07/11/2025
የስራ ዕድል ፈጠራ የዜጎች የኑሮ ደረጃ በማሻሻል ድህነትን ለመቀነስ ፍትሀዊ ዕድገት ለማረጋገጥና የማክሮ ኢኮኖሚ ሚዛን ለማስጠበቅ ሚናው የጎላ መሆኑ ተገለፀ ።
ጥቅምት 28/2018ዓ.ም ቡታጅራ
" ጠንካራ ቅንጅት ለዘላቂ የስራ እድል ፈጠራ እምርታ " በሚል መሪ ቃል የምስራቅ ጉራጌ ዞን ስራ ዕድል ፈጠረና ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያ የንቅናቄና የስራ እድል ፈጠራ ምክር ቤት የ2018 ዓ.ም የ4ወር አፈፃፀምና የተሻሻለ የግብ ስምምነት መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር እያካሄደ ነው።
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ስራ ዕድል ፈጠረና ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ ታጁ ነስሩ የስራ ዕድል ፈጠራ የዜጎች የኑሮ ደረጃ በማሻሻል ድህነትን ከመቀነስና ፍትሀዊ ዕድገት ማረጋገጥ የማክሮ ኢኮኖሚ ሚዛን ለማስጠበቅ ሚናው የጎላ መሆኑ ተናግረዋል ።
እንደ ሀገር ዘላቂና አስተማማኝ የስራ ዕድል ለመፍጠር የሪፎርም ስራዎች ተቀርጾ እየተሰራ መሆኑም ገልፈዋል።
መምሪያው በአራት ወር ውስጥ ከ15 ሺ በላይ ዜጎች ስራ መፍጠርሩንና ከ32 ሺ በላይ ስራ ፈላጊዎች ገበያ ተኮር ስልጠና መሰጠቱ ተናግረዋል ።
አያይዘውም ኢንተርፕራይዞች ተጠቃሚ ለማድረግ 583ሄ/ር መሬትና 37ሼዶች ማቅረብ መቻሉ አብራርተዋል ።
ቋሚ የስራ እድል ፈጠራ ለማሻሻል ፣ተዘዋዋሪ ፈንድ ና የውዝፍ እዳ አመላለስ ላይ እንዲሁም የስራ ፈላጊዎችና ኢንተርፕራይዞች በኢትዮጵያ ስራ ገበያ መረጃ ማስመዝገብ በተመለከተ ተሳታፊዎች በሰፊው እንዲመክሩበት ጠቁመዋል።
በመድረኩ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ተወካይና የትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ሰልማን ሳኒ፣የዞኑ ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ እንዳልካቸው ጌታቸው፤ የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ሀላፊ ተወካይና የሚዲያ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ካሳሁን ቱጂ፤ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዝዳንት አቶ ሁሴን ሽፋ፤ የመምሪያ ኃላፊዎች፤ የወረዳና ከተማ አስተዳደር አስተዳዳሪዎች፤ ከንቲባዎች የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤትሀላፊዎች፣ የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ፅ/ቤት ሀላፊዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው ።
ዘገባው የምስራቅ ጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ነው