13/02/2025
ኤርዶጋን ምስራቃዊ እየሩሳሌም ዋና ከተማዋ የሆነች የፍልስጤም ሉዓላዊ መንግስት እንዲመሰረት ጥሪ አቀረቡ
የቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ከኢንዶኔዢያ አቻቸዉ ፕራቦዎ ሱቢያንቶ ጋር በፍልስጤም ጉዳይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫው "ቱርኪ በጋዛ መልሶ ግንባታ ላይ ከኢንዶኔዥያ ጋር ተባብራ መስራትን ለመቀጠል" ያለንን ፍላጎት መግለጽ እንፈልጋለን ብለዋል።
ምስራቃዊ እየሩሳሌም ዋና ከተማዋ የሆነች የፍልስጤም ሉዓላዊ መንግስት ለመመስረትም ጥሪ አቅርበዋል።
ኤርዶጋን ጋዛ እና ፍልስጤማውያን ሰላም እስኪያገኙ ድረስ በቀጠናው ያሉ ሌሎች ሀገራት መረጋጋት እንደማይችሉ አስረግጠዋል።
“በእስራኤል ለ15 ወራት የዘለቀው ጥቃት ያደረሰው አጠቃላይ ጉዳት ወደ 100 ቢሊዮን ዶላር ይጠጋል።
በህጋዊ መርሆች መሰረት ይህ ጉዳት ከአድራጊው መሰብሰብ አለበት” ሲሉ እስራኤልን በመጥቀስ ወንጅለዋል።
በሌላ በኩል የአረብ ሊግ ዋና ጸሃፊ አህመድ አቡል ጌይት ፍልስጤማውያንን ከጋዛ ሰርጥ እና ከዌስት ባንክ ማፈናቀል ለአካባቢው "ተቀባይነት የሌለው" ሲሉ ውድቅ አድርገዋል።
በዱባይ በተካሄደው የአለም መንግስታት ጉባኤ ላይ "የዛሬ ትኩረት በጋዛ ላይ ነው እናም ነገ ፍልስጤምን ታሪካዊ ነዋሪዎቿን ባዶ ለማድረግ በማሰብ ወደ ዌስት ባንክ ትሸጋገራለች" ሲሉ ተደምጠዋል።
"ይህን ሃሳብ ለ100 አመታት ሲዋጋ ለቆየው የአረቡ አለም ተቀባይነት የለውም።"
አቡል ጌይት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ፍልስጤማውያንን ከጋዛ ለማስወጣት በያዙት እቅድ ላይ አስተያየት በመስጠት ንግግሩ በአረቡ አለም በስፋት የተወገዘ ነው ብለዋል።