
27/03/2025
ጥርጣሬን ከመከተል መቆጠብ
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
ጥርጣሬ የአንድን ነገር ትክክለኛ መሆን/አለመሆን ለመቀበል መቸገር ነው። ጥርጣሬ የማሰብ ምልክት ቢሆንም የማሰብ ሂደቱ የሚቋጨው ግን በማስረጃ እንጂ በራሱ በጥርጣሬው መሆን የለበትም። ጥርጣሬ ለእውነተኛነቱ ወይም ለሐሰተኛነቱ ማስረጃ ሊፈለግለት የሚገባ ነገር ሆኖ ሳለ ጥርጣሬን ራሱን እንደማስረጃ መውሰድ ስህተት ነው። ማጣራትና ማረጋገጥ እየተቻለ ጥርጣሬን መከተልም አግባብ አይደለም።
አንዳንዶች ጥርጣሬያቸውን ብቻ እንደ ማስረጀ ሲከተሉ ይታያል። ይህ ግን በቁርኣን የተነቀፈ ተግባር ነው። አላህ (ሱወ) እንዲህ ይላል...
"ለእነርሱ በዚህ ምንም እውቀት የላቸውም። የሚከተሉት ጥርጣሬን ብቻ ነው። ጥርጣሬ ከእውነት ምንም አያብቃቃም።" (ሱራ አል ነጅም፡ 28)
11/ ስሜትንና ዝንባሌን ከመከተል መቆጠብ
🍄🍄🍄🍄🍄🍄🍄🍄🍄🍄🍄🍄🍄
አንዳንዶች ለእስልምና ጥላቻ ከማሳየት በቀር ስለሃይማኖቱ ምንም አለማንበባቸው አሳዛኝ ተጨባጫችን ነው። ስለእስልምና ብዙ አሉባልታዎችን ሰምተዋል። አንዱንም ግን በራሳቸው ለማረጋገጥ አልሞከሩም። ማስረጃ ቢጠየቁም ማምጣት አይችሉም። ለያዟቸው አቋሞች ተጨባጭ ማስረጃ የላቸውም። ውስጣቸው ግን በአሉታዊ ስሜትና ኢስላምን በማጣጣል ዝንባሌ ተሞልቷል።
እንዲህ ዓይነት ሰዎች በመልዕክተኛው (ሰዐወ) ዘመን ነበሩ። አላህ ለያዙት አቋም ማስረጃ እንዲያቀርቡ ጥሪ እንዲያቀርቡላቸው ነቢዩ ሙሐመድን (ሰዐወ) አዘዛቸው። ሰዎቹ ግን ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ። ቁርኣኑ ይህንኑ ያወሳል...
"እሺ ባይሉህም የሚከሉት ዝንባሌዎቻቸውን ብቻ መሆኑን ዕወቅ። ከአላህም የሆነ መመሪያ ሳይኖረው ዝንባሌውን ከተከተለ ሰው ይበልጥ የጠመመ አንድም የለም።" (ሱራ አል ቀሶስ፡ 50)
ማስረጃን እንጂ የሰዎችን ከንቱ ስሜትና ፍላጎት መከተል አደገኛ መዘዝ አለው። ቁርኣን እንዲህ ሲል ገልጾታል...
"(ይህ) እውቀት ከመጣልህ በኋላ የእነርሱን ከንቱ ስሜቶች ብትከተል ከአላህ (ቅጣት የሚታደግህ) ረዳትም ጠባቂም አታገኝም።" (ሱራ አል ረዕድ፡ 37)
ሙሉውን ለማንበብ 👇👇👇
https://www.facebook.com/share/p/19JuC8H2Ji/