወደ ቤተክርስቲያን አትላኩ" የገጹ ባለቤት Aba Gebremariam ይላል።

በመሠረቱ ታላላቅ የኢኦተቤክ ቤተክርስቲያን ሰዎች በአለማዊ ትምህርት ከዶ/ር እስከ እጩ ፕሮፌሰር ናቸው። ኦርቶዶክስና አለማዊ ትምህርት ተጋጭቶ አያቅም።

ጽንሰ ሐሳቡ ግን በጣም የሚያሳዝን ነው። "አንድ ሕጻን ለምን 30 አመት ሳይሞላ ወደ እግዚአብሔር ቤት ይመጣል? ለምን ዘማሪና ዲያቆን ይሆናል? ከ30 አመት በኋላ እግዚአብሔር ራሱ ጠርቶት ይመጣልና ወደ ቤተክርስቲያን አትላኩ" የምል ነው።

ይህ መልዕክት ጸረ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው። ብዙ የእግዚአብሔር ተጋድሎ ያደረጉ ሕጻናት በልጅነታቸው እግዚአብሔርን ስያገለግሉ እንደነበር ቅዱስ መጽሐፉ ያስተምራል።
“ሳሙኤል ግን ገና ብላቴና ሳለ የበፍታ ኤፉድ ለብሶ በእግዚአብሔር ፊት ያገለግል ነበር።”
— 1ኛ ሳሙኤል 2፥18
አዛሪያ አናኒያ ሚሳኤል የተባሉ ሦሥቱ ሕጻናት ፈጽሞ ለሰው አንሰግድም ብሎ እግዚአብሔርን ያመሰገኑት በልጅነታቸው ነው።
የሠለስቱ መዝሙር 1:1-3
ሌላው ጌታችንና መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር በሚያስተምርበት ጊዜ እንዲህ ብሎአል።
“ሕፃናትን ተዉአቸው፥ ወደ እኔም ይመጡ ዘንድ አትከልክሉአቸው፤ መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉ ናትና አለ፤”
— ማቴዎስ 19፥14

የዚህ ገጽ ሁለት ተልዕኮ አንግቧል። የመጀመሪያ ሕጻናት በልጅነታቸው መታነጻቸው ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ ቤተክርስቲያንን ከመንግስት ጋር ማጋጨት ነው። ለማንኛውም አልተሳካለትም።
ስጋታቸው ይኸው ነው።የሕጻናት አዕምሮ ንጹሕ ወረቀት ነው። አምላካቸውን በንጹሕ አዕምሮ ከተቀበሉ ነገ መበረዝ ከባድ ነው።ወደ ምንፍቅና አለም የሚሄድ አይኖርም ነው። ከዚህ ቀደም የነበሩ አንዳንድ አካባቢ በልጅነታቸው ተኮትኩቶ ሳያድጉ ካደጉ በኋላ መጥቶ ስርአተ ክህነት ተቀብሎ ሳይውሉ ሳያድሩ ወደ ምንፍቅና መንደር የተቀላቀሉ ግለሰቦችን በሥም መቁጠር ይቻላል።
ስለሆነም ቤተክርስቲያኗ ምንም ከአለማዊ ትምህርት ጋር የሚጋጭ ሰዓት አጠቃቀም የላትም። አለማዊ ትምህርት ሰዓታቸውን ተጠቅሞ ከጨረሱ በኋላ ሰንበትና ሰርክ ሰዓት ተጠቅማ ምንም ያልተበረዘ ንጹሕ አዕምሮ ያለው ትውልድ ትፈጥራለች።
በመጨረሻም መልዕክቴ ከተለያየ ሱስ የጸዳና ፈርሐ እግዚአብሔር ያለው ልጅ እንድኖርዎት ከፈለጉ ትርፍ ሰዓቱን ወደ እግዚአብሔር ቤት ይላኩ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

30/05/2025

ማርያም ማርያም ማርያም....

ግንቦት 21 የእሜቤታች ክብረ በዓለት ውስጥ አንዱ ነው። እንኳን አደረሰን  .... ስለ ዛሬ እለት አብራሩ።
29/05/2025

ግንቦት 21 የእሜቤታች ክብረ በዓለት ውስጥ አንዱ ነው። እንኳን አደረሰን
.... ስለ ዛሬ እለት አብራሩ።

25/05/2025

ሰሞኑን አድስ ነገር አለ።
አድስ ሕይወት ይፈጠር ይሁን?
ወደ እውነት መንገድ ይመለስ ይሁን? አብረን የምናየው ነው!

23/05/2025

እግዞኦ ማረነ ክርስቶስ

23/05/2025
23/05/2025

የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ

አበነ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ባደረገው ስብሰባ የሚከተለውን ውሳኔ አስተላልፏል፦

1. ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆርስን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፤
2. ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤
3. ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስን የሐዲያ ሀ/ስብከትን እንደያዙ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
4. ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዘኮሎራዶን የቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ገዳማት ሊቀ ጳጳስ፤
5. ብፁዕ አቡነ ናትናኤልን ሚኒሶታን እንደያዙ የኮሎራዶ ሀ/ስብከትን እንዲመሩ፤
6. ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የደቡብ አፍሪካ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳ ጳስ፤
7. ብፁዕ አቡነ ዕንባቆምን የገዳማት መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ፤
8. ብፁዕ አቡነ ሙሴ አውስትራልያን እንደያዙ የግቢ ቅዱስ ገብርኤልና የበዐታ ለማርያም ገዳም ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ ወስኗል።

12/02/2025

@የአየር ንብረት ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየደረሰ ነው

Address

Bonga
Bonga

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when AberaHoeto ዘኢትዮጵያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to AberaHoeto ዘኢትዮጵያ:

Share